ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ በፋይናንስ ዘርፍ ላይ ያሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ወደ አገር ውስጥ ገብተው ሥራ እንዲጀምሩ አዋጅ መዘጋጀቱን ተከትሎ፣ የአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት እንዳይዳከሙ መጠናከር እንደሚገባቸው በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማት ለጣቢያችን ገልጸዋል።
በአገር ውስጥ ያለው የፋይናንስ አሠራር እና የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ አገር በቀል የሆኑ የፋይናንስ ተቋማት ማደግ በሚገባቸው ልክ እንዳያድጉ ማድረጉን የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የኢንተርፕራይዝ ማኔጅመንት ዳይሬክተር አቶ ፍሥሐ ተስፋዬ ገልጸዋል። በአንጻሩ በፋይናንስ ዘርፉ ላይ የተሰማሩ ተቋማት በጋራና በጥምረት ሊሠሩባቸው የሚችሉ ጉዳዮችን በመለየት ማጠናከር እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።
በኢትዮጵያ በርካታው የማኅበረሰብ ክፍል የሚገኘው በአገሪቱ ገጠራማ አካባቢዎች ላይ እንደመሆኑ፣ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ የኅብረት ሥራ ተቋማት አቅማቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ የኢንፊኒቲ ብድርና ቁጠባ ኅብረት ሥራ ተቋም ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እስክንድር መኩሪያ ይገልጻሉ። በተለይም ደግሞ በፋይናንስ ዘርፉ ላይ የሚስተዋለው የትብብር ማነስ፣ የጥሬ ገንዘብ እጥረትና ተደራሽነት፣ እንዲሁም ጠንካራ ተቋማት ጥቂት መሆን ሊሻሻሉ የሚገቡ ጉዳዮች ናቸው ብለዋል።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶክተር ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ወደ አገር ውስጥ ገብተው ሥራ መጀመራቸው ለትልልቅ የኢንቨስትመንት ሥራዎች እና ለውጭ ምንዛሬ አቅርቦት በጎ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ተናግረዋል። ከሰሞኑ በኢንቨስትመንት ባንክ ሥራ ላይ የተሰማራው የናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል ግሩፕ በካፒታል ገበያ ላይ ሕጋዊ ፈቃድ ያገኘ ሲሆን፣ በቀጣይም በኢትዮጵያ በባንክ አገልግሎት ዘርፍም ሆነ በኢንሹራንስ ዘርፍ የተሰማሩ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ፈቃድ አግኝተው ሥራ ሲጀምሩ ለኢኮኖሚው ጠቃሚ እንደሚሆኑና በአገር በቀል ባንኮች ላይ ጫና እንደማያሳድሩ አመላክተዋል።
የውጭ አገር ባንኮች በአገር ውስጥ ገብተው እንዲሠሩ የሚፈቅደው አዋጅ መጽደቁ የሚታወስ ሲሆን፣ የኢንሹራንስ ድርጅቶች እንዲሠሩ የሚፈቅደው ረቂቅ አዋጅም በቅርቡ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ከ1 ሺህ 500 በላይ አዳዲስ መጋቢ እናቶችን ለመቅጠር መታቀዱ ተገለጸ፡፡
ነሐሴ 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በበጀት ዓመቱ በተለያዩ ምክንያቶች ሥራ በሚያቆሙ መጋቢ እናቶች ምትክ ከ1 ሺህ 500 በላይ እናቶችን ለመቅጠር... read more
የአፍሪካ ህብረት ያስተናገደዉ ትችት
https://youtu.be/QaJRu6aY5H0
read more
አርሰናል ከክሪስታል ፓላስ ጋር የሚያደርጉት የካራባኦ ካፕ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ቀን የተወሰነ ሲሆን መነጋገሪያ ርዕስን ከፍቷል
ጥቅምት 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) – አርሰናል ብራይተንን፣ ክሪስታል ፓላስ ደግሞ ክዊንስ ፓርክ ሬንጀርስን በመርታት በካራባኦ ካፕ አራተኛ ዙር ጨዋታ... read more
ከ600ሺህ በላይ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙ ተገለጸ
ለ2017/18 የምርት ዘመን ግብዓት የሚውል 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ለመግዛት ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱ ተመላክቷል።
ከዚህ ውስጥ... read more
የእስራኤል እና የኢራን ጦርነት አሁናዊ ሁኔታ
ባለፉት ቀናት በእስራኤል እና በኢራን መካከል ያለው ግጭት እጅግ በጣም ተባብሶ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ የከተተ ክስተቶች ተከስተዋል። ሁለቱም ሀገራት በቀጥታ... read more
‹‹የምድር ጌጥ ኢትዮጵያ» ታሪካዊና ባህላዊ አዉደ ርዕይ ለሶስት ሳምንታት መራዘሙ ተገለጸ
መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) «የምድር ጌጥ ኢትዮጵያ» በሚል ርዕስ ሲካሄድ የቆየው ታሪካዊና ባህላዊ አውደ ርዕይ የመጎበኛ ጊዜ፣... read more
በሃረሪ ክልል የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች መታደሳቸው የቱሪስት ፍሰቱ እንዲጨምር አድርጓል ተባለ
በሃገራችን ኢትዮጵያ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ቅርሶች እና የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች ከሚገኙባቸው አከባቢዎች አንዱ የሃረሪ ክልል ሲሆን የጀጎል ግንብ፤ የጅብ ትርዒት... read more
የዩኤንኤድስ (UNAIDS) ሪፖርትና በአፍሪካ ሴቶች ላይ ያለው አደጋ
የተባበሩት መንግሥታት የኤድስ መከላከል ፕሮግራም (ዩኤንኤድስ) ዓለም አቀፍ የኤድስ ቀንን አስመልክቶ ይፋ ባደረገው የ2025 ሪፖርት፣ በኤድስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከ2010... read more
ባለፉት 6 ወራት በከተማዋ ከተፈጠረው የሥራ ዕድል ውስጥ 54 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው ተባለ
መጋቢት 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች፣ ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ፤ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ እንዲሁም ተጠቃሚነት በተመለከተ... read more
በደሴ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ12 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ
ጥር 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በደሴ ከተማ ሰኞ ገበያ ክፍለ ከተማ ኮሸምበር ቀበሌ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ጉዞውን ከፒያሳ ወደ ገራዶ... read more
ምላሽ ይስጡ