መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ)በበጋ ወራት ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸውን በሚያገኙ የደቡብ እና ደቡብ ምሥራቅ አካባቢዎች ያሉ አርሶ አደሮች የሚያገኙትን ዝናብ በአግባቡ ሊጠቀሙ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሜቴኦሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡ በኢንስቲትዩቱ ትንበያ መሠረት በአካባቢው ለሚገኙ አርሶ አደሮች፣ ከፊል አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች መረጃው እንዲደርስ እየተደረገ መሆኑን የተቋሙ የግብርና ሜቴኦሮሎጂ ባለሙያ አቶ ይመር አሰፋ ገልጸዋል፡፡ በአካባቢው የሚኖሩ አርሶ አደሮች በወቅቱ የመሬት ዝግጅት፣ የዘር ምርጫ እና የግብዓት አቅርቦት ሥራ ማከናወን እንዳለባቸው ጠቅሰዋል፡፡ የተለያየ የዝናብ መጠን እና ሥርጭት ሊያጋጥም ስለሚችል አርሶ አደሮች ከአካባቢያቸው የግብርና ባለሙያዎች ጋር በመመካከር ለዝናብ ሁኔታው ተስማሚ ጊዜ እና የዘር ዓይነት መምረጥ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል በበጋው ወራት የኤልኒኖ ክስተት ለእነዚህ አካባቢዎች አዎንታዊ ሚና እንዳለው የተናገሩት ባለሙያው፤ በሰሜን አጋማሽ አካባቢዎች ደግሞ ሰብል የሚሰበሰብበት ወቅት እንደመሆኑ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የሚያስከትል በመሆኑ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው አብራርተዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን በተለያዩ አማራጮች የበጋ የአየር ትንበያ መረጃ ተደራሽ እንዲሆን ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን አቶ ይመር ገልጸዋል፡፡ በደቡብና ደቡብ ምሥራቅ አካባቢዎች የበልግ ዝናብን የሚጠብቁ አርሶ አደሮች፣ የሚገኘውን የዝናብ ዕድል ወደ ምርት ለመቀየር የዘር፣ የመሬት፣ የግብዓትና የውኃ ዝግጅታቸውን በወቅቱ ማጠናቀቅ እንዳለባቸው ተመልክቷል፡፡ ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በጣሊያን የአውሮፕላን ሞተር ሰው ስቦ አስገባ
በጣሊያን አንድ ሰው በአውሮፕላን ሞተር ተስቦ በመግባቱ የተነሳ ሁሉም የቤርጋሞ አውሮፕላን ማረፊያ በረራዎች እንዲታገዱ ተደረገ
ሐምሌ 1 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በሰሜናዊ ጣሊያን... read more
የኢትዮጵያ የተቀናጀ የቤተሰብ ጥናት በሚቀጥሉት 4 ወራት እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ
በተያዘው አመት መስከረም ወር ላይ የተጀመረው የስነ-ህዝብና ጤና ቆጠራ ባለፉት 8 ወራት ውስጥ በሁሉም የሃገሪቱ ክልሎች በተሰራው ስራ ከግማሽ በላይ... read more
በአንድ “እምቢታ” የጣሊያንን ሕግ የቀየረችው የ17 ዓመት ወጣት ድፍረት!
👉ክብርን ለመጠበቅ ደፋሪን ማግባት ግዴታ ነው የተባለችው ፍራንካ ቪዮላ ማን ናት?
ጥቅምት 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የዛሬ ዓመታት በፊት በጣልያን ሲሲሊ ክልል... read more
ለአጭር ጊዜ ለሚቆይ ዘገባ እና የቀረጻ ስራ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ሙያተኞች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተጠቆመ
ለአጭር ጊዜ የዘገባ እና የቀረፃ ስራ ወደ ሀገር ውስጥ የሚመጡ የውጪ ሀገር መገናኛ ብዙኃን እና የፊልም ድርጅቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ... read more
ምርጫ ቦርድ አካታችነት የጎደለው አባላትን የሚያቀርቡ ፓርቲዎችን ለመቆጣጠር የዲጂታል አሰራር ማዘጋጀቱ ገለጸ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በቀጣይ አመት ለሚኖረው ሃገራዊ ምርጫ በርካታ የቅድመ ዝግጅት ሰራዎችን መስራቱን ገልጿል ። በተለይም ምርጫ በደረሰ ጊዜ... read more
የ7 ዓመት ህፃን የደፈረው ግለሰብ ከማንኛውም ህዝባዊ መብቶች እንዲታገድ ተወሰነበት
በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ የሰባት ዓመት ህፃን ልጅ አስገድዶ የደፈረው በእስራት መቀጣቱን የቃሉ ወረዳ ፖሊስ አስታውቋል።
ተከሳሹ በእስራት... read more
ራስ-የሌለው ዶሮ
👉ለአንድ ዓመት ተኩል በሕይወት በመቆየት ዓለምን ያስደመመው የዶሮው ተዓምራዊ ታሪክ
ነሐሴ 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዘመናት ተዓምር ተብሎ የሚጠራው እና በዓለም... read more
በአማራ ክልል በተያዘው መጋቢት ወር መጨረሻ የአጀንዳ ማሰባሰብ እንደሚጀመር ተገለጸ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በመጋቢት ወር መጨረሻ ቀናት በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ እንደሚያካሂድ አስታውቋል።
በመሆኑም የወረዳ... read more
የፈረንጆች አዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ርችት እንደሚተኮስ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ
ታኅሳስ 22 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የደህንነትና ልዩ ኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ዛሬ ታህሳስ 22 ቀን 2017... read more
በዘንድሮ በጀት ዓመት ለህዳሴው ግድብ እስካሁን 1 ነጥብ 25 ቢሊየን ብር መሰብሰቡ ተገለጸ
የህዳሴው ግድብ የመሰረት ድንጋይ በ2003 ዓ/ም መጋቢት 24 ከተጣለ ጀምሮ በተለያዩ መንገዶች የገቢ ማሰባሰቢያ እየተደረገ ይገኛል፡፡
የዘንድሮ ዓመት የግድቡ ግንባታ ማጠናቀቂያ... read more
ምላሽ ይስጡ