መስከረም 08 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ2019 ዓ.ም የአየር ሁኔታ ትንበያን ተከትሎ የኤልኒኖ ክስተት ሊያስከትላቸው ስለሚችላቸው የዝናብና የሙቀት ለውጦች የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ይፋ አድርጓል። በተለይም በጎርፍ፣ በድርቅ፣ በግብርና ምርት እና በሕዝብ ጤና ላይ ሊከሰቱ ለሚችሉ ተፅዕኖዎች ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅትና የምላሽ ሥራዎች እንዲጠናከሩ በተቋሙ በኩል ባሉት 11 ቅርንጫፍ ማዕከላት በኩል መረጃ የመስጠት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አሳምነው ተሾመ ገልጸዋል። ኢንስቲትዩቱ በክረምቱ ወራት የሰጠው የትንበያ መረጃ 79 በመቶ መከሰቱን ጠቅሰዋል። በዚህም በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ አርሶ አደሮች የአየር ትንበያ መረጃን በመከታተል የዘር ምርጫ፣ የመዝራት ጊዜና የውኃ አጠቃቀም ውሳኔዎችን ከሚገኘው መረጃ ጋር ማስማማት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። በሌላ በኩል ኤልኒኖ በክረምት ሲከሰት እና በበጋ ሲከሰት አሉታዊ እንዲሁም አዎንታዊ ተፅዕኖ ያለው መሆኑን በመጥቀስ፣ ችግሮችን ለመቀነስ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጋራ በመሥራት ላይ እንደሚገኙ አብራርተዋል። የአየር ሁኔታ ትንበያን በወቅቱ መከታተል፣ የሥጋት አካባቢዎችን ቀድሞ መለየትና የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በማጠናከር በኤልኒኖ እና በሌሎችም የአየር ሁኔታ አደጋዎች የሚመጡ ተፅዕኖዎችን ለመቀነስ የሚወጡ መረጃዎችን መከታተል እንደሚገባ ተመላክቷል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የጥንታዊ ኢትዮጵያ ጀግኖች ዓርበኞች ማህበር እየሰራ ባለው የታሪክ ማሰባሰብ ሂደት አንዳንድ ዓርበኞች የሚያውቁትን ታሪክ ለመናገር ፈቃደኛ አለመሆናች ችግር እንደፈጠረበት ተገለጸ
የካቲት ወር የድል በዓላት የሚበዙበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በርካታ ኢትዮጲያዊያን ዓርበኞች የሚዘከሩበት እና ገድላቸው የሚነገርበት መሆኑ የሚታወቅ ነው ። ድል... read more
የመሬት መንቀጥቀጡ ቀጣይነት እያሳየ በመሆኑ በአፋር ክልል የሚገኘው ከሰም ስኳር ፋብሪካ ወደ ምርት እንዳይመለስ አድርጎቷል ተባለ
ጥር 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአፋር ክልል እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ መቀጠሉን ተከትሎ ከሰም ስኳር ፋብሪካ ወደ ምርት መመለስ እንዳይችል... read more
የሕግ ማዕቀፍ የሚሻው የማር ምርት
https://youtu.be/RkEjE2P7sok
read more
በአሜሪካ እና የብሪክስ አባል አገራት መካከል የሚፈጠር ውጥረት እና የንግድ ፉክክር ለአዳጊ ሃገራት የኢኮኖሚ ውድቀት ሊፈጥር ይችላል ተባለ
ኅዳር 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዓለም አቀፉ ገበያ ላይ በበላይነት ያለው የመገበያያ ገንዘብ የሀገራቱን የፖለቲካ ሁኔታ የሚወስን እንደመሆኑ፣ ኢትዮጵያ ከበለጸጉ... read more
እስራኤልና ኢራን ሶስተኛ ቀናቸውን ቀጥለውበታል
እስራኤል እና ኢራን ለሶስተኛ ተከታታይ ቀን ጥቃቶችን እየተለዋወጡ ሲሆን፣ ሁለቱም ሀገራት ለአጥቂነት ምላሽ መስጠታቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። ይህ ውጥረት ከዚህ ቀደም... read more
ሰሜን ኮሪያ የአሜሪካና ደቡብ ኮሪያን ወታደራዊ ልምምድ በመቃወም ለሁለተኛ ጊዜ የክሩዝ ሚሳኤል ሙከራ አደረገች
መጋቢት 09 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ታዳጊ ልጃቸውን ኪም ጁ ኤን በማስከተል በሀገሪቱ ስልታዊ የክሩዝ... read more
በአማራ ክልል የሚገኙ አርሶ አደሮች ማዳበሪያ እንዳንወስድ ተከልክለናል አሉ
የግብርና ሚኒስቴር በበኩሉ ለአማራ ክልል የሚያስፈልገዉን የማዳበሪያ መጠን መላኩን አስታዉቋል፡፡
በአማራ ክልል ያሉ አርሶ አደሮች ለመናኸሪያ ሬዲዮ ባሰሙት ቅሬታ፤ መጪው የበልግ... read more
ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት ተሾሙ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወትን ከሚያዝያ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ አድረገው ሾመዋል።__
ሀሳብ... read more
3 ሺህ 285 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 3 ሺህ 285 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡
በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 9 ዙር በረራ የተመለሱት 2747... read more
በሃይል ላይ የተመሰረተ አሸናፊነት ህዝብንም ሃገርንም ስለማይጠቅም ልዩነቶችን በውይይት መፍታት እንደሚገባ ፓርቲዎች ገለጹ
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በሃገር ጉዳይ ላይ ያገባናል የሚል ዜጋ ሁሉ በቅድሚያ የሃገርን ሰላም ማስጠበቅና የመልካም አስተዳደር... read more
ምላሽ ይስጡ