መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በሀገሪቱ ከሚገኙ አካል ጉዳተኞች መካከል 11.8 በመቶ ያህሉ ብቻ የትምህርት ዕድል እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን ብሔራዊ ማኅበር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የማኅበሩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ገብሬ ተሾመ ተናግረዋል። የትምህርት ዕድል ያላገኙ ሕፃናትና አካል ጉዳተኞች ቁጥር ከፍተኛ እንደሆነና ሽፋኑ አሁንም ዝቅተኛ መሆኑን ቁጥራዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩም ገልጸዋል። ወላጆች አካል ጉዳተኛ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ገበታ ከመላክ አንጻር ክፍተት እንዳለባቸው የተናገሩት ኃላፊው፤ ወላጆች ይህንን ችግራቸውን በመቅረፍ ልጆቻቸውን የማስተማር ቀዳሚ ኃላፊነት እንዳለባቸው መዘንጋት የለባቸውም ብለዋል። የትምህርት ዘርፉ ኃላፊዎችና ባለሙያዎችም በሚያካሂዱት የቅኝትና የቁጥጥር ሥራ ወቅት፤ በየአካባቢው ካሉ አካል ጉዳተኞች ምን ያህሉ ትምህርት ቤት እንደገቡ ሊከታተሉና አስፈላጊውን እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ማኅበሩ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ከአማራ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልሎች ትምህርት ቢሮዎች ጋር በመተባበር ያሳተማቸውን የብሬል መጻሕፍት ለዓይነ ስውራን ተማሪዎች ተደራሽ ቢያደርግም በቂ እንዳልሆነ የሚናገሩት አቶ ገብሬ፤ የማኅበሩ ግዴታ መንግሥት ይህንን እንዲያሟላ መጠየቅ ቢሆንም፣ አንዳንድ የመንግሥት አካላት ሳይቀሩ ማኅበሩ እንዲያሟላ ሲጠይቁ ይስተዋላል ብለዋል። የትምህርት ሚኒስቴርን ጨምሮ የክልል ትምህርት ቢሮዎች ለዓይነ ስውራን ተማሪዎች የሚያስፈልጉ የትምህርት ግብዓቶችን በሚፈለገው ልክ ማቅረብ እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡ የአካል ጉዳተኞችና የመምህራን ማኅበራትን ጨምሮ ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት፣ አካል ጉዳተኞች እንደማንኛውም ዜጋ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ከአደጋ ቁጥሮች በስተጀርባ ያሉ ህይወቶች፡ በኢትዮጵያ የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ መዋቅራዊ ለውጥ ለምን ያስፈልጋል?
በየእለቱ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ዜናዎች ላይ “በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰዎች ህይወት አለፈ” የሚሉ መርዶዎችን መስማት የተለመደ የዕለት ተዕለት ክስተት ሆኗል። ነገር... read more
በዝናብ ወቅት የሚከሰት የዶሮ በሽታን ለመከላከል መንግስት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ
ነሐሴ 12 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የዝናብ ወቅት ለዶሮ በሽታ አምጪ ተህዋስያን መራባትና መስፋፋት አመቺ በመሆኑ፣ መንግስት የባለሙያ ድጋፍና የግንዛቤ ማስጨበጫ... read more
የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሰራተኞችን ስራ ለማቆየት ደመወዛቸውን ቀንሰው ከፓይለቶች ያነሰ ገቢ እንዲያገኙ ማድረጋቸው ተገለጸ
ሐምሌ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጃፓን አየር መንገድ (Japan Airlines - JAL) ዋና ስራ አስፈፃሚ የነበሩት ሃሩካ ኒሺማትሱ፣ የኩባንያውን ሰራተኞች... read more
የወረቀት ተረፈ ምርቶችን በድጋሚ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ እየተሰራ ነው ተባለ
በተለያዩ አጋጣሚዎች ጥቅም የላቸውም ተብሎ የሚጣሉ ወረቀት እና ካርቶኖችን ለስራ እድል ፈጠራ እንዲውሉ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አንዲ ማማ ድርጅት አስታውቋል።... read more
በህጻናት ፓርላማዎች የሚነሱ ጥያቄዎች ተፈጻሚ እየሆኑ አይደለም ተባለ
ኅዳር 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የህጻናት መብትን፤ ችግሮችን እና በህጻናት ልጆች ላይ ለሚከሰቱ ጥቃቶች እና መሰል በደሎችን ማስተጋባት እንዲችሉ በህጻናት... read more
የአርሰናል ወጣቶች የዝውውር ውሳኔ ደጋፊዎቹን አስደነገጠ
ሚያዚያ 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) አርሰናል በዚህ ክረምት ከፍተኛ ተስፋ የሚጣልባቸውን የወጣት አካዳሚ ተጫዋቾቹን ኤታን ንዋኔሪን እና ማይልስ ሉዊስ ስኬሊን... read more
ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት ተሾሙ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወትን ከሚያዝያ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ አድረገው ሾመዋል።__
ሀሳብ... read more
በ80 ዓመት አዛውንት እናት ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ በ80 ዓመት አዛውንት ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በ10 ዓመት ፅኑ... read more
አፍሪካዊው የፈጠራ ሰው ከ40 በላይ ቋንቋዎችን በቅጽበት የሚተረጉም የጆሮ ማዳመጫ ፈጠረ
👉የቋንቋ አለመቻል ችግርን ይቀርፋል ተብሏል
ሐምሌ 27 ቀን2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአንድ አፍሪካዊ የፈጠራ ባለሙያ የተሰራው አዲስ የጆሮ ማዳመጫ፣ ከ40 በላይ የሚሆኑ ቋንቋዎችን የበይነመረብ... read more
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የ103 የእሳት ቃጠሎ መንስኤዎችን በፎረንሲክ ምርመራ አጣርቶ ውጤቱን ይፋ አደረገ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2017 ዓ.ም ስድስት ወራት ውስጥ በአዲስ አበባ እና በሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች የደረሱ የ103 የእሳት ቃጠሎ መንስኤዎችን በፎረንሲክ... read more
ምላሽ ይስጡ