መስከረም 05 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ይህ በእንዲህ እንዳለ ሪቻርልሰን የቫስኮ ዳ ጋማን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ተገልጿል። የቶተንሃም ሆትስፐርሱ ብራዚላዊ አጥቂ ሪቻርልሰን ከብራዚሉ ክለብ ቫስኮ ዳ ጋማ የቀረበለትን የውል ስምምነት ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ ከለንደኑ ክለብ የመልቀቅ እድሉ ሳይሳካለት ቀርቷል። የቲምቶክ ዘገባ እንደሚያመለክተው ከሆነ የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሃም የ29 ዓመቱን የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አጥቂ በ20 ሚሊዮን ዩሮ ገደማ ለቫስኮ ዳ ጋማ ለመሸጥ ከስምምነት ላይ ደርሶ የነበረ ቢሆንም፣ ተጫዋቹ የቀረቡለትን የውል መስፈርቶች ባለመቀበሉ ዝውውሩ ሙሉ በሙሉ ከሽፏል። በአዲሱ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዜርቢ የፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾች ስብስብ ውስጥ ያልተካተተው ሪቻርልሰን ወደ ሀገሩ ብራዚል ለመመለስ ፍላጎት የነበረው ቢሆንም፣ እስከ መጪው ጥር የዝውውር መስኮት ብቻ የሚቆይ የአጭር ጊዜ ውል በመፈለጉ ምክንያት ድርድሩ ሳይሳካ ቀርቷል። ቫስኮ ዳ ጋማ በበኩሉ ከፍተኛ ወጪ የሚያወጣበት ዝውውር በመሆኑ ተጫዋቹ ቢያንስ የ18 ወራት የረጅም ጊዜ ውል እንዲፈርም ቢጠይቅም ተጫዋቹ በዚህ ጉዳይ ሊስማማ አልቻለም። ቀደም ሲል ወደ ቀድሞ ክለቡ ኤቨርተን ለመመለስ የቀረበለትን እድል ውድቅ ያደረገው እና ወደ ቱርኩ ትራብዞንስፖር ለማመራት የነበረው ዝውውር የከሸፈበት ሪቻርልሰን፣ አሁንም በቶተንሃም ቤት የወደፊት እጣ ፈንታው አጠራጣሪ ሆኖ ቀጥሏል።
___
ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
ምላሽ ይስጡ