መስከረም 09 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባንኩ ከታክስ በፊት 4.3 ቢሊዮን ብር ትርፍ ሲያስመዘግብ፣ ጠቅላላ ሀብቱም 111.3 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታውቋል። ባንኩ ከዚህ በፊት ባካሄደው 33ኛ መደበኛ እና 16ኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ 4.3 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማድረጉንና ጠቅላላ ገቢው የ21 በመቶ እድገት በማስመዝገብ 16.4 ቢሊዮን ብር መድረሱን ገልጿል፡፡ እ.ኤ.አ. የ2025-26 በጀት ዓመት የአፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዲሹ ሁሴን፣ የባንኩ የሂሳብ ሚዛን እና የካፒታል አቅም እያደገ መምጣቱን እንዲሁም የባንኩን መደበኛ ስራዎች የሚያቀላጥፉ ቴክኖሎጂ መር ፕሮጀክቶች መተግበራቸውን ገልፀዋል:: የቦርድ ሰብሳቢው አክለውም ባንኩ በበጀት ዓመቱ ያጋጠሙትን የተለያዩ ዓለም አቀፋዊ እና ሀገራዊ ተግዳሮቶች በመቋቋም በፋይናንስና ፋይናንስ ነክ ባልሆኑ የአፈፃፀም መለኪያዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቅሰዋል። የባንኩ ጠቅላላ ሀብት ሰኔ 30 ቀን 2026 ዓ.ም. 111.3 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው 84.3 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር የ32 በመቶ ዕድገት ያሳየ መሆኑን አቶ አብዲሹ ገልፀዋል። በተመሳሳይም የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ 81.3 ቢሊዮን ብር መድረሱን ጠቅሰው፣ ይህም ካለፈው በጀት ዓመት 66.2 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር የ23 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡን በመጠቆም ባንኩ በበጀት ዓመቱ ጠንካራ የሀብት ማሰባሰብ እንቅስቃሴ ማድረጉን እንደሚያሳይ ተናግረዋል፡፡ በተያያዘም ባንኩ በበጀት ዓመቱ 366 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሪ ያገኘ መሆኑን የጠቀሱት አቶ አብዲሹ፣ ይህ አፈፃፀም እ.ኤ.አ. ከ2024-25 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ34 በመቶ ዕድገት እንዳለው ገልፀዋል። ባንኩ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የሰጠው ጠቅላላ ብድርም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የ26 በመቶ እድገት በማስመዝገብ 67.3 ቢሊዮን ብር መድረሱን ጠቅሰዋል፡፡ ባንኩ የቀጣይ ዓመታት የአዲሱን የዳይሬክተሮች ቦርድ የሥራ ድርሻ ያስቀመጠ ሲሆን፣ የዲጂታል አሰራርን ማስፋፋት፣ የአሰራር መዋቅርን ማሳደግ፣ እንዲሁም የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓትን መከተልና መተግበር ዋና ዋናዎቹ እንደሆኑ ተመላክቷል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በትግራይ ክልል ያለው የነዳጅ እጥረት የፖሊዮ ክትባትን ተደራሽ ለማድረግ ስጋት መሆኑ ተገለ
በትግራይ ክልል ከየካቲት 14 እስከ 17/2017 ዓ.ም ድረስ ከአምስት አመት በታች ለሆኑ ህፃናት የፖሊዮ ክትባት እንደሚሰጥ የክልሉ ጤና ቢሮ... read more
ከአደጋ ቁጥሮች በስተጀርባ ያሉ ህይወቶች፡ በኢትዮጵያ የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ መዋቅራዊ ለውጥ ለምን ያስፈልጋል?
በየእለቱ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ዜናዎች ላይ “በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰዎች ህይወት አለፈ” የሚሉ መርዶዎችን መስማት የተለመደ የዕለት ተዕለት ክስተት ሆኗል። ነገር... read more
በትምህርት ፍኖተ ካርታው ውስጥ የሀገር በቀል እውቀት ትግበራን ለማከናወን የማስፈጸሚያ ሰነድ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ
ሰኔ 02 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ተግባራዊ በሆነው አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ውስጥ የሀገር በቀል እውቀት ከጽሑፍ ያለፈ ለትግበራ የተዘጋጀ አካሄድ የለም... read more
ወደ ፍጻሜው የደረሰው የጋዛ ተኩስ አቁም ስምምነትና ኔታንያሁ የገጠማቸው የካቢኒያቸው ጫና
https://youtu.be/DTfy1rTwgxI
read more
ወተት ለምን ተወደደ?
👉
https://youtu.be/-Jy9xIQPybo
read more
ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ጉዳይ ከውጪ ሃገራት ጋር የምታደርገውን ግንኙነት በጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ብልሃት መምራት እንደሚገባት ተገለጸ
መጋቢት 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በቀይ ባህር ጂኦ-ፖለቲካዊ ውጥረቱ እየጨመረ በመምጣቱ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሟን ለማስከበር በምትከተለው መርህ የቀጠናው ውስብስብ የፖለቲካ... read more
ኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ከምታደርገው ጥረት ጎን ለጎን በቴክኖሎጂ የታገዘ የንግድ ስርዓት መገንባት እንዳለባት ተገለጸ
ኢትዮጵያ በአለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ከምታደርገው ጥረት ጎን ለጎን በቴክኖሎጂ የታገዘ የንግድ ስርዓት መገንባት እንደሚገባ ለመናኸሪያ ሬዲዮ የገለጹት በንግድና... read more
አፍሪካ በተባበሩት መንግስታ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ሁለት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት እንደሚገባ ተጠየቀ
በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው 38ተኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ አፍሪካ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት እንደሚገባ ተጠይቋል።
የአፍሪካ ህብረት... read more
የቱሪዝም ሚኒስቴር ለ38ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ በሚደረገው ቅድመ ዝግጅት በ15 ሆቴሎች የድንገተኛ ፍተሻ ማድረጉ ተገለጸ
ጥር 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የካቲት 8 እና 9 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለሚካሄደው 38ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ የቱሪዝም... read more
በጋምቤላ ክልል የሙቀት መጠን እየጨመረ በመምጣቱ ከነገ ጀምሮ ለሦስት ወራት የሚቆይ የስራ ሰዓት ለውጥ እንደሚደረግ ታውቋል
በጋምቤላ ክልል የሙቀት መጠን እየጨመረ በመምጣቱ የመንግስት የስራ ሰዓት ከነገ ጀምሮ ለውጥ እንደሚደረግ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት አስታውቋል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር... read more
ምላሽ ይስጡ