መስከረም 05 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከትላንት በስቲያ በኦልድ ትራፎርድ በተደረገው የማንቸስተር ደርቢ ጨዋታ ላይ የማንቸስተር ሲቲውን አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ ያስቆጠራትን ግብ በማጽደቅ “የውሳኔ ስህተት” የፈጸመው የቪኤአር ዳኛ በሚመጣው ሳምንት ከሚደረጉ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ዳኝነት ምደባ ውጪ መደረጉ ተገለጸ። ዘ ኢንዲፔንደንት እንደዘገበው ከሆነ፣ የቪኤአር ዳኛው ማት ዶኑሄ እና ረዳቱ ብሌክ አንትሮበስ በጨዋታው ወቅት ኤንዞ ፈርናንዴዝ በኦፍሳይድ ስፍራ ላይ ሆኖ በጨዋታው እንቅስቃሴ ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩን ሳያገናዝቡ ግቡ እንዲጸድቅ በማድረጋቸው ምክንያት ከሳምንቱ የዳኝነት ስብስብ ውጪ ተደርገዋል። የዳኞች የበላይ አካል (PGMOL) ውሳኔው የዳኝነት ስህተት እንደነበር በማመን ለሁለቱም ዳኞች የቅጣት እርምጃ ወስዷል።
___
ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
ምላሽ ይስጡ