ነሐሴ 06 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በሆርሙዝ ሰርጥ አቅራቢያ በተካሄደ ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ የተመቱ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ባስከተሉት ተደጋጋሚ የነዳጅ መፍሰስ ምክንያት፣ የኢራን የባህር ዳርቻዎች በተለይም በቀሽም (Qeshm) እና ላራክ (Larak) ደሴቶች አካባቢ በወፍራም የነዳጅ እና ታር (tar) ቆሻሻ መሸፈናቸው ተገለጸ።
በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተሰራጩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች የባህር ዳርቻዎቹ ሙሉ በሙሉ ወደ ጥቁርነት መቀየራቸውንና የነዳጅ ቆሻሻው የባህር ውኃውን መሸፈኑን ያሳያሉ። ይህ የአካባቢ ጥበቃ ውድመት የጀመረው ከየካቲት 2026 ጀምሮ በቀጣናው በተቀሰቀሰው ግጭትና በንግድ መርከቦች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት እንደሆነ ተመልክቷል።
ይህ የነዳጅ ብክለት ጥበቃ የሚደረግለት የሀራ ማንግሩቭ (Hara mangrove) ደን የመጨረሻ ክፍሎች የደረሰ ሲሆን፣ የፋርስ ባሕረ ሰላጤ የውኃ ጥልቀት ማነስና አነስተኛ የውኃ እንቅስቃሴ አደጋውን አባብሶታል። ሁኔታው በኮራል ሪፎች፣ በባህር ህይወታውያን እና በአካባቢው አሳ አጥማጆች መኖሪያ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።
የኢራን አስቸኳይ ጊዜ ባለስልጣናት የብከላውን ስፋት አረጋግጠው የፅዳት ስራዎችን ያዘዙ ቢሆንም፣ አደጋው ከአንድ ነጠላ ክስተት ይልቅ ለወራት ከቀጠለው ወታደራዊ ግጭት የተከማቸ እንደሆነ ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ከኦማን ዳርቻ አቅራቢያ ከሩሲያ የነዳጅ ጫኝ መርከብ የወጣ ሌላ የነዳጅ ብክለት የተስተዋለ ሲሆን፣ ይህም ክስተት ግጭቱ ካበቃ በኋላም ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የአካባቢ ውድመት እንደሚያስከትል ስጋት ፈጥሯል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
የትምህርት ሚኒስትር የዩኒቨርሲቲዎች በጀት ባስመዘገቡት ውጤት ልክ የሚመደብ ይሆናል ቢልም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በበጀት ጉዳይ እንደማይመለከተው እና ስምምነቱ ተግባራዊ ቢደረግ በትምህርት ጥራት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚፈጥር ተገለጸ
ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከሰሞኑ በሰጡት መግለጫ የዩኒቨርሲቲዎች በጀት ባስመዘገቡት ውጤት ልክ የሚመደብ ይሆናል... read more
ዘመናዊ የባህል፤ቅርስና ቋንቋ መልክዓ ምድረርን ለመፍጠር ቴክኖሎጂን ጥቅም ላይ ማዋል ይገባል ተባለ
ዘመኑ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የባህል፣ ቅርስ እና ቋንቋን ለመመዝገብና ለመሰነድ ከፍተኛ እድል የሚሰጥ ነው ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል ኪነ... read more
በጸጥታ ችግር ምክንያት ከ7 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ አልተመለሱም
በአንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠረ የጸጥታ ችግር ምክንያት ከ7 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው አለመመለሳቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ... read more
የታክስ አስተዳደር ረቂቅ አዋጁ ለሙስና ተጋላጭ እንዳይሆን አሳሪ የህግ ማዕቀፍ ሊኖረው ይገባል ተባለ
ሰኔ 01 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ የንግድ ስርዓት በደረሰኝ የመገበያየት ልማድ ሰፊ ክፍተት እንደሚታይበትና፥ በሸማቹም ሆነ በነጋዴው ማህበረሰብ ዘንድ ደረሰኝ... read more
በሰሜን ጎንደር ዞን በደባርቅ ወረዳ በደረሰ ከፍተኛ የመኪና አደጋ የሰው ሕይወት አለፈ
በሰሜን ጎንደር ዞን በደባርቅ ወረዳ ልዩ ስሙ አበርጊና ቀበሌ በደረሰ ከፍተኛ የመኪና አደጋ የ12 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡
በአደጋው ከሟቾች በተጨማሪ... read more
በእግረኞች መንገድ በተሽከርካሪ የሄደው ግለሰብ 100 ሺህ ብር መቀጣቱ ተገለፀ
ሰኔ 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በትላንትናው እለት በአቃቂ ክፋለ ከተማ በእግረኞች መንገድ ላይ በኮድ 4... read more
ከ2መቶ 78ሺህ ብር በላይ ከደንበኞች አካውንት በመቀነስ ለግል ጥቅሙ ያዋለ የባንክ ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ዋለ
♻️ከ2መቶ 78ሺህ ብር በላይ ከደንበኞች አካውንት በመቀነስ ለግል ጥቅሙ ያዋለ የባንክ የደንበኞች አገልግሎት ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ውሎ ክስ መመስረቱን የአዲስ... read more
ለተማሪዎች ደመወዝ የምትከፍለው አስገራሚዋ ሀገር!
ሰኔ 13 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ወጣቶች ወደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲገቡ ትምህርታቸውን ጥለው እንዳይወጡ እና በትምህርታቸው ላይ ብቻ ትኩረት... read more
በተመረጡ ስድስት ዘርፎች 5ኛው የጣፋጭ ህይወት የምስጋና መርሃ-ግብር ሊካሄድ ነዉ
በተመረጡ 6 ዘርፎች ላይ 5ኛው የጣፋጭ ህይወት የምስጋና መርሃ-ግብር ሊካሄድ መሆኑን ጣፋጭ ህይወት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
በየአመቱ እየተከናወነ ያለዉ... read more
የኢትዮጵያ የፍራፍሬ ልማት፦ ዕድሎች፣ ተግዳሮቶች እና የወደፊት ተስፋዎች
ግብርና የበርካታ ሀገራትን ምጣኔ ሀብታዊ እንቅስቃሴ በማሳደግ፣ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ በፍጥነት እንዲሸጋገሩ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና እንዳለው... read more
ምላሽ ይስጡ