መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል የሴት ልጅ ግርዛትን በተመለከተ የተጣለው የወንጀል ቅጣት እጅግ አነስተኛ በመሆኑ እንዲሻሻል የህግ ማሻሻያ ጥናት ለፍትህ ሚኒስቴር መቅረቡ ተገልጿል። በወንጀል ህጉ የተቀመጠው የሴት ልጅ ግርዛት ቅጣት የሦስት ወራት እስራት እና የ500 ብር የገንዘብ መቀጮ ብቻ መሆኑን በመጥቀስ፣ ይህ የድርጊቱን ፈጻሚዎች የሚያስተምር እና መጣኝ ባለመሆኑ ጥናቶችን በማድረግ ህጉ እንዲሻሻል ለፍትህ ሚኒስቴር መላኩን በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች መብት ጥበቃና ምላሽ መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ አለሙ ወርቁ ተናግረዋል። ጉድለት ያለባቸውን ህጎች የመለየቱ ሥራ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጨምሮ ፍትህ ሚኒስቴር፣ ጤና ሚኒስቴር እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት የተሳተፉበት መሆኑን ጠቅሰዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከህግ ማሻሻያ ባለፈ በግል በዚህ ጉዳይ ላይ ከሚሰሩ የተለያዩ ማህበራት ጋር በጋራ በመስራቱ አሁን ላይ ለሚታዩ መሻሻሎች ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አብራርተዋል። ችግሩ እጅግ አሳሳቢ በመሆኑ በመንግስትም ሆነ በግል በሚንቀሳቀሱ ማህበራት በኩል የሚሰሩ ሥራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተመልከቷል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ቻይና እና ኢትዮጵያን በህክምና ዘርፉ በጥልቀት ማገናኘት የሚቻልበት መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው
ነሐሴ 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በመርሀ ግብሩ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው አካላት የተገኙ ሲሆን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ፤ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ... read more
ከምንጊዜውም በላይ ሰላምን ለማጽናት የጋራ ትብብር እንደሚያስፈልግ ተገለጸ
ህዳር 01 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ሕይወት የሚቀጥፍ፣ ብዙሃኑን ለመፈናቀልና ለጥቃት የሚዳርገውን ጦርነት ማስቆም የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን... read more
የወረቀት ተረፈ ምርቶችን በድጋሚ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ እየተሰራ ነው ተባለ
በተለያዩ አጋጣሚዎች ጥቅም የላቸውም ተብሎ የሚጣሉ ወረቀት እና ካርቶኖችን ለስራ እድል ፈጠራ እንዲውሉ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አንዲ ማማ ድርጅት አስታውቋል።... read more
ዘመናዊ የመንገድ ደህንነት ባለመኖሩ አካል ጉዳተኞች ለትራፊክ አደጋ እየተጋለጡ ነው ተባለ
ሰኔ 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የክልል ከተሞች ዘመናዊ የመንገድ ግንባታ እየተሰራ ቢሆንም፣ አካል ጉዳተኞችን ያማከለ አለመሆኑን... read more
ሞሀመድ ሳላህ ዘንድሮ ከሻምፒዮንስ ሊጉ ይበልጥ ፕሪሚየር ሊጉን ማሳካት እፈልጋለሁ ሲል ሀሳቡን ሰጥቷል
ታኅሳስ 26 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ግብፃዊው ኮኮብ ፍርኦኑ ሞ ሳላህ ዘንድሮ አይቀመሴ አቋም ላይ ነው የሚገኘው። በወርሀ ታኅሳስ ብቻ በ7... read more
ስደት ወይስ ፍልሰት? ከቃላት አጠቃቀም በላይ የሆነው የሰብአዊ መብት ልዩነት
መጋቢት 09 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (IOM Ethiopia) በሀገራችን ያለውን የሰዎች እንቅስቃሴ በተመለከተ በሚያወጣቸው ወቅታዊ ሪፖርቶች ላይ... read more
የጣሪያ ግድግዳ/ንብረት ግብር ተብሎ የወጣውን መመሪያ ክስ በተመለከተ የፍርድ አፈጻጸም ፋይል ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን እናት ፓርቲ አስታወቀ
የንብረት ግብር ማስተባበሪያ ጊዜያዊ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አጥንቶ ያቀረበው በአዲስ አበባ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ አማካኝነት ሚያዝያ 3ቀን 2015 ዓም በተፃፈ ደብዳቤ... read more
በዝናብ ወቅት የሚከሰት የዶሮ በሽታን ለመከላከል መንግስት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ
ነሐሴ 12 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የዝናብ ወቅት ለዶሮ በሽታ አምጪ ተህዋስያን መራባትና መስፋፋት አመቺ በመሆኑ፣ መንግስት የባለሙያ ድጋፍና የግንዛቤ ማስጨበጫ... read more
ለጋዜጠኞች የሙያ ማረጋገጫ እውቅና አልሰጥም – የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን
መጋቢት 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት፤ ለጋዜጠኞች የሙያ ማረጋገጫ ለመስጠት እና የጋዜጠኞች ምዝገባ ለማከናወን ውይይት እና እንቅስቃሴ... read more
በግድያ ወንጀል እና ከባድ በሰው አካል ላይ ጉዳት ማድረስ ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተቀጣ
ተከሳሽ በፍቃዱ ተሰማ በጋምቤላ ክልል በማጃንግ ብሔረሰብ ዞን በጎደሬ ወረዳ ካቦ ቀበሌ ውስጥ በቀን 22/4/2015 ዓ/ም ከምሽቱ 1 ሰዓት አካባቢ... read more
ምላሽ ይስጡ