መስከረም 05 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቲምቶክ ጸሐፊ ጋዜጠኛ አለን ኒክሰን እንዲሁም ሪለክተንት ኒኮ ያወጡት መረጃ፣ መድፈኞቹ ይህንን ተስፈኛ ወጣት ኮከብ ተጫዋች ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው በዝርዝር አመላክቷል። የ18 ዓመቱ እንግሊዛዊ ወጣት የክንፍ አጥቂ መስመር ተጫዋች በሚፈልገው እና በሚጠብቀው ደረጃ የጨዋታ ደቂቃዎችን እያገኘ አይደለም። «እንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ» እንዲሉ፣ አቅሙን በደንብ ማሳየት በሚችልበት ቦታ ላይ ሦስተኛ ተመራጭ የሚያደርገውን ውሳኔ ሊቨርፑል መወሰኑ ማለትም ብራድሊ ባርኮላን በድምሩ በ120 ሚሊዮን ፓውንድ ለማስፈረም መወሰናቸው በአጠቃላይ ሪዮ ንጎሞሀ ክለቡን ለመልቀቅ እንዲያስብ እያደረገው እንደሚገኝ ተዘግቧል። ይህንንም ተከትሎ የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የ18 ዓመቱን የሊቨርፑል ወጣት የክንፍ አጥቂ ሪዮ ንጎሞሃን ሁኔታ በጥብቅ እና በቅርበት በመከታተል ላይ እንደሚገኝ ጋዜጠኛ አለን ኒክሰን በቲምቶክ በኩል ይዞት የወጣው መረጃ ያመላክታል። ሆኖም ግን የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ወጣቱ የ18 ዓመት ተጫዋች የወደፊት የቡድኑ አካል በመሆኑ በቀላሉ ለሽያጭ ያቀርበዋል ተብሎ አይገመትም።
___
ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
ምላሽ ይስጡ