ሰኔ 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ፥ የቀድሞዋን የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን በምስራቅ አፍሪካ እና በአፍሪካ ቀንድ ቀጠናዊ ተፅዕኖን እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን በበላይነት የማጠናከር እና የማስተካከል ትልቅ ኃላፊነት እንደሰጧቸው ተሰማ። ይህ የተሰጣቸው አዲስ ተልዕኮ በቀጠናው እየታዩ ያሉ የጸጥታ እና የዲፕሎማሲ መሻከር አዝማሚያዎችን በታዋቂ እና አንጋፋ ዲፕሎማቶች አማካኝነት ለመፍታት ከተያዘው የድርጅቱ ስትራቴጂ ጋር የተያያዘ መሆኑ ታውቋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የውስጥ ምንጮች እንደገለጹት፣ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ በቀጠናው ባላቸው የረጅም ጊዜ የዲፕሎማሲ ልምድ፣ በተለይም ቀደም ሲል በጅቡቲ፣ በሴኔጋል እና በፈረንሳይ አምባሳደር እንዲሁም በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (IGAD) እና በአፍሪካ ህብረት የዩኤን ልዩ መልዕክተኛ ሆነው በከፍተኛ የኃላፊነት ደረጃ የሰሩ በመሆናቸው ለዚህ ታላቅ ቀጠናዊ ሚና ተመራጭ አድርጓቸዋል።
ዋና ፀሐፊው አንቶኒዮ ጉተሬዝ ይህንን ውሳኔ ያሳለፉት በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለውን የፖለቲካ ውጥረት ለማርገብ፣ በሀገራት መካከል ያለውን ትብብር መልሶ ለመገንባት እና የድርጅቱን ቀጠናዊ ተሰሚነት ከፍ ለማድረግ ታስቦ መሆኑ ተጠቁሟል። ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴም በቅርቡ የስልጣን ዘመናቸውን ካጠናቀቁ በኋላ በተለያዩ አህጉራዊ የግጭት አፈታት እና የሰላም ግንባታ ውይይቶች ላይ በንቃት እየተሳተፉ መቆየታቸው ይታወሳል።
ይህ ሹመት ዩኤን ለአፍሪካ ቀንድ ቀውስ ዘላቂ መፍትሄ ለመፈለግ በወሰደው ስልታዊ እርምጃ ውስጥ ትልቅ ግምት የተሰጠው ሲሆን፥ አዳዲስ ዝርዝር መረጃዎችን እና የሹመቱን ሙሉ ይዘት እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ 1.5 ሚሊየን የሚጠጉ ጎብኚዎች ወደ ላሊበላ ከተማ ያቀናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገለጸ
ታኅሳስ 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዚህ ባለንበት ወርሃ ታህሳስ መጨረሻ ላይ የሚከበረዉን የገና በዓል በስፋት ከሚከበርባቸው ቦታዎች መካከል አንዱ የላሊበላ... read more
ደረጃ የወጣላቸው ምርቶች ብሔራዊ የደረጃ ምልክት መጠቀም እንዳለባቸው ተገለጸ
አስገዳጅ ደረጃ የወጣላቸው ሁሉም ምርቶች ብሔራዊ የደረጃ ምልክት መጠቀም እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡
የኢንስቲትዩቱ የሕዝብ ግንኙነት ስራ አስፈጻሚ ብሩክ ሀብቴ... read more
‘‘በደብረጽዮን የሚመራው ህወሓት ከኤርትራ መንግስት ጋር እየሰራ ነው’’ – ጊዜያዊ አስተዳደሩ
የጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራር ከሆኑት ከአቶ #ጣዕመ #አረዶም ጋር የተደረገ ቆይታ
https://youtu.be/F1ilWPpFztU
read more
አውስትራሊያ ለአሜሪካው ጥሪ “አይሆንም” አለች
መጋቢት 08 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአንቶኒ አልባኒዝ የሚመራው የአውስትራሊያ መንግስት በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን የነዳጅ መስመር ደህንነት ለመጠበቅ አሜሪካ ላቀረበችው ጥሪ “መርከብ... read more
የፌዴራል መንግሥት ባስፈለገ እና በተገደበ ሁኔታ በክልሎች ጣልቃ እንዲገባ የሚያስችለው አዋጅ መጽደቁ የዜጎችን ሰላምና ደህንነትን ለማረጋግጥ ያግዛል ተባለ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 22ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ የወጣ የማሻሻያ አዋጅን መርምሮ አጽድቋል፡፡
የአዋጁ... read more
የካቲት 12 ሆስፒታልን ወደ ዩኒቨርሲቲነት ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የባለሙያ እጥረት ተግዳሮት መፍጠሩ ተገለጸ
በርካታ የጤና ባለሙያዎችን በማፍራት 102 ዓመታትን ያስቆጠረው የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2016 ዓ.ም ባስቀመጠው የ10 አመት የስትራቴጂ ዕቅድ ኮሌጁን... read more
የቻይናው ግዙፍ የኒውክሌር ጦር መርከብ ሚስጥር ይፋ ሆነ፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተገነባው ባለ 286 ሜትር የጦር መርከብ ሳተላይቶችን አስደንግጧል
ግንቦት 20 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዓለምን የኃይል ሚዛን ሊቀይር ይችላል የተባለውና በከፍተኛ ሚስጥር ሲገነባ የቆየው የቻይናው አዲሱ የጦር መርከብ (Type... read more
ለእንቁላል ዋጋ መጨመር የመኖ ምርት የሚመጣባቸዉ አካባቢዎች የጸጥታ ችግር ዋነኛ ምክንያት ነዉ ተባለ
በመዲናዋ የእንቁላል ዋጋ ከ17 እስከ 20 ብር ድረስ እየተሸጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ዋጋዉ እየተጋነነ መምጣቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ የዶሮ አርቢዎች እና አቀናባሪዎች... read more
የአድዋ ገድልን በዲፕሎማሲያዊው መስክ መጠቀም እንደሚገባ ተገለጸ
ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ ያላት እውቅና የጨመረው እና የአውሮፓ ሀያላን ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር በእኩልነት መንፈስ መደራደራቸውን የቀጠሉት ከአድዋ ማግስት መሆኑ... read more
አዲስ የተመረጡም ሆኑ ነባር የሕዝብ እንደራሴዎች የሕዝቡን ጥያቄ በሚገባ ማንጸባረቅ እንዳለባቸው ተገለጸ
መስከረም 08 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) 7ኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ማሸነፉን ተከትሎ ብልጽግና ፓርቲ በያዝነው ወር መጨረሻ አዲስ መንግሥት እንደሚመሰርት ይታወቃል።... read more
ምላሽ ይስጡ