መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት (NEWA) ያለዕድሜ ጋብቻን፣ የሴት ልጅ ግርዛትን እና ሌሎች ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስቆም በማህበረሰብ ደረጃ ግንዛቤ የማስጨበጥና የንቅናቄ ሥራዎችን በስፋት እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ በሴቶችና በወጣቶች የሚመሩ የማህበረሰብ አደረጃጀቶችን አቅም በማጎልበት፣ ሴቶችን እና ወጣቶችን በጎጂ ልማዶች ላይ በሚደረገው ንቅናቄ በማሳተፍ እና የማህበረሰብ መዋቅሮችን በማጠናከር በተለያዩ ክልሎች ሲሰሩ መቆየታቸውን የቅንጅቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳባ ገ/መድህን ገልፀዋል ። በተጨማሪም የሃይማኖትና የባህል መሪዎችን፣ ወንዶችንና ወጣቶችን በማሳተፍ የማህበረሰብ አመለካከትና ልማድ እንዲቀየር የሚያግዙ ሥራዎች እያከናወኑ መሆኑን አብራርተዋል። የሴቶች ያለዕድሜ ጋብቻና ግርዛትን በተመለከተ በሀገር አቀፍ ደረጃ መሻሻሎች ቢኖሩም፣ በአንዳንድ ክልሎች ግን ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ወ/ሮ ሳባ ጠቅሰዋል ። ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን የ2030ን ግብ ለማሳካት እና የሴት ልጅ ግርዛት እንዲሁም ሌሎች ጎጂ ልማዶችን ለማስቆም፣ በያለዕድሜ ጋብቻ ላይ 19 እጥፍ፣ እንዲሁም በግርዛት ላይ 24 እጥፍ ጨምሮ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
ምላሽ ይስጡ