መስከረም 08 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) በትግራይ ክልልም ምርጫውን ለማከናወን አመቺ ሁኔታዎች ከተፈጠሩ ወዲያው ወደ ዝግጅት ምዕራፍ ለመግባት መዘጋጀታቸውንም ቦርዱ ገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ባልተካሄደባቸው በአማራ ክልል 8 የምርጫ ክልሎችን ጨምሮ፣ ከትግራይ ክልል ውጪ ባሉት ምርጫው ባልተካሄደባቸውና ድጋሜ በሚካሄድባቸው ቦታዎች ለማከናወን የሚያስችል የጊዜ ሰሌዳ እየተዘጋጀ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተክልቲ ይመሰል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ኅብረት ባዘጋጀው መድረክ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፣ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከነ ጉድለቶቹም ቢሆን ስኬታማ ነበር ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ በአማራ ክልል 8 የምርጫ ክልሎችን ጨምሮ ምርጫው ባልተካሄደባቸውና ዳግም በሚካሄድባቸው ቦታዎች ምርጫ ለማድረግ የጊዜ ሰሌዳ እየተዘጋጀ መሆኑን በመግለጽ፣ በትግራይ ክልልም ቢሆን አመቺ ሁኔታዎች ከተፈጠሩ ወዲያው ቦርዱ ወደ ዝግጅት ምዕራፍ እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡ ቀሪ እና በድጋሚ የሚካሄደው ምርጫ ውጤታማ እንዲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማኅበራትና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ከወዲሁ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል፡፡
___
ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
ምላሽ ይስጡ