መስከረም 08 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከሃምሳ ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ይሳተፉበታል ተብሎ የሚጠበቀው ሁለተኛው ታላቁ የኢሬቻ ሩጫ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ እንደሚካሄድ የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታውቋል። የኦሮሚያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሮዛ ቢያ ለውድድሩ አሸናፊዎች ከፍተኛ የሆነ ሽልማት መዘጋጀቱን በመግለጽ፣ በዚህም በሁለቱም ጾታዎች ለአንደኛ ለወጡት አንድ አንድ ሚሊዮን ብር፣ ለሁለተኛ ሰባት መቶ ሺህ፣ ለሦስተኛ አምስት መቶ ሺህ እያለ እስከ ስድስተኛ ለሚወጡት ሽልማት እንደተዘጋጀላቸው ገልጸዋል። ውድድሩ አስር ኪሎሜትሮችን የሚሸፍን ሲሆን፣ የዲባባ ቤተሰቦች የዚህ ዓመት የውድድሩ ብራንድ አምባሳደሮች መሆናቸውን አስረድተዋል። በዚህ ዓመትም ኢሬቻን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ብቸኛው ውድድር መሆኑን በመግለጽ፣ የተወዳዳሪዎች የምዝገባ ቦታዎች በአዲስ አበባ፣ በአዳማ እና በቢሾፍቱ ከተሞች እንደሚካሄዱ ተናግረዋል። የኦሮሞ አባገዳዎች ኅብረት ዋና ጸሐፊ አባገዳ ጌቱ ተሊላ ሁሉም በአንድነት ሩጫው ላይ እንዲሳተፉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ በበኩላቸው ሩጫውን ጨምሮ ለኢሬቻ ክብረ በዓል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። የመጀመሪያው ታላቁ የኢሬቻ ሩጫ በ2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወሳል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፉ ምግብና መጠጦችን እንዳስወገደ የአዲስ አበባ ምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ
ኅዳር 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በመዲናዋ 6 ሚሊየን 44ሺህ 402 ብር የሚያወጣ ግምት ያላቸው የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፉ ምግብና መጠጦች ናቸው... read more
የአሜሪካው ኤፍ-15 ጄት በኢራን ሰማይ ላይ ከመውደቁ በፊት ያጋጠመው አስገራሚ ክስተት፤ “የጄሊፊሽ ቅርጽ ያላቸው ድሮኖች ከበቡን”
ሰኔ 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በቅርቡ በኢራን የአየር ክልል ውስጥ የተመታው የአሜሪካ አየር ኃይል ኤፍ-15 ኢ ስትራይክ ኢግል ተዋጊ ጄት ፓይለት... read more
የብሪክስ ልማት ባንክ ኢትዮጵያ ከአዳዲስ የገንዘብ ምንጮች ተጠቃሚ እንድትሆን እና በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተሳትፎ ለማሳደግ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው ተገለጸ
ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል አገራት ልማት ባንክ (New Development Bank) አባል ለመሆን በይፋ ጥያቄ ማቅረቧ ተገልጿል። ጥያቄው ተቀባይነት ካገኘ ኢትዮጵያ ለተለያዩ... read more
የሰው ሠራሽ አስተውሎት ከመስፋፋቱ አስቀድሞ፣ ቴክኖሎጂውን የሚመራውን የሰው ሃይል ዝግጁነት መጠየቅ ይገባል ተባለ
ነሐሴ 28 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በፋይናንስ ዘርፍ የቴክኖሎጂ ለውጥና የሰው ኃይል ዝግጁነትን በሚመለከተው FinHuman 2026 መድረክ፣ የወደፊቱን የሥራ ዓለም ለመምራት... read more
የውጭ ባንኮች ከሀገር ውስጥ ባንኮች ጋር በጥምረት የሚሰሩበት አማራጭ ሊዘረጋ ይገባል ተባለ
ታኅሳስ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከሰሞኑ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 11ኛ መደበኛ ስብሰባው የውጭ ባንኮች ሀገር ውስጥ ገብተው እንዲሰሩ... read more
ከአሜሪካ ምዕራብ ወደ ምሥራቅ የሚያሻግረው ታሪካዊ የባቡር ጉዞ
ሕዳር 15 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአሜሪካን አህጉር ከምዕራብ ዳርቻ (ፓሲፊክ ውቅያኖስ) ወደ ምሥራቅ ዳርቻ (አትላንቲክ ውቅያኖስ) የሚያገናኘው አስደናቂ የባቡር ጉዞ ርዝመትና... read more
በትግራይ ክልል በተካሄደው የ8ተኛ ክልል አቀፍ ፈተና ይሳተፋሉ ተብሎ ከተጠበቀው 50 በመቶ የሚሆኑት አለመሳተፋቸው ተገለጸ
ታኅሳስ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል በጦርነት ምክንያት ተማሪዎች በመደበኛ የትምህርት ሰዓት እየተማሩ አለመሆኑ እና የፈተና ሰዓትም ጠብቀዉ እየተፈተኑ... read more
የአፍሪካ መሪዎች አዲሱን ዓመት በሰላም እና አንድነት እንዲያሳልፉ ጥሪ ቀረበ
ታኅሳስ 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የሳህል ቀጠና እና የምስራቅ አፍሪካ መሪዎች ለሰላም እና መረጋጋት አፅንኦት እንዲሰጡ የኬንያው ፕሬዝዳንት ጠይቀዋል፡፡
የአፍሪካ መሪዎች አዲሱን... read more
በሰዓት 400 ቶን የታጠበ የድንጋይ ከሰል ማምረት የሚችለው “ዮ ሆልዲንግ” በዓመቱ መጨረሻ ምርቱን ወደ ውጭ ለመላክ ማቀዱን አስታወቀ።
መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል "ቦረዳ ወረዳ" የድንጋይ ከሰል ማምረትና ማጠብ ሥራ ላይ የተሰማራው ዮ... read more
የተሻሻለው የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ደንብ ላይ የተደረገው የአገልግሎት ክፍያ ወሰን ጭማሪ የተጋነነ ነው ሲሉ የህግ ባለሙያዎች ተናገሩ
ኅዳር 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የወጣው ረቂቅ ደንብ የክፍያ ወሰን ጭማሪ ከሰሞኑን ለህዝብ ተወካዮች... read more
ምላሽ ይስጡ