መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሚገኙ 5 ነባር ብሔረሰቦች መካከል አንዱ የሆነው የቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ ቋንቋ የመጥፋት አደጋ ላይ በመሆኑ የመንግሥትን ትኩረት እንደሚሻ የአካባቢው ተወላጅና ፖለቲከኛው ዶ/ር መብራቱ አለሙ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል። እያንዳንዱ አርሶ አደር ቢያንስ አንድ ዲግሪ ያለው ልጅ ያለው መሆኑ የቦሮ ሺናሻን ማኅበረሰብ ልዩ ያደርገዋል የሚሉት ዶክተር መብራቱ፣ የብሔረሰቡ ምሁራን ቋንቋውን ለማስቀጠል የማስተዋወቅና የምርምር ሥራ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። መንግሥት ለብሔር ብሔረሰቦች መብት፣ እኩልነትና ባህላቸውን ለማስተዋወቅ የሚያደርገው ድጋፍ አበረታች ቢሆንም፣ ባህል፣ ወግና ቋንቋቸው የመጥፋት አደጋ ለተጋረጠባቸው ብሔረሰቦች ልዩ ትኩረት በመስጠት ጥናት ማድረግ እንደሚገባው ፖለቲከኛው ገልጸዋል። በተለይ ከብሔረሰቡና ከክልሉ ውጪ ለሚኖሩ የብሔረሰቡ ተወላጆች ቋንቋውን በማስተላለፍና በማስቀጠል ረገድ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴርን ትኩረት እንደሚሻ ዶክተር መብራቱ ተናግረዋል። እንደ ማኅበረሰብ አናሳ ከሚባሉት መካከል የቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ ተጠቃሽ ቢሆንም አናሳነቱ በቁጥር እንጂ በባህል ሀብት አይደለም የሚሉት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ የባህልና ሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ኃላፊ አቶ በላይ አፋ ናቸው። የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አሁን ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ የብሔረሰቡን ቋንቋ የመጠበቅና የማስተዋወቅ ሥራ ሊሠራ እንደሚገባው ገልጸዋል። ብሔር ብሔረሰቦች በመዲናዋ ባህላቸውንና የዘመን መለወጫ ሥርዓታቸውን እንዲያከብሩ ከመፍቀድና ከማገዝ በተጨማሪ ቋንቋና ባህላቸው የመጥፋት አደጋ ለተጋረጠባቸው በጥናት ላይ የተመሠረተ ሥራ በመሥራት መጠበቅ እንደሚገባም ተመልክቷል። የቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ክብረ በዓል ከመስከረም 11 እስከ መስከረም 18 ባሉት ቀናት እየተከበረ ይውላል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ደቡብ ሱዳን በዓባይ ወንዝ ላይ ግድብ ለመገንባት መወሰኗ በግብፅ በኩል የነበረውን የውኃ አጠቃቀም የበላይነትና ጫና በጋራ ለመጋራት የሚረዳ ነው ተባለ
መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በዓባይ ወንዝ ላይ የሚገነቡ የኃይል ማመንጫ ግድቦች በታችኞቹ የተፋሰሱ ሀገራት ላይ ተጽዕኖ ቢኖራቸውም፣... read more
የእስራኤል እና የኢራንን ወቅታዊ የህዝብ ብዛትና የቆዳ ስፋት እንዲሁም #ወታደራዊ አቅም ሲዳሰስ
🔰የእስራኤል ዝርዝር መረጃ‼️
እስራኤል በ2025 የህዝብ ብዛቷ ወደ 9,517,181 የተጠጋ ሰዎች እንዳሏት መረጃዎች አመላክተዋል።
የቆዳ ስፋት ደግሞ 22,145 ካሬ ኪሎ ሜትር እንደሆነና... read more
አንድ መርማሪ በግዴታ ስራ ላይ እያለ ከአቅሙ በላይ በሆነ መንገድ ከግድያ ውጪ ማንኛውንም ወንጀል ከፈፀመ ተጠያቂ የማይሆንበት አንቀጽ በምክር ቤት ጸደቀ
👉ይህ አይነቱ አንቀጽ ዜጎችን ለሰብዓዊ መብት ጥስት የሚያጋልጥ ነው ሲሉ የምክር ቤት አባላት ተቃዉሟቸዉን ገልጸዋል፡፡
ሰኔ 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሕዝብ... read more
ፓርቲው ከተሰረዘ በኋላ የሚያደረጋቸው የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ኢ-ህገ መንግስታዊ እንደሚሆን ተገለጸ
አንድ ፓርቲ ከምርጫ ቦርድ ህጋዊ እውቅናውን ካጣ በኋላ የሚያደርገው ማንኛውም እንቅስቃሴ ኢ-ህገ መንግስታዊ ይሆናል ሲሉ የህግና የፌዴራሊዚም ባለሙያዎች ለመናኸሪያ ሬዲዮ... read more
የስርቆት ወንጀል ፈጽሞ በቆሻሻ መውረጃ ትቦ ውስጥ በመግባት ሊያመልጥ የነበረው ተከሳሽ ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ዋለ
👉ወንጀለኛው በ2 ዓመት ከ3 ወር እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን የየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል
ሸጋው አየነው የተባለው ተከሳሽ የወንጀል ድርጊቱን ፈጽሞ... read more
በጣሊያን የአውሮፕላን ሞተር ሰው ስቦ አስገባ
በጣሊያን አንድ ሰው በአውሮፕላን ሞተር ተስቦ በመግባቱ የተነሳ ሁሉም የቤርጋሞ አውሮፕላን ማረፊያ በረራዎች እንዲታገዱ ተደረገ
ሐምሌ 1 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በሰሜናዊ ጣሊያን... read more
በአንድ “እምቢታ” የጣሊያንን ሕግ የቀየረችው የ17 ዓመት ወጣት ድፍረት!
👉ክብርን ለመጠበቅ ደፋሪን ማግባት ግዴታ ነው የተባለችው ፍራንካ ቪዮላ ማን ናት?
ጥቅምት 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የዛሬ ዓመታት በፊት በጣልያን ሲሲሊ ክልል... read more
ህዝቡን ማወያየት አልቻልንም ያሉ እንደራሴዎችና የክልሉ ምላሽ
https://youtu.be/1rmEngeMVGk
read more
ኢራንን የሚደግፉ ወዮላቸው – ትራምፕ
👉
https://youtu.be/e5Nvw7On-xU
በትዕግስቱ በቀለ
read more
ኤሎን ማስክ በትራምፕ ሪፐብሊካን “ትልቅ፣ ቆንጆ ሂሳብ” ላይ ትችታቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል
ሰኔ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የስፔስኤክስ እና ቴስላ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤሎን ማስክ በትራምፕ ሪፐብሊካን አስተዳደር የቀረበውን "ትልቅ፣ ቆንጆ ሂሳብ"("big,... read more
ምላሽ ይስጡ