መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በሃገር ጉዳይ ላይ ያገባናል የሚል ዜጋ ሁሉ በቅድሚያ የሃገርን ሰላም ማስጠበቅና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ማንሳት እንደሚገባ ያመላከቱት የሕብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ግርማ በቀለ ናቸው፡፡ የልዩነት ጥያቄዎችን በሰለጠነ መልኩ በማንሳት የህዝብን ሰላም መጠበቅ ላይ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አክለው፣ በግጭቶች ምንም አይነት መፍትሔ ማምጣት ስለማይቻል ለሰላም ቅድሚያ ሊሰጥ ይገባል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ላለፉት 50 አመታት ባልተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ እንድታልፍና በአንዳንድ አካባቢዎች አለመረጋጋቶች እንዲፈጠሩ ያደረገው፣ ሃገራዊ የሆኑ መግባባቶች ላይ ትኩረት ባለማድረጋችን መሆኑን ገልጸው፣ አሸናፊነት በሃይል ላይ የተመሰረተ ከሆነ ለውጥ ማምጣት ስለማይቻል ወጣቶች፣ የሲቪል ማህበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና በመንግስት በኩል ለሰላም ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ አስምረውበታል፡፡ ሠላም የሁሉም ነገር መሰረት እንደሆነና ከጦርነት የምናተርፈው ነገር እንደሌለ የገለፁት ደግሞ ሌላኛው ‹የአዲስ ትውልድ ፓርቲ› ፕሬዝዳንትና የኦሮምያ የጋራ ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ ሰለሞን ታፈሰ፣ ጦርነት ንብረት ከማውደም፣ ህዝብን በስነ-ልቦናና በአካል ከመጉዳት ውጭ ትርፍ ስለሌለው እርቅን ማስቀደም ይገባል ብለዋል፡፡ በሃሳብ አለመግባባቶች ምክኒያት አዛውንቶች እንዲሰደዱ ህፃናት እንዳይማሩና ንብረት እንዲወድም ምክኒያት እንዳንሆን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ወጣቶችና የሃይማኖት አባቶች በሙሉ ሃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡ ከግጭት የምናተርፈው ነገር ስለሌለ በሃገር አቀፍ ደረጃ ሰላምን ለማስፈን ሁሉም አካል በያገባኛል ስሜት ሊሰራ እንደሚገባ ፓርቲዎቹ አመላክተዋል፡፡ ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ጊፍት ሪል እስቴት 2 ሺሕ ቤቶችን ለመሸጥ የሚያስችለውን የሽያጭ መርሃ ግብር በይፋ አስጀመረ
ነሐሴ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጊፍት ሪል እስቴት በለገሀር ሳይቱ 2 ሺሕ ቤቶችን ለሽያጭ ማቅረቡን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።
ከ2ሺህ ቤቶቹ... read more
የአርበኞች ቀንና የኋላ ታሪካቸው
👉
https://youtu.be/8PGo7h-L6zU
read more
ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ጠብ አጫሪ ንግግር ከሰላማዊ አማራጭ ያለፈ ምላሽ እንደማትሰጥ ተገለጸ
ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ጠብ አጫሪ ንግግር ከሰላማዊ አማራጭ ያለፈ ምላሽ እንደማትሰጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
እንደ ሀገር የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ መርህ ከጎረቤት... read more
የሴቶች ተሳትፎ ባልተረጋገጠበት የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታን እውን ማድረግ እንደማይቻል ተገለጸ
መጋቢት 14 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ከክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጋር በመተባበር በሚያዘጋጀው “ጉሚ በላል” የሃሳብ መድረክ... read more
በሃረሪ ክልል የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች መታደሳቸው የቱሪስት ፍሰቱ እንዲጨምር አድርጓል ተባለ
በሃገራችን ኢትዮጵያ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ቅርሶች እና የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች ከሚገኙባቸው አከባቢዎች አንዱ የሃረሪ ክልል ሲሆን የጀጎል ግንብ፤ የጅብ ትርዒት... read more
በአፍሪካ የመጀመሪያው ማስተር ካርድ ይፋ ተደረገ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የካርድ ክፍያ ሥርዓቱን አንድ ደረጃ ከፍ ያደርጋል የተባለለትና በበይነ መረብ መጠቀም የሚያስችል ቨርቿል ማስተር ካርድን የኢትዮጵያ ንግድ... read more
በእርዳታ የሚገቡ የምግብና የህክምና መሳሪያዎች ሁሉ ችግር የሌለባቸዉ አድርጎ የማሰብ የገንዛቤ ክፍተት እንዳለ ባለስልጣኑ አስታወቀ
ለእርዳታ ከውጭ የሚገቡ የምግብና የህክምና መሳሪያዎችን የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ ቢሆንም ሁሉም የእርዳታ መሳሪያዎችና የምግብ ድጋፎች... read more
ድጋፍ የሚሹት በጎ አድራጎት ድርጅቶች..👉
https://youtu.be/eMP3cELi4bk
read more
ከጅቡቲ 94 በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎች ወደሀገራቸው ገቡ
ኅዳር 26 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በጅቡቲ በችግር ውስጥ የነበሩ 94 ኢትዮጵያውያን ወደሀገራቸው መግባታቸው ተገለጸ።
በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች... read more
ክሪስታል ፓላስ አዲስ አሰልጣኝ መሾሙ ተሰማ
ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ክሪስታል ፓላስ ፈረንሳዊውን ታክቲሻን ፒየር ሴጅን አዲሱ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ለመሾም ከስምምነት ላይ መድረሱን ታዋቂው... read more
ምላሽ ይስጡ