መስከረም 09 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባንኩ ከታክስ በፊት 4.3 ቢሊዮን ብር ትርፍ ሲያስመዘግብ፣ ጠቅላላ ሀብቱም 111.3 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታውቋል። ባንኩ ከዚህ በፊት ባካሄደው 33ኛ መደበኛ እና 16ኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ 4.3 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማድረጉንና ጠቅላላ ገቢው የ21 በመቶ እድገት በማስመዝገብ 16.4 ቢሊዮን ብር መድረሱን ገልጿል፡፡ እ.ኤ.አ. የ2025-26 በጀት ዓመት የአፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዲሹ ሁሴን፣ የባንኩ የሂሳብ ሚዛን እና የካፒታል አቅም እያደገ መምጣቱን እንዲሁም የባንኩን መደበኛ ስራዎች የሚያቀላጥፉ ቴክኖሎጂ መር ፕሮጀክቶች መተግበራቸውን ገልፀዋል:: የቦርድ ሰብሳቢው አክለውም ባንኩ በበጀት ዓመቱ ያጋጠሙትን የተለያዩ ዓለም አቀፋዊ እና ሀገራዊ ተግዳሮቶች በመቋቋም በፋይናንስና ፋይናንስ ነክ ባልሆኑ የአፈፃፀም መለኪያዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቅሰዋል። የባንኩ ጠቅላላ ሀብት ሰኔ 30 ቀን 2026 ዓ.ም. 111.3 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው 84.3 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር የ32 በመቶ ዕድገት ያሳየ መሆኑን አቶ አብዲሹ ገልፀዋል። በተመሳሳይም የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ 81.3 ቢሊዮን ብር መድረሱን ጠቅሰው፣ ይህም ካለፈው በጀት ዓመት 66.2 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር የ23 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡን በመጠቆም ባንኩ በበጀት ዓመቱ ጠንካራ የሀብት ማሰባሰብ እንቅስቃሴ ማድረጉን እንደሚያሳይ ተናግረዋል፡፡ በተያያዘም ባንኩ በበጀት ዓመቱ 366 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሪ ያገኘ መሆኑን የጠቀሱት አቶ አብዲሹ፣ ይህ አፈፃፀም እ.ኤ.አ. ከ2024-25 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ34 በመቶ ዕድገት እንዳለው ገልፀዋል። ባንኩ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የሰጠው ጠቅላላ ብድርም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የ26 በመቶ እድገት በማስመዝገብ 67.3 ቢሊዮን ብር መድረሱን ጠቅሰዋል፡፡ ባንኩ የቀጣይ ዓመታት የአዲሱን የዳይሬክተሮች ቦርድ የሥራ ድርሻ ያስቀመጠ ሲሆን፣ የዲጂታል አሰራርን ማስፋፋት፣ የአሰራር መዋቅርን ማሳደግ፣ እንዲሁም የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓትን መከተልና መተግበር ዋና ዋናዎቹ እንደሆኑ ተመላክቷል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በመዲናዋ የተከናወኑ ትልልቅ ጉባዔዎች የሆቴል ዘርፉ እንዲነቃቃ እና በቀጣይም ለሚዘጋጁ ሁነቶች እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ እድል የፈጠረ ነው ተባለ
መስከረም 06 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ ከጷጉሜ 1 እስከ ጷጉሜ 5 ድረስ የሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ እና የሁለተኛው... read more
ባለፉት አራት ወራት ውስጥ 420 ሚሊየን ዶላር የውጪ ምንዛሬ ለባንኮች ተሽጧል ተባለ
ሐምሌ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ብሄራዊ ባንክ ከመጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀመሮ በየሁለት ሳምንት ሲያካሂደ የነበረው የውጪ ምንዛሬ ጨረታ... read more
በክልሉ በምሽትና በርቀት ተምረው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 23 ሺህ 281 ተማሪዎች ውስጥ አንድም ተማሪ የማለፊያ ውጤት አለማምጣቱን የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡
ነሐሴ 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በምሽትና በርቀት በግልና በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ትምህርታቸውን ተከታትለው... read more
መሐመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ
ኅዳር 20 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ መሐመድ እንድሪስ አቶ ብናልፍ... read more
የውጭ አገር ዜጎች በኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበት ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ
ሰኔ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባለፈው ግንቦት ወር አጋማሽ ላይ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ የነበረው አዋጅ ዛሬ ሲጸድቅ ከአዋጁ... read more
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ ገዝነት ለመሸጋገር እየተዘጋጀሁ ነው አለ
ኅዳር 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማርና ሌሎች ተግባራትን በላቀ ደረጃ ለመፈፀምና ተወዳዳሪነቱን ለማስቀጠል ወደ ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ... read more
“ሶላር ኢምፐልስ 2” የተባለች አውሮፕላን በፀሐይ ኃይል ብቻ ዓለምን በመዞር ክብረ ወሰን ሰበረች
👉በዜሮ ነዳጅ፣ በዜሮ ልቀት 40,000 ኪሎሜትሮችን በአንድ ጊዜ መብረር ያስችላታል ነው የተባለው
ሐምሌ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአቪዬሽን ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተው... read more
በኢትዮጵያ ፖስታ ተቀጥሮ ሲሰራ የተቋሙን ገንዘብ ለግል ጥቅሙ አውሏል የተባለው ግለሰብ በጽኑ እስራት ተቀጣ
በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ተቀጥሮ ሲሰራ ከተለያዩ የክፍያ አይነቶች የተሰበሰበ ገንዘብን ለግል ጥቅሙ አውሏል የተባለው ግለሰብ በጽኑ እስራትና በገንዘብ መቀጣቱ ተነግሯል፡፡
ተከሳሽ... read more
ፕሬዚዳንት ትራምፕ የኔቶ አንቀጽ 5 ቁርጠኝነትን እና የ5% የመከላከያ ወጪን አደነቁ
ሰኔ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኔዘርላንድስ ሄግ በተካሄደው የኔቶ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ንግግር ባደረጉበት ወቅት፣ የኔቶን የጋራ... read more
ምላሽ ይስጡ