🔴የስዊዘርላንዷ አልቢነን መንደር ነዋሪዎቿ በመመናመናቸው ወደ መንደሯ ገብተው ለሚኖሩ ቤተሰቦች እስከ 50 ሺህ ዶላር እንደምትከፍል አስታወቀች
ሕዳር 14 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ)በስዊዘርላንድ ተራራማ አካባቢ የምትገኘው ውቧ አልቢነን (Albinen) መንደር፣ ወጣቶች ለሥራና ለትምህርት ወደ ትላልቅ ከተሞች መፍለሳቸውን ተከትሎ ነዋሪዎቿ በእጅጉ በመቀነሳቸው፣ ወደ መንደሯ ገብተው ለሚኖሩ ሰዎች ከፍተኛ የገንዘብ ማበረታቻ ማዘጋጀቷን ይፋ አደረገች።
ከ250 የማይበልጡ ነዋሪዎች ብቻ የቀሩባት ይህች መንደር፣ ቀዬዋ ሙሉ በሙሉ ባዶ እንዳይቀር ለማድረግ ዕድሜያቸው ከ45 ዓመት በታች ለሆኑ አዋቂዎች እያንዳንዳቸው 25 ሺህ የስዊስ ፍራንክ (ወደ 28 ሺህ ዶላር ገደማ) እንዲሁም ለእያንዳንዱ ልጅ 10 ሺህ የስዊስ ፍራንክ ለመክፈል ወስናለች። በዚህም መሰረት ሁለት ልጆች ያሏቸው ባለትዳሮች ወደ መንደሯ ገብተው ለመኖር ሲወስኑ ከ70 ሺህ ፍራንክ (ከ80 ሺህ ዶላር) በላይ ማበረታቻ ያገኛሉ።
ይሁን እንጂ ገንዘቡን የሚወስዱ ሰዎች በመንደሯ ውስጥ ቢያንስ ለ10 ዓመታት የመኖር እና ቢያንስ 200 ሺህ ፍራንክ የሚያወጣ መኖሪያ ቤት የመግዛት ወይም የመገንባት ግዴታ ይኖርባቸዋል።
የመንደሯ አስተዳደር ይህንን ውሳኔ ያሳለፈው የተዘጋውን የመንደሯን ትምህርት ቤት ዳግም ለመክፈትና የአካባቢውን ሕይወት መልሶ ለማነቃቃት በማሰብ መሆኑ ተገልጿል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ቻይና የሸንዙ-22ን የጠፈር መንኮራኩር ነገ ልታመጥቅ ነው
ሕዳር 15 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ቻይና ሸንዙ-22 የተባለውን ሰው የጫነ የጠፈር መንኮራኩር ነገ ኅዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም ለማምጠቅ የመጨረሻ... read more
እንስሳትን ወደ ድንጋይነት የሚቀይር የሰሜን ታንዛኒያ አስፈሪ ተአምር
ሐምሌ 29 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሰሜን ታንዛኒያ የሚገኘው የናይትሮን ሐይቅ፣ እንስሳትን ወደ ድንጋይነት የመቀየር ኃይል ያለው አስገራሚና ገዳይ የውሃ አካል... read more
በ274ቱ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሥጋ ቤቶች ለአዲስ ዓመት የአንድ ኪሎ ሥጋ ዋጋ 1,200 ብር እንዲሆን ከሥጋ ቤቶቹ ጋር ስምምነት መደረጉ ተገለጸ
ነሐሴ 29 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን በአዲስ ዓመት ከሥጋ አቅርቦትና ዋጋ ጋር በተያያዘ ሸማቹ ኅብረተሰብ እንዳይቸገር... read more
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት 100 የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎችን መግዛቱን አስታወቀ
ሰኔ 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)አገልግሎቱ 100 የከባድ ጭነት ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት በሂደት ላይ መሆኑንም ገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና... read more
ከሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተሰጠ መግለጫ!
መስከረም 07 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካ ኤምባሲ ዶሎ ዞንን በተመለከተ ያወጣው የጉዞ ማስጠንቀቂያ በአካባቢው ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ አያንጸባርቅም! የሶማሌ ክልል... read more
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ ገዝነት ለመሸጋገር እየተዘጋጀሁ ነው አለ
ኅዳር 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማርና ሌሎች ተግባራትን በላቀ ደረጃ ለመፈፀምና ተወዳዳሪነቱን ለማስቀጠል ወደ ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ... read more
ሞርተን ዩልማንድ አትሌቲኮን ለመቀላቀል መስማማቱ ተዘግቧል።
ሐምሌ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአትሌቲኮ ማድሪድ ክለብ የፖርቹጋሉን ስፖርቲንግ ሊዝበን አምበል እና የዴንማርክ ብሔራዊ ቡድን አማካኝ ሞርተን ዩልማንድን ለማስፈረም የተቃረበ... read more
አንድ ታይላንዳዊ ግለሰብ በመኖሪያ ቤቱ መጸዳጃ ቤት ሲጠቀም የዘር ፍሬውን በእባብ ተነከሰ
ሐምሌ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ35 ዓመት ወጣት ታይላንዳዊ ሰው በኖንታቡሪ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ የመታጠቢያ ክፍል ውስጥ መጸዳጃ ቤት ውስጥ... read more
ኢራን ከእስራኤል ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት መደረሱን አረጋገጠች
ሰኔ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢራን የፀጥታ ምክር ቤት ከእስራኤል ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት መደረሱን ማረጋገጡን የሀገሪቱ የመገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።... read more
ካናዳ የፍልስጤምን መንግስት በመስከረም ወር እውቅና ለመስጠት ከፈረንሳይና ከእንግሊዝ ጋር ተቀላቀለች
ሐምሌ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ካናዳ በመስከረም ወር የፍልስጤምን መንግስት በይፋ እውቅና እንደምትሰጥ ማስታወቋን ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ አስታወቁ። ካናዳ በዚህ... read more
ምላሽ ይስጡ