ሕዳር 14 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሰሜን ኮሪያውን መሪ ኪም ጆንግ ኡንን በቀጥታ ለማነጋገር ያደረጉት ጥረት ምላሽ እንዳላገኘና የላኩላቸው ደብዳቤም ሳይከፈት መመለሱን ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል (The Wall Street Journal) ዘገበ።
ዘገባው እንደሚያመለክተው፣ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ባለፈው ዓመት በተለያዩ መንገዶች ኪምን ለማግኘት ቢሞክሩም ምንም ምላሽ ማግኘት አልቻሉም። በመቀጠልም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) የሰሜን ኮሪያ ዲፕሎማት በኩል ደብዳቤ ቢልኩም፣ ደብዳቤው ሳይከፈት ለአሜሪካ ተወካይ ተመልሷል።
ትራምፕ ከቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ እና ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በተገናኙበት በቅርቡ ባደረጉት የእስያ ጉብኝት ወቅትም፣ ከኪም ጆንግ ኡን ጋር ውይይት ለማድረግ ጥረት ማድረጋቸው ተጠቁሟል።
ይሁን እንጂ ሰሜን ኮሪያ ዋይት ሀውስ ሊቀበላቸው የማይችላቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ማስቀመጧ የተነገረ ሲሆን፣ ኪም ጆንግ ኡን ሀገራቸው እንደ ኑክሌር ኃይል ታወቅላት የሚል ፍላጎት እንዳላቸው ተዘግቧል።
ዶናልድ ትራምፕ በመጀመሪያው የፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው ከኪም ጆንግ ኡን ጋር ሦስት ጊዜ የተገናኙ ቢሆንም፣ ውይይቶቹ ሰሜን ኮሪያን ከኑክሌር ነጻ በማድረግ ረገድ ምንም ዓይነት እድገት ሳያስመዘግቡ ማብቃታቸው ይታወሳል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
በኤስካሌተሮች ጎን የሚገኙት ብሩሾች ለጫማ ማጽጃ ወይስ ከአደጋ መጠበቂያ? ከጀርባቸው ያለው አስገራሚ የህይወት አድን ምስጢር!
ሰኔ 18 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) ዘመናዊ የገበያ ማዕከላት፣ የአውሮፕላን ማረፊያዎች ወይም ትላልቅ ህንፃዎች ውስጥ በመግባት ተንቀሳቃሽ ደረጃዎችን (Escalators) ስንጠቀም፣... read more
የአፍሪካ ህብረትና ኢጋድ ለደቡብ ሱዳን ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገለጹ
የአፍሪካ ህብረት እና ኢጋድ በደቡብ ሱዳን ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት ለማስፈን እየተደረገ ላለው ጥረት ያልተቆጠበ ድጋፋቸውን ማድረግ እንደሚቀጥሉ አስታወቁ።
የደቡብ ሱዳን... read more
በኢትዮጵያ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ብርቅዬ የተባለውን ሰማያዊ ላቫ አመነጨ
የኢትዮጵያ እሳተ ገሞራዎች ውስጥ እጅግ ብርቅዬ የሚባለውን ሰማያዊ ላቫ እየፈነጠቀ መሆኑ እንደ ክስተት እየታየ ይገኛል። ከኢንዶኔዢያ ጃቫ ግዛት ካዋ ኢጄን... read more
ኢሚግሬሽን ውስጥ የሚታየው ብልሹ አሰራርና መፍትሄው
https://youtu.be/df_HeM5X-Ws
read more
የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር የእስራኤል አትሌቶች ከዓለም አቀፍ ውድድሮች እንዲታገዱ ጠየቁ
መስከረም 06 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ፣ በእስራኤል አትሌቶች ላይ የዓለም አቀፍ እገዳ እንዲጣል ጥሪ ማቅረባቸው ተገለጸ።... read more
የመጀመሪያው የኢትዮ-ባንግላዲሽ የገበያ ትስስር ጉባኤ ተካሄደ
ሕዳር 04 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የመጀመሪያው የኢትዮ-ባንግላዲሽ የንግድ ሾው በአዲስ አበባ መካሄዱ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የንግድ ትስስር ዕድል የሚፈጥር መሆኑን የውጭ ጉዳይ... read more
በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስቆም በክልሎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት (NEWA) ያለዕድሜ ጋብቻን፣ የሴት ልጅ ግርዛትን እና ሌሎች ጎጂ... read more
ለአንድ ሃገር ዘላቂ ሰላም መስፈን ከሚያስፈለጉ ነገሮች መካከል በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ያለው ግንኙነት የጠነከረ እና ሰላማዊ መሆን እንዳለበት ይገለጻል፡፡
ቢሆንም ግን በሃገራችን ያለው የፖለቲካ ውቅር እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ግንኙነት ደካማ ሆኖ የቆየ መሆኑ ይነሳል።
ቢሆንም ግን ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ... read more
የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አቅም ያሳድጋል የተባለው የኢትዮጵያ – አውሮፓ ህብረት የንግድ ፎረም 2026 ተጀመረ
ሚያዚያ 12 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አቅም ያሳድጋል የተባለውና ከዛሬ ሚያዝያ 12 እስከ ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚቆየው የኢትዮጵያ... read more
ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፉ ምግብና መጠጦችን እንዳስወገደ የአዲስ አበባ ምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ
ኅዳር 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በመዲናዋ 6 ሚሊየን 44ሺህ 402 ብር የሚያወጣ ግምት ያላቸው የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፉ ምግብና መጠጦች ናቸው... read more
ምላሽ ይስጡ