መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) ከዛሬ ከመስከረም 15/2019 ጀምሮ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌት በአዲስ አበባ ከተማ ማሽከርከር እንደተከለከለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ገለጸ። አንዳንድ ወንጀል ፈጻሚዎች ሞተር ብስክሌትን በመጠቀም የቅሚያ እና የስርቆት ወንጀል ሲፈጽሙ ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን መምሪያው ገልጻል። ወንጀል ፈጻሚዎች ከቦታ ቦታ ለመዘዋወር እና የተሰረቁ እቃዎችን ለማጓጓዝ ሞተር ብስክሌትን በብዛት እንደሚጠቀሙ ፖሊስ አስታውቋል። ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የትራፊክ ደንቡን እንደማያከብሩ በተለይ ቀይ መብራትን መጣስ፣ ሌሎች ተሽከርካሪዎችን በመግጨት ማምለጥ፣ ሄልሜት ሳያደርጉ ማሽከርከር፣ የተፋፋቀ እና ለእይታ አስቸጋሪ የሆኑ የሠሌዳ ቁጥሮችን መጠቀም በአሽከርካሪዎቹ በስፋት የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶች መሆናቸውን የፖሊስ መረጃ አመላክቷል። ወንጀልን ለመከላከል እና በሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የሚፈጸምን የደንብ ጥሰት ለመቆጣጠር ከዛሬ ከመስከረም 15/2019 ዓ/ም ጀምሮ ከኮድ 4 እና ከፖሊስ ሞተር ብስክሌት ውጭ በአዲስ አበባ ከተማ ባለ ሁለት እግር ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር መከልከሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል። የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች እና ባለ ንብረቶች ህጉን እንዲያከብሩ ያሳሰበው ፖሊስ ማሳሳቢያውን በሚተላለፉት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጻል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በመካከለኛው ምስራቅ የጦርነት ድባብ፤ አሜሪካ ታዋቂ የሆኑትን “ኤ-10 ዋርትሆግ” የጦር አውሮፕላኖቿን ቁጥር በእጥፍ አሳደገች
መጋቢት 24 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በመካከለኛው ምስራቅ እየጨመረ የመጣውን ወታደራዊ ውጥረት ተከትሎ፣ አሜሪካ በየብስ ውጊያ ድጋፍ ሰጪነታቸው የሚታወቁትን 18 ተጨማሪ "ኤ-10... read more
በቲክቶክ ቪዲዮ የፕሬዝዳንቱን ክብር አዋረዱ የተባሉ ወጣቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ
መስከረም 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ሁለት የቲክቶክ ተጠቃሚዎች ፕሬዝዳንቱን የሚያወግዝ ዳንስ በመደነስ የቀረጹትን በማህበራዊ ሚዲያ... read more
በትውልድ ግንባታ ሂደት ወጣቶች የአርበኞችን ታሪክ እንዲረዱ ማድረግ ይገባል ተባለ
በቀደምት ጊዜ ሃገር በጠላት እጅ እንዳትወድቅ ለመከላከል በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ አርበኞች ከፍተኛ መስዋት የከፈሉበትን ቀን ለመዘከር የአርበኞች ቀን በዛሬው ዕለት... read more
ኢትዮ ቴሌኮም በጅማ ከተማ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን የሚያስችል የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት ስምምነት ተፈራረመ
ኢትዮ ቴሌኮም ከጅማ ከተማ አስተዳደር ጋር በከተማዋ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያደርግ የስማርት ሲቲ “ስማርት ጅማ” ፕሮጀክትን ለመተግበር የሚያስችል... read more
በተያዘው ዓመት የትራንስፖርት አሰሪዎችና አሽከርካሪዎችን የስራ ውል ሙሉ በሙሉ ለማስተግበር እንደሚሰራ ፌዴሬሽኑ ገለጸ
መስከረም 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በአሽከርካሪዎችና በአሰሪ ባለንብረቶች መካከል ይተገበራል የተባለው የስራ ውል በያዝነው 2018 ዓ.ም እንዲተገበር አደርጋለሁ ሲል የኢትዮጵያ... read more
የሽንት ቤት ወረቀት ለማግኘት ማስታወቂያ መመልከት ግዴታ ሆነ
መስከረም 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በቻይና አንዳንድ የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች፣ የሽንት ቤት ወረቀትን ለመስጠት ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠ አዲስ ሥርዓት መዘርጋታቸው... read more
በመጪው ሳምንት የደሴ ሙዚየም ለጎብኝዎች ክፍት እንደሚሆን ተገለጸ
በደሴ ሙዜም የተዘረፉ ቅርፆችን ለማሰባሰብና ሙዚየሙ ዘመኑን በዋጀ መልኩ በኢዲስ መልክ ለማደስ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማህበር ከብሪትሽ ካውንስል ባገኘው 25... read more
የካሳ ክፍያ እና የፀጥታ ችግር ሀገራዊ የመንገድ ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ እንዳይጠናቀቁ ማድረጉ ተገለጸ
እንደ ሀገር የፀጥታ ችግርና ካሳ ክፍያ የመንገድ ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ እንዳይጠናቀቁ ማድረጉን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
ተቋሙ የተበላሹ መንገዶችና... read more
ሰሜን ኮሪያ 5,000 ቶን የሚመዝን #አጥፊ የጦር መርከብ በሚቀጥለው ጥቅምት ልትገነባ ነው
ሐምሌ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ሰሜን ኮሪያ ሶስተኛውን 5,000 ቶን የሚመዝነውን የቾይ ህየን (Choe Hyon) ክፍል የጦር መርከብ በገዢው ሰራተኞች ፓርቲ... read more
“በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ ሙሉ ቁጥጥር አለን፤ ኢራንን በፍጹም አላምንም!” – ዶናልድ ትራምፕ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በስትራቴጂካዊው የሆርሙዝ ሰርጥ የባህር መስመር ላይ "ሙሉ ቁጥጥር" እንዳላት በመግለጽ በኢራን ላይ የሰነዘሩትን ጠንካራ ወቀሳ... read more
ምላሽ ይስጡ