ነሐሴ 29 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን በአዲስ ዓመት ከሥጋ አቅርቦትና ዋጋ ጋር በተያያዘ ሸማቹ ኅብረተሰብ እንዳይቸገር በመዲናዋ ካሉ 274 የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሥጋ ቤቶች ጋር ውይይት መደረጉን አስታውቋል። በቅርቡ በበዓላት ወቅት ከሥጋ አቅርቦትና ዋጋ ጋር በተያያዘ የነበረውን ችግር ለመቅረፍ ኅብረት ሥራ ኮሚሽኑ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጓል። በዚህም በሁሉም የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሥጋ ቤቶች ኅብረተሰቡ ሥጋን በቀላሉ ማግኘት ይችላል ብለዋል። በተጨማሪም በ274ቱም የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሥጋ ቤቶች በ1,200 ብር ብቻ እንዲቀርብ ከሥጋ ቤቶቹ ባለቤቶች ጋር ስምምነት ላይ ተደርሷል። ይሁን እንጂ ከዚህ ዋጋ ውጭ የሚሸጡ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሥጋ ቤቶች ካሉ ኅብረተሰቡ ጥቆማ ማቅረብ ይችላል ብለዋል። ለሥጋ ቤቶቹም በመንግሥት በኩል አስቀድሞ ከበሬ አቅራቢዎች ጋር የትስስር መፍጠር ሥራ በመሠራቱ ምክንያት የሚቀርብ ቅሬታ እንደማይኖር ጠቁመዋል። የአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ለበዓሉ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በሁሉም ምርቶች በኩል ማድረጉ የተገለጸ ሲሆን፣ ሸማቹም ከእሁድ ገበያና ከኅብረት ሥራ ማኅበራት በአማራጭነት እንዲገበያይ ጥሪ ቀርቧል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ