መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በትግራይ ቴሌቪዥን (Tigray TV) ላይ ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ እገዳ መጣሉን ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ። ባለሥልጣኑ በመግለጫው እንዳስታወሰው፣ በኢፌዴሪ መንግሥት እና በሕወሓት መካከል በፕሬቶሪያ የተፈፀመውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ባደረገው ውይይትና በተደረሰበት ስምምነት መሠረት ቀደም ሲል በትግራይ ቴሌቪዥን ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነስቶ ወደ ሥራ መመለሱ ይታወቃል። ከዚህም በተጨማሪ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ለትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞችና ባለሙያዎች የሰላም ግንባታና የሙያ ብቃት ማሳደጊያ ሥልጠናዎችን በመስጠት ሚዲያው ወደ ሕገ-መንግሥታዊና ሙያዊ መስመር እንዲመለስ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የትግራይ ቴሌቪዥን በተሰጠው ዕድል ተጠቅሞ እና የሙያ ሥነ-ምግባር አክብሮ አገልግሎት መስጠት ሲገባው፣ የሀገርንና የሕዝብን ደህንነት እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅምን አደጋ ላይ የሚጥሉ፣ ወደ ግጭት የሚገፋፉ እና ፅንፈኝነትን የሚያበረታቱ መልእክቶች በተከታታይ እየተላለፉበት እንደሚገኝ በተደረገው የሚዲያ ይዘት ክትትልና ግምገማ ማረጋገጡን ባለሥልጣኑ ገልጻል። በመሆኑም በሕግ የተጣለበትን ኃላፊነት መሠረት በማድረግ ጣቢያው ላይ ይህንን እገዳ ለመጣል መወሰኑን አስታውቋል። በመጨረሻም ማንኛውም ዲጂታል፣ ብሮድካስትም ሆነ የሕትመት ሚዲያ የትግራይ ቴሌቪዥንን እንደ መረጃ ምንጭ መጠቀም ወይም የቴሌቪዥን ጣቢያው በሕገ-ወጥ መንገድ የሚያሰራጫቸውን ይዘቶች አሰራጭቶ ወይም አስተጋብቶ መገኘት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ባለሥልጣኑ አሳስቧል። ይህንን መመሪያ ተላልፎ በሚገኝ ማንኛውም ሚዲያ ላይ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃዎች የሚወስድ መሆኑን አጥብቆ አሳስቧል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
መርዛማ ብረቶችን በመመገብ ንፁህ ወርቅ የሚያመነጭ ባክቴሪያ ተገኘ
ሐምሌ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ሳይንቲስቶች መርዛማ ብረቶችን ከተመገበ በኋላ ንፁህ ወርቅ የማምረት ችሎታ ያለው ባክቴሪያ መለየታቸውን አስታወቁ። ይህ ግኝት በወርቅ... read more
ኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ከምታደርገው ጥረት ጎን ለጎን በቴክኖሎጂ የታገዘ የንግድ ስርዓት መገንባት እንዳለባት ተገለጸ
ኢትዮጵያ በአለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ከምታደርገው ጥረት ጎን ለጎን በቴክኖሎጂ የታገዘ የንግድ ስርዓት መገንባት እንደሚገባ ለመናኸሪያ ሬዲዮ የገለጹት በንግድና... read more
የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምስል ያረፈበት የ24 ካራት ወርቅ ሳንቲም ሊታተም ነው
መጋቢት 15 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአሜሪካ የነፃነት 250ኛ ዓመት መታሰቢያን አስመልክቶ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምስል ያለበት ባለ 24 ካራት የወርቅ ሳንቲም... read more
ጆዜ ሞሪንሆ የሪያል ማድሪድ ቀጣዩ አሰልጣኝ የመሆን እድላቸው እጅግ ሰፊ መሆኑን Sky Sport አረጋግጧል
ግንቦት 04 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ቡድናቸው ላለፉት ሁለት ዓመታት ያጋጠመው የዋንጫ እጦት በክለቡ ያልተለመደ እና እንግዳ ነገር መሆኑን... read more
በቻይና የፈጠራ ጥበብ የተሰራውና ራሱ ተንቀሳቅሶ አገልግሎት የሚሰጠው አስገራሚው “ሮቦት መጸዳጃ ቤት”
ሰኔ 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በቴክኖሎጂው ዘርፍ ዓለምን እያስደመሙ የሚገኙት የቻይና ሳይንቲስቶች፣ አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞችን ከሰው እጅ ጠባቂነት... read more
ግማሽ ጭንቅላቷን ብታጣም ተስፋ አልቆረጠችም፦ የክሪስቲና ሳንታውስ አስገራሚ የሕይወት ታሪክ
መጋቢት 08 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በስምንት ዓመቷ ሕይወቷን አደጋ ላይ የሚጥልና በቀን እስከ 150 ጊዜ የሚደርስ የሚጥል በሽታ (seizure) ያጋጥማት... read more
በክልሉ አዋሳኝ ቦታዎች የኤም ፖክስ የምርመራ ስራ መጀመሩ ተገለጸ
በክልሉ የሚገኙ ጤና ተቋማት በኤም ፖክስ በሽታ የተጠቁ ሰዎችን አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸው የኦሮሚያ ክልል አስታውቋል፡፡ በኤም ፖክስ 8 ሰዎች... read more
ማኅበራዊ ሚዲያ ተከፍቶላቸው እንዲወያዩ የተደረጉት ሮቦቶች ውይይታቸው በጦርነት ተጠናቀቀ
ነሐሴ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአምስተርዳም ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በቅርቡ ባደረጉት አስገራሚ ጥናት፣ 500 ቻትቦቶችን (AI ሮቦቶችን) ያሳተፈ የማኅበራዊ ሚዲያ ሙከራ... read more
የኦሮሚያ ክልል ሰሞኑን በጅማ ዞን የተከሰተውን ጉዳይ በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል
የካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም በጅማ ዞን ጌራ ወረዳ ውስጥ በኢንቨስትመንት ተሰማርተው ይሰሩ በነበሩት በአቶ ዛኪር አባ ኦሊ ላይ አስደንጋጭ... read more
ስኳር ፋብሪካዎች ከክረምት ጥገና በኋላ መደበኛ ስኳር የማምረት ሥራ መጀመራቸው ተገለጸ
ታኅሳስ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከ2016 ዓ.ም የክረምት ወራት መግባት ጋር ተያይዞ አጠቃላይ የጥገና ሥራ ሲያከናውኑ የቆዩት ስኳር ፋብሪካዎች መደበኛ... read more
ምላሽ ይስጡ