ነሐሴ 08 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በማዕከላዊ እና በደቡብ አሜሪካ በሚገኙ ጥቅጥቅ ያሉ ደኖች ውስጥ የሚኖረውና «የዲያብሎስ ወፍ» በመባል የሚታወቀው የስትጂያን ጉጉት፣ በአስፈሪው ገጽታውና በሌሊት በሚያንፀባርቁት ቀያይ ዓይኖቹ በብዙ አገራት ባህላዊ ታሪኮች ውስጥ የመጥፎ እድልና የጨለማ መንፈስ ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል።
ጉጉቱ ጥቁር የመሰለ ላባ፣ በራሱ ላይ እንደ ቀንድ የሚወጡ ረጅም ላባዎች እንዲሁም አደገኛ እይታ ስላለው በተለያዩ የገጠር አከባቢዎች ከመጥፎ አጋንንታዊ ነገሮች ጋር ተያይዞ ሲነሳ ኖሯል። አዳኝነቱና በሌሊት ብቻ መንቀሳቀሱም ለባህላዊ ፍርሃቱ ተጨማሪ ምክንያት ሆኗል።
በቀን ብርሃን የጉጉቱ ዓይኖች ብርቱካናማ ወይም ቢጫ ቀለም ያላቸው ሲሆኑ፣ በሌሊት በሚነሱ ፎቶዎች ላይ የሚያንፀባርቁት አስፈሪው ቀይ ብርሃን ግን የካሜራ ፍላሽ ወይም ሰው ሠራሽ ብርሃን በዓይኖቹ የኋላ ክፍል በሚገኙት የደም ስሮች ላይ በማረፍ ተመልሶ በመንፀባረቁ ምክንያት የሚፈጠር ተፈጥሯዊ ክስተት ነው።
ምንም እንኳን በአካባቢው ህዝብ ዘንድ «የዲያብሎስ ወፍ» የሚል አስፈሪ ስም ቢሰጠውም፣ ይህ ጉጉት ለተፈጥሮ ሥነ-ምህዳር መዛባት ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ፍጡር ነው ተብሏል። በሌሊት የሚበሩ የሌሊት ወፎችን፣ ትናንሽ አእዋፋትንና አይጦችን በማደን የአካባቢውን ተፈጥሯዊ ሚዛን የመጠበቅ ታላቅ ድርሻ ይወጣል ነው የተባለው።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ