መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በየመን ለሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን አስፈላጊው ክትትል እየተደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡ በየመን መንግሥት ኃይሎችና በኢራን በሚደገፉት የሑቲ ታጣቂዎች መካከል እየተካሄደ ባለው ውጊያ በርካታ ዜጎች ከየመን ወደ ጅቡቲ እየተሰደዱ መሆናቸውን የሚወጡ መረጃዎች አመልክተዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ መረጃም በሀገሪቱ ከሚገኙና ከተመዘገቡ ስደተኞች መካከል ትውልደ ኢትዮጵያውያን በርካታ እንደሆኑ ገልጿል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅ፣ የእስያና ፓሲፊክ ሀገራት ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር ደዋኖ ከድር ሚኒስቴሩ በየመን በሥጋት ውስጥ የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በአካባቢው ያለው ሁኔታ አስቸጋሪ ቢሆንም በተቻለ መጠን ለዜጎች ለመድረስ እየተሞከረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተለይም በዜጎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ባሉበት እንዲቆዩና እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ የማድረግ፣ እንዲሁም ድጋፍ እንዲያገኙ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር እየተሠራ መሆኑን አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡ በየመን የሚገኙ የተወሰኑ ነዋሪዎችን በሚኒስቴሩ በኩል እንደሚያገኟቸው የተናገሩት አምባሳደር ደዋኖ፣ ሌሎቹንም ያሉበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡ በየመን እየተካሄደ ባለው ጦርነት በርካታ ዜጎች በቀይ ባሕር በኩል ወደ ጅቡቲ እየገቡ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የ12 ዓመቷ ታዳጊ የፈጠራ ስራ የዓለምን ትኩረት ሳበ፤ ለትምህርት ቤቶች የሚሆን 11.5 ሚሊዮን ዶላር በጀትም አስገኘ
ሚያዚያ 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በትምህርት ቤቶች ውስጥ የአየር ጥራትን ለማሻሻልና የአየር ወለድ ቫይረሶችን ስርጭት ለመቀነስ የሚረዳ ዝቅተኛ ወጪ የሚጠይቅ የአየር... read more
በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እስካሁን 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኝ መተከሉ ተገለጸ
ሐምሌ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አማካኝነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 7ኛ ዙር የክረምት ወራትም በመከናወን... read more
በሰባ ቦሩ ወረዳ በአፈር መደርመስ አደጋ የ8 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል
በጉጂ ዞን ሳባ ቦሩ ወረዳ በባሕላዊ መንገድ ማዕድን በማውጣት ላይ የነበሩ 8 ሰዎች በአፈር መደርመስ አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል፡፡
አደጋው ትናንት... read more
ዴማ ሆፕ ሪል እስቴት ባለ 21 ፎቁን የቦሌ አደይ አበባ 1 ፕሮጀክት በ18 ወራት አጠናቆ አስመረቀ
ዴማ ሆፕ ሪል እስቴት በ18 ወራት አጭር ጊዜ ውስጥ ግንባታውን ያጠናቀቀውንና ሁለተኛ ሳይቱ የሆነውን ባለ 21 ፎቅ የቦሌ አደይ አበባ... read more
ትላንት በምግብ ማብሰያነት ያገለገለው ዘይት የነገ ተሽከርካሪዎችን ነዳጅ ሊሆን እንደሚችል ያውቁ ኖሯል? ከፊንላንድ የተሰማ አስገራሚ የቴክኖሎጂ ስኬት!
ሰኔ 18 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በየቀኑ በቤታችንም ሆነ በተለያዩ ምግብ ቤቶች ውስጥ ለምግብ ማብሰያነት ተጠቅመን የምንደፋው ወይም የምናስወግደው የቆሸሸ... read more
በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስቆም በክልሎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት (NEWA) ያለዕድሜ ጋብቻን፣ የሴት ልጅ ግርዛትን እና ሌሎች ጎጂ... read more
ትራምፕ ቲክቶክ አሜሪካ ውስጥ የተወሰነ ጊዜ ሳይዘጋ እንዲቆይ ማድረግ አስፈላጊ ሊሆን እንደሚችል ገለጹ
ታኅሳስ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የምርጫ ቅስቀሳ በሚያካሂዱበት ወቅት በቲክቶክ በቢሊዮን የሚቆጠር እይታ ማግኘታቸውን የገለጹት ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ... read more
በአዲስ አባባ ከተማ ከህንጻ ተደራሽነት ጋር በተያያዘ ግልጽ የአቤቱታ ማቅረቢያ መድረክ አዘጋጅቶ መፍትሔ እያሰጠ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጸ
በመዲናዋ በህንጻ ተደራሽነት ዙሪያ ግልጽ የአቤቱታ ማቅረቢያ መድረክ ተዘጋጅቶ አካል ጉዳተኞች ለመንግስት አመራሮች ቅሬታቸውን አቅርበው ምላሽ ማግኘታቸውን ኮሚሽኑ ለጣቢያችን አስታውቋል፡፡
ኮሚሽኑ... read more
በጥርስ እና ጸጉር ንቅለ ተከላ ዙሪያ የሚተላለፉ ማስታወቂያዎች ከልክ በላይ የተጋነኑ በመሆኑ ቁጥጥር እና እርምጃ እየተወሰደባቸው ነው ተባለ
ታኅሳስ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የንግድ ውድድሩን ተከትሎ የጤና ተቋማት አማላይ ማስታወቂያዎችን በማስነገር ህብረተሰቡን ወደ ተሳሳተ እይታ እየመሩት ነው ያለው... read more
ስፔን ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ የኃይል ፍጆታዋን ከታዳሽ ኃይል ማግኘቷ ተዘገበ
ሐምሌ 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ስፔን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታዋን ከታዳሽ ኃይል ምንጮች በማግኘት ታሪካዊ ምዕራፍ አስመዘገበች።
ይህ... read more
ምላሽ ይስጡ