ሐምሌ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአትሌቲኮ ማድሪድ ክለብ የፖርቹጋሉን ስፖርቲንግ ሊዝበን አምበል እና የዴንማርክ ብሔራዊ ቡድን አማካኝ ሞርተን ዩልማንድን ለማስፈረም የተቃረበ ሲሆን፣ በግል ጥቅማጥቅሞች ዙሪያ ከተጫዋቹ ጋር ሙሉ ስምምነት ላይ ደርሷል።
ታዋቂው የስፖርት ጋዜጠኛ ማትዮ ሞሬቶ እንደዘገበው፤ አትሌቲኮ ማድሪድ ከሊዝበን ጋር የነበረው የ35 ሚሊዮን ዩሮ የመጀመሪያ ጥያቄ ውድቅ ከተደረገበት በኋላ፣ አጠቃላይ የዝውውር ሂሳቡን ወደ 40 ሚሊዮን ዩሮ (35 ሚሊዮን ቋሚ እና 5 ሚሊዮን ዩሮ ተጨማሪ ማበረታቻዎች) በማሳደግ ተጫዋቹን ለማስፈረም ተቃርቧል።
የ26 ዓመቱ አማካኝ እስከ 2031 ዓ.ም የሚያቆየውን የ5 ዓመት ኮንትራት ለመፈረም የተስማማ ሲሆን፣ በአዲሱ ክለቡ የቅድመ-ውድድር ዝግጅት ለመጀመር ወደ ማድሪድ ያመራል ተብሎ ይጠበቃል። አትሌቲኮ ማድሪድ ፊቱን ወደ ዩልማንድ ያዞረው፣ ከዎልቭሱ ጆአኦ ጎሜስ ወኪል ጆርጅ ሜንዴስ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ተከትሎ የዝውውር እቅዱን በመቀየሩ ነው።
ሞርተን ዩልማንድ ባለፈው የ2025/2026 የውድድር ዘመን በፖርቹጋል ፕሪሜራ ሊጋ እና በተለያዩ ውድድሮች ለስፖርቲንግ ሊዝበን በአማካኝ መስመር ላይ ቁልፍ ሚና የነበረው ሲሆን፣ 1 ግብ አስቆጥሮ 1 ለግብ የሚሆን ኳስ ማመቻቸት ችሏል።
አትሌቲኮ ማድሪድ ይህንን ተጫዋች አጥብቆ የፈለገበት ዋነኛው ምክንያት በአሰልጣኝ ዲዬጎ ሲሚዮኒ የጨዋታ ስልት ውስጥ ጠንካራ፣ ኳስ አስጣይ እና መከላከል ላይ ያተኮረ ንቁ የተከላካይ አማካኝ (Defensive Midfielder) እንዲሁም በተከላካይ እና በአጥቂ መስመር መካከል ድልድይ የሚሆን ተጫዋች ስለሚያስፈልገው ነው።
ዩልማንድ በስፖርቲንግ ሊዝበን መሪነቱን እና የአማካኝ ክፍሉን በአግባቡ የመቆጣጠር ብቃቱን ያሳየ በመሆኑ፣ ሲሚዮኒ ለሚገነቡት አዲስ የአማካኝ መስመር ጥንካሬ ዋነኛ ምርጫቸው አድርገውታል፤ ተጫዋቹም በሮጂብላንኮዎቹ ቤት ለ5 ዓመታት የሚያቆየውን ኮንትራት ይፈራረማል ተብሎ ይጠበቃል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ምክር ቤቱ ሁለት የብድር ስምምነት አዋጆችን አጽድቋል
ጥር 19 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ በዛሬው ዕለት... read more
በመዲናዋ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ከ200 ማለፋቸው ተገለጸ
በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደረውን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ያለበትን የኑሮ ጫና ለማቅለል በመንግስት የተቋቋሙት የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ከ200 ማለፋቸውን የአዲስ አበባ... read more
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በተጨመረለት የ1 ዓመት የስራ ቆይታ አጀንዳዎችን የመቅረፅ እና ይፋ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ ገለጸ
ሰሞኑን የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሦስት ዓመት የስራ... read more
አል ሂላሎች ሞሀመድ ሳላህን በእጃቸው ለማስገባት በጣም አይን አዋጅ የሆነ ኮንትራት በማቅረብ ተጫዋቹ ኔይማር ጁኒየርን እንዲተካላቸው ይፈልጋሉ ሲል Sky sport ይዞት የወጣው መረጃ ያመላክታል
ጥር 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የ32 አመቱ ግብፃዊው ኮኮብ ሞሀመድ ሳላህ እስካሁን በኮንትራቱ ጉዳይ አዲስ ነገር እንደሌለ እና ለሱ ይሄ በሊቨርፑል... read more
በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ የገንዘብ እና የመሥሪያ ቦታ እጥረት ለዘርፉ ዋነኛ ተግዳሮቶች መሆናቸው ተገለ
ነሐሴ 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአገራችን እየተከናወኑ ባሉ የሥራ ዕድል ፈጠራና የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሥራዎች ውስጥ የፋይናንስ አቅርቦት እጥረት እና ተስማሚ... read more
የባህሬን ወደብ፤የአሜሪካ የባህር ኃይል መርከቦች ለቀው መውጣታቸው ተገለጸ
የዩናይትድ ስቴትስ የባህር ኃይል ንብረት የሆኑ ሁሉም የፊት መስመር መርከቦች ከባህሬን ቁልፍ ወደብ መውጣታቸውን የሳተላይት ምስሎች ማሳየታቸውን ኒውስዊክ ዘግቧል። ይህ... read more
ቻይና በ110 ቀናት ውስጥ የአለማችን ሰፊውን የውሃ ውስጥ ዋሻ በመገንባት ክብረወሰን አስመዘገበች
ሐምሌ 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ቻይና በ110 ቀናት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የአለማችንን እጅግ ሰፊ የውሃ ውስጥ ዋሻ በመገንባት አዲስ ክብረወሰን... read more
ሳዳም ሁሴን በጦርነት ማዕበል ውስጥ የሠራው አስገራሚው የሆሊዉድ ስታይል ፊልም ታሪክ!
ነሐሴ 08 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በታሪክ ውስጥ ከተሠሩት እጅግ አነጋጋሪ እና ያልተለመዱ የፊልም ሥራዎች መካከል የሳዳም ሁሴን ፕሮጀክት የሆነው... read more
ሊቨርፑል ለያን ዲዮማንዴ ያቀረበው የ100 ሚሊዮን ዩሮ የዝውውር ጥያቄ ውድቅ እንደተደረገበት ዴቪድ ኦርንስታይን (David Ornstein) ዘግቧል
ሰኔ 12 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ሊቨርፑል ከተጫዋቹ ወኪሎች ጋር ይፋዊ ንግግር ከጀመረ ሰነባብቷል፤ ይሁን እንጂ ያቀረበው 100 ሚሊዮን ዩሮ ክለቡ... read more
አፍሪካ አቅም ግንባታ ፋውንዴሽን በ33 ዓመታት ጉዞው የአህጉሪቱን የልማት አቅም በማጎልበት ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል ተባለ
መስከረም 27 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአፍሪካ አቅም ግንባታ ፋውንዴሽን (Africa Capacity Building Foundation - ACBF) ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ለ33 ዓመታት... read more
ምላሽ ይስጡ