መስከረም 08 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የማንቸስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ እሁድ ዕለት በኦልድ ትራፎርድ ማንቸስተር ዩናይትድን 1-0 ባሸነፉበት የደርቢ ጨዋታ ላይ በኤርሊንግ ሀላንድ ብቸኛ ጎል ታግዘው 199ኛውን የማንቹሪያን ደርቢ በድል መወጣታቸው የሚታወስ ነው። ታዲያ በጎሉ ዙሪያ የተነሳውን የVAR ውዝግብ አስመልክተው የሰጡት ምላሽ የእግር ኳስ አፍቃሪዎችን ትኩረት ስቧል። የዳኞች የበላይ አካል PGMOL በጨዋታው ወቅት የVAR ዳኞች ኤንዞ ፈርናንዴዝ በኦፍሳይድ ስፍራ ሆኖ እንቅስቃሴ በማድረጉ የሀላንድ ግብ መሻር ነበረበት በማለት ለዩናይትድ ይቅርታ መጠየቃቸውን ተከትሎ፣ ማሬስካ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ጠንካራ አስተያየት ሰጥተዋል። ማሬስካ በ2023 በኦልድ ትራፎርድ ሲቲ 2-1 በተረታበት ጨዋታ ማርከስ ራሽፎርድ በግልጽ ኦፍሳይድ ላይ ሆኖ ኳሱን ሳይነካ በመሮጡ የብሩኖ ፈርናንዴዝ ግብ መጽደቁን በማስታወስ ነው “እኛም ከሶስት ዓመት በፊት ለተቆጠረብን መደበኛ ያልሆነ ግብ እስከዛሬ የPGMOLን ይቅርታ እየጠበቅን ነው” ሲሉ ምላሽ የሰጡት ኤንዞ ማሬስካ በጊዜው አሰልጣኝየነበሩት የአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ምክትል በመሆን ይሰራ እንደነበር ይታወቃል። በተጨማሪም ማሬስካ ቡድናቸው ፊል ፎደን በ23ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከወጣበት በኋላ ለ70 ደቂቃዎች ያህል በ10 ተጫዋች ተከላክሎ እና ተፋልሞ ያመጣውን አስደናቂ ድል ትቶ፣ ትኩረቱን በሙሉ በአንድ የVAR ውሳኔ ላይ ማድረግ “ደካማ አመለካከት” ነው ሲሉ ተናግረዋል። በኳስ ጨዋታ የውሳኔ ስህተቶች አንዳንዴ ወደ አንተ አንዳንዴ ደግሞ በተቃራኒ ቡድን ጸጋ ይዘው ሊመጡ እንደሚችሉና ዳኞች በሰከንዶች ውስጥ ውሳኔ መስጠት ስላለባቸው ስህተት ተፈጥሯዊ መሆኑን አክለው ገልጸዋል። ማንቸስተር ሲቲ አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካን የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ከሾመ በኋላ በዚህ የውድድር ዘመን አስደናቂ ጅማሮን በማሳየት ሁሉንም ጨዋታዎች በድል በመወጣት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን በጎል ክፍያ እየመራ ይገኛል። የማንቸስተር ሲቲው አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ አያይዘው በኮሚኒቲ ሺልድ ጨዋታ ወቅት ባጋጠመው የባት ጉዳት ምክንያት ከሜዳ ርቆ የቆየው የ24 ዓመቱ ቤልጂየማዊ የክንፍ አጥቂ ዠሬሚ ዶኩ (Jeremy Doku) ወደ ሙሉ አካላዊ ብቃት ተመልሶ ለጨዋታ ዝግጁ ለመሆን በጣም መቃረቡን ተናግረዋል። አሰልጣኝ ማሬስካ ስለ ተጫዋቹ አጠቃላይ ሁኔታ ሲናገሩ “ዶኩ ወደ ስብስቡ ለመመለስ በጣም ተቃርቧል፤ በዚህም ደስተኞች ነን፤ ተጫዋቹ ለቡድናችን ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያለው ተጫዋች ነው” ሲሉ ገልጸውታል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ስንብትን አልፈራም ሲል ፔፕ ጋርዲዮላ ሀሳቡን ሰጥቷል
ከዛሬው ተጠባቂ የሻምፒዮንስ ሊግ የknock out Play-off ጨዋታዎች በፊት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በሰጠው የቅድመ ጨዋታ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የትኛው ማንቸስተር... read more
ጆአዎ ፔድሮ በጉዳት ምክንያት ከብራዚል ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውጪ እንደሚደረግ እና ጥሪ እንደማይደርሰው ተሰምቷል
መስከረም 08 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ አጥቂ የሆነው ጆአዎ ፔድሮ ባጋጠመው የጉዳት ህመም ምክንያት ከመጪው ዓለም አቀፍ... read more
በክለቦች ትልቁ የውድድር መድረክ በሆነው በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ቀሪ ጨዋታ ዛሬ ምሽት በኢንተርሚላን እና ባርሴሎና መካከል ይከናወናል
👉ሁለቱ ቡድኖች የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን ካሳኩ 10 አመት እና ከዛ በላይ ያስቆጠሩ ቡድኖች ናቸው።
የ2010 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን በልዩው ሰው The... read more
ራፊኛ እስከ 2030 ከባርሴሎና ጋር የሚያቆየውን ውል ማደሱ ተሰምቷል
መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) ዘንድሮ እጅግ በጣም አስደናቂ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኘው የብሉግራናዎቹ አምበል እና የፊት መስመር ተጫዋች... read more
ሩበን አሞሪም ቋሚ 11 ቡድኔን ልመርጥ በጣም ትንሽ ነው የሚቀረኝ ሲሉ ተደምጠዋል
ኅዳር 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) አዲሱ የ39 አመቱ ፖርቹጋላዊ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ዩናይትድን በአሰልጣኝነት ከተረከበ በኋላ በፕሪሚየር ሊጉ 1 ጨዋታ... read more
የሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ዳሰሳ
በየአመቱ ከሚከናወኑ እና የክለቦች ፉክክር ከሚደምቅበት እንዲሁም በአውሮፓ ውስጥ ሀያሉ ክለብ ለመባል የሚደረግ የክለቦች ትንቅንቅ በተለያዩ የአውሮፓ ግዙፍ ስቴዲየሞች በባውዛ... read more
ማንቸስተር ሲቲዎች ኢሊማን ንዲያዬን ለማስፈረም ጥረት እያደረጉ መሆኑ ተገለጸ
ነሐሴ 23 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ማንቸስተር ሲቲዎች የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት የኤቨርተኑን ኢሊማን ንዲያዬን ለማስፈረም ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ጋዜጠኛ ቤን... read more
አርሰናል በሪዮ ንጎሞሀ ላይ የቅርብ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ የሚጠቁሙ መረጃዎች ወጥተዋል
መስከረም 05 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቲምቶክ ጸሐፊ ጋዜጠኛ አለን ኒክሰን እንዲሁም ሪለክተንት ኒኮ ያወጡት መረጃ፣ መድፈኞቹ ይህንን ተስፈኛ ወጣት ኮከብ... read more
የሴቶች ማራቶን ሪከርድ ባለቤቷ ኬንያዊቷ ሩት ጄፒንጌች በጊዜያዊነት መታገዷ ተሰምቷል
ሐምሌ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኬንያዊቷ የረጅም ርቀት ሯጭ የሆነችው ሩት ጄፒንጌች በአለም አትሌቲክ ኢንቴግሪቲ ዩኒት ወይም የአለም አትሌቲክስ የውድድር... read more
የአርሰናል የተከላይ መስመር ተጫዋች የሆነው ዩሪየን ቲምበር ጉልበቱ ላይ የቀዶ ጥገና እንደሚያከናውን ተገልጿል
ተያይዞም ሌላው የመሀል ተከላካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነው ዊሊያም ሳሊባ በበኩሉ ተጨማሪ ምርመራዎች እንደሚደረጉለት ክለቡ አሳውቋል።
ዩሪየን ቲምበር ያለፉትን ወራቶች ከነጉዳቱ ሲጫወት... read more
ምላሽ ይስጡ