ሰኔ 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)አገልግሎቱ 100 የከባድ ጭነት ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት በሂደት ላይ መሆኑንም ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ሀገሪቱ የደረሰችበትን የዕድገት ደረጃ የሚመጥን የከባድ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት ለመዘርጋት የ5 ዓመት ዕቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነም ይታወቃል፡፡
የአገልግሎቱ የማርኬቲንግ መምሪያ ኃላፊና ተወካይ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደምሰው በንቲ፤ በመርከብ፣ በከባድ ተሽከርካሪዎችና በሌሎችም ዘርፎች ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ታቅዶ በዚህ ዓመት ብቻ 100 የከባድ ተሽከርካሪዎችን በመግዛት አጠቃላይ ቁጥሩን ወደ 6 መቶ 52 ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ የወደብ ፍላጎቷን ለማሟላት በርካታ ሥራዎችን እየሠራች ባለችበት በአሁኑ ወቅት፤ ፈጣን፣ ዘመናዊና በተለያዩ የቴክኖሎጂ አማራጮች የተሳሰሩ አሰራሮችን መዘርጋት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ አሁን ላይ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በሚያስችል መልኩ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠሩ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ለማስገባት በሂደት ላይ መሆናቸውን አቶ ደምሰው ተናግረዋል፡፡
የባህር ትራንስፖርት ዘርፉ በሰው ሀብት ማብቃት፣ በዘመናዊ አሠራርና በመሣሪያ አቅርቦት ረገድ በሚጠበቀው ልክ አይደለም ያሉት ዳይሬክተሩ፤ እነዚህን ክፍተቶች ለማሟላት የ5 ዓመት ዕቅድ ተነድፎ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠትና አሠራሩን ለማቀላጠፍ በርካታ የማሻሻያ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ራስ ገዙ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ለምሁራን የሰጠሁት “በህግ የተቀመጠ መብት ስላለኝ ነው” ብሏል
👉ትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ ስለተሰጠዉ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ መረጃ እንደሌለዉ ገልጿል፡፡
ታኅሳስ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ትምህርት ሚኒስቴር ከሰሞኑ የፕሮፌሰርነት ማእረግ መስጠት ጉዳይ... read more
በውጭ ሀገር ስራ ስምሪቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል የሰጠው ውክልና የለም ተባለ
ኅዳር 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) “ካናዳን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ለሥራ ዜጎችን እንልካለን፤ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ፍቃድ አግኝተናል” በሚል በተለያዩ የማህበራዊ... read more
ለሰዎች ጅራት ሰርተው እየገጠሙ ያሉት የጃፓን ሳይንቲስቶች
ነሐሴ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጃፓን የሚገኙ ሳይንቲስቶች፣ የሰውን ልጅ ሚዛን ለመጠበቅ የሚረዳ፣ የእንስሳትን ጅራት የሚመስል 'ሮቦቲክ ጅራት' በመንደፍ ፈተና... read more
የቱሪስት ፍሰቱን የሚቆጣጠር የመረጃ ቋት አለመኖር የጎብኚዎች ቁጥር በግምት እንዲሰላ አድርጎታል ተባለ
በተለያዩ ጊዜያት ሀገሪቷን ለመጎብኘት የሚመጡ የሀገር ውስጥ እንዲሁም የውጭ ጎብኚዎች እንዳሉ ቢታወቅም በአብዛኛው በሚባል ደረጃ የጎብኚዎች ቀጥር እየተቀመጠ ያለው በግምት... read more
በኢንዶኔዢያ የመርከብ የእሳት አደጋ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ ከ500 በላይ ተሳፋሪዎች ወደ ባህር በመዝለል ሕይወታቸውን አተረፉ
ሐምሌ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢንዶኔዢያ ሱላዌሲ የባህር ዳርቻ ላይ አንድ ጀልባ በእሳት ከተያያዘ በኋላ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ፣ ከ500 በላይ... read more
የዶናልድ ትራምፕ በዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ ላይ እየጨመረ ያለው ጫና
ነሐሴ 12 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪን በሩሲያ ላይ የሚደረገውን ጦርነት በተመለከተ ጫና... read more
የአሜሪካ ኤምባሲ ማሳሰቢያ የቱሪስት ቪዛን ለህጻናት መውለጃ መጠቀም ላይ
መስከረም 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚኖሩ ዜጎች አዲስ ማሳሰቢያ ይፋ አድርጓል፤ ይህም በቱሪስት ቪዛ... read more
ለወራት በአየር ላይ የሚቆዩት “የሰማይ ላይ ሳተላይቶች”፦ የHALE ድሮኖች አዲስ አስገራሚ ስኬት!
ሚያዚያ 16 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአውሮፕላን ምህንድስናው ዘርፍ ከፍተኛ መነጋገሪያ የሆኑት High-altitude long-endurance (HALE) የተሰኙት ድሮኖች በከፍተኛ ከፍታ ላይ ለረጅም... read more
እድሎችን እና አጋጣሚዎችን በምን መልኩ እንጠቀም?
https://youtu.be/mrcGnMZkczw
read more
በከተማዋ አዳዲስ የሚገነቡ ትምህርት ቤቶች፣ የልዩ ፍላጎት ተማሪዎችን ታሳቢ ባዳረገ መልኩ እንደሚሰሩ ተገለጸ
በአዲስ አበባ ከተማ አዳዲስ በሚገነቡ ትምህርት ቤቶች፣ በሁሉም ዘርፍ የልዩ ፍላጎት ወይም ስፔሻል ኒድ ተማሪዎችን ታሳቢ ተደርገው እንደሚገነቡ የከተማ አስተዳደሩ... read more
ምላሽ ይስጡ