መስከረም 08 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ አጥቂ የሆነው ጆአዎ ፔድሮ ባጋጠመው የጉዳት ህመም ምክንያት ከመጪው ዓለም አቀፍ የወዳጅነት እና የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች ከሀገሩ ብራዚል ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውጪ መሆኑ ተረጋገጧል። ባለፈው ሳምንት ቼልሲ ከሃል ሲቲ ጋር 2-2 በተለያየበት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ላይ ለ90 ደቂቃ ተሰልፎ የአቻነቷን ግብ ያስቆጠረው የ24 ዓመቱ አጥቂ፣ ከጨዋታው በኋላ በተደረጉ የልምምድ መርሃ ግብሮች ላይ ሳይሳተፍ ቀርቷል። የሴሌሳኦዎቹ አሰልጣኝ ካርሎ አንቼሎቲ ለአውስትራሊያ እና ህንድ የወዳጅነት ጨዋታዎች በስብስባቸው ውስጥ አካተውት የነበረ ቢሆንም፣ በጉዳቱ ምክንያት ከስብስቡ ውጪ በመሆኑ የፍሉሚኔሴው ማርቲኔሊ በእሱ ቦታ ተተክቶ መጠራቱን የብራዚል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል። ጆአዎ ፔድሮ በያዝነው አዲሱ የውድድር ዘመን በ4 የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች 3 ግቦችን በማስቆጠር እና 3 ግቦችን አመቻችቶ በመስጠት አስደናቂ አጀማመር ያደረገ ሲሆን፣ የነሐሴ ወር የፕሪምየር ሊጉ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ መመረጡ ይታወሳል። የቼልሲው አሰልጣኝ ሻቢ አሎንሶ በቅርቡ ስለ ተጫዋቹ አጠቃላይ ብቃት ሲናገሩ፣ ከሳጥን ውጪ እና ውስጥ ባለው ሁለገብነት የታከለ የመጫወት ችሎታው የቀድሞውን የሪያል ማድሪድ አንጋፋ ተጫዋች ካሪም ቤንዜማን እንደሚያስታውሳቸው መናገራቸው የሚታወስ ነው። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ሪካርዶ ካሊያፊዮሪ በዚ የውድድር ዘመን ለ4ኛ ጊዜ ጉዳት እንዳጋጠመው እየተገለፀ ነው
ጥር 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ይህ ጣልያናዊ ለጉዳት በጣም ተጋላጭ የሆነ ተጫዋች መሆኑ በተደጋጋሚ ገና ቦሎኛም እያለ የጉዳት ታሪክ በብዛት... read more
አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዜርቢ «ሪቻርልሰን ጤነኛ ቢሆንም እንኳ ከስብስቡ ውጪ ነው፤ ቦታ የለውም» ሲሉ ተናግረዋል
መስከረም 05 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ይህ በእንዲህ እንዳለ ሪቻርልሰን የቫስኮ ዳ ጋማን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ተገልጿል። የቶተንሃም ሆትስፐርሱ ብራዚላዊ አጥቂ... read more
ያኒክ ሲነር ዌምብልደንን አሸነፈ
ሐምሌ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በAll england club አዘጋጅነት ሲከናወን የቆየው ተወዳጁ እና ትልቁ የሜዳ ቴኒስ ውድድር ዌምብልደን ትላንት ሲጠነመቀቅ በወንዶች... read more
አርሰናል ቀጣይ አመት የሚጠቀሙበትን ማልያ ይፋ አድርገዋል
አርሰናል ከአዲዳስ የትጥቅ አምራች ተቋም ጋር ባላቸው ስምምነት መሰረት በየአመቱ የክለቡን ታሪክ ፤ ማንነትን ሊያሳዩ የሚችሉ ዲዛይኖችን በመጠቀም ሁሌም አዲሱ... read more
ቲዮ ኸርናንዴዝ ሚላኖች እሱን ባስተናገዱበት መንገድ ደስተኛ አለመሆኑን ለወኪሉ አሳውቋል ተብሏል
ታኅሳስ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ይህ ፈረንሳዊ የቡድኑ አምበል የኮንትራት ሁኔታው አሳሳቢ እንደሆነ ይታወቃል። በ2026 ውሉ ይጠናቀቃል ስለዚህ ውሉን እንዲያድስ... read more
በማንችስተር ደርቢ ጨዋታ ላይ ማንቸስተር ሲቲ በስህተት ያስቆጠረውን ጎል እንዲጸድቅ ያደረገው እና በቪኤአር (VAR) ላይ ተሰይሞ የነበረው ዳኛ ቅጣት ተላልፎበታል
መስከረም 05 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከትላንት በስቲያ በኦልድ ትራፎርድ በተደረገው የማንቸስተር ደርቢ ጨዋታ ላይ የማንቸስተር ሲቲውን አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ ያስቆጠራትን... read more
«ባሎንዶሩ ለእኔ ነው የሚገባው» ሲል ላሚን ያማል አስተያየቱን ሰጠ
መስከረም 05 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የባርሴሎናው ወጣት አጥቂ ላሚን ያማል የ2026 የባሎንዶር ክብር ለእሱ እንደሚገባው በራስ መተማመን የተሞላበት አስተያየት የሰጠ... read more
ፍይኖርዶች ሩበን ቫን ፐርሲን በአሰልጣኝነት መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል
የ41 አመቱ የቀድሞ የማንቸስተር ዩናይትድ እና የአርሰናል የአጥቂ መስመር ተጫዋች የሆነው ሮቨን ቫን ፐርሲ በኤርዲቪዝዬው እየተጫወተ የሚገኘው ኸረንቪን እያሰለጠነ እንደሚገኝ... read more
ማንቸስተር ሲቲዎች ፍሎሪያን ቪርትዝን ለማስፈረም ከሚደረገው ፉክክር ራሳቸውን አገለሉ
የ22 አመቱ ጀርመናዊ የአጥቂ አማካኝ መስመር ተጫዋች በአሁን ሰአት ከሚፈለጉ ፤ በጣም አስደናቂ እንቅስቃሴን ከሚያደርጉ ተጫዋቾች ተርታ ስሙ ይሰለፋል።
ታዲያ ተጫዋቹን... read more
ካርሎስ አልካራዝ አስደናቂ ድል በማስመዝገብ የግራንድ ስለም ሻምፒዮን መሆኑን አረጋገጠ
በታሪክ ረጅም ሰአት የፈጀው የሮላንድ ጌሮስ የፈረንሳይ ሜዳ ኦፕን ቴኒስ የፍፃሜ ውድድር በስፔናዊው ተስፈኛ የሜዳ ቴኒስ ተወዳዳሪ ካርሎስ አልካራዝ አሸናፊነት... read more
ምላሽ ይስጡ