መስከረም 08 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) አዲሱ የፕሪምየር ሊግ ውድድር ዘመን ከተጀመረ አራት ሳምንት ወይም 40 ጨዋታዎች የተደረገ ቢሆንም፣ የእንግሊዝ የስፖርታዊ ውርርድ ተቋማት ከመንበራቸው በመጀመሪያ የሚሰናበቱ አሰልጣኞችን ይፋ አድርገዋል። በዚህ መሠረት የኮቨንትሪ ሲቲው አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ እና የማንቸስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ከሥራ ኃላፊነታቸው የመሰናበት ዕድላቸው በከፍተኛ ሁኔታ የስንብት ሥጋት የተጋረጠባቸው ግለሰቦች ሲሆኑ፣ በተለይም ኮቨንትሪ ሲቲ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ከተመለሰ በኋላ ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ያስመዘገበው ደካማ ውጤት በላምፓርድ ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል። ከፊት ለፊታችን የሚጠበቀው የሦስት ሳምንታት የብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታዎች እረፍት (International break) ለክለብ ባለቤቶች አዲስ አሰልጣኝ ለመቀየር እና ለቀጣይ ጨዋታዎች በቂ ዝግጅት ለማድረግ አመች ጊዜ የሚፈጥር በመሆኑ በአሰልጣኞቹ ላይ ያለው ሥጋት እንዲጨምር አድርጎታል። በዚህ ሳምንት ኮቬንትሪ ሲቲዎች ወደ ሲቲ ግራውንድ አምርተው ከኖቲንጋም ፎረስት ጋር፣ እንዲሁም ማንቸስተር ዩናይትድ ወደ ክራቨን ኮቴጅ በማቅናት ከፉልሃም ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በማንችስተር ደርቢ ጨዋታ ላይ ማንቸስተር ሲቲ በስህተት ያስቆጠረውን ጎል እንዲጸድቅ ያደረገው እና በቪኤአር (VAR) ላይ ተሰይሞ የነበረው ዳኛ ቅጣት ተላልፎበታል
መስከረም 05 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከትላንት በስቲያ በኦልድ ትራፎርድ በተደረገው የማንቸስተር ደርቢ ጨዋታ ላይ የማንቸስተር ሲቲውን አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ ያስቆጠራትን... read more
ቼልሲዎች ከሬናቶ ቬይጋ ጋር በቋሚነት ለመለያየት ዝግጁ ስለመሆናቸው አሳውቀዋል።
ጥር 06 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዝውውር መስኮቱ ሲከፈት ቼልሲ ሁሉ አማረሽ ይመስል የተጫዋቾች አቅም ፤ ክህሎት ከአሰልጣኙ ፍልስፍና ጋር ተጣጥሞ... read more
የሳዑዲ ፕሮ ሊግ ክለብ አልሂላል የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ኦሊ ዋትኪንስን ከአስቶን ቪላ ለማስፈረም ከስምምነት ላይ መድረሱ ተሰማ።
ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዝውውር ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሠራው ታዋቂው ጋዜጠኛ ፋብሪዚዮ ሮማኖ እንደገለጸው፣ ሁለቱ ክለቦች በ58.4 ሚሊዮን... read more
የተጣለ መስታወት ወደ መንገድ ግንባታ — የጃፓን የመልሶ መጠቀም ሙከራ
መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በጃፓን የተጣሉ የመስታወት ጠርሙሶችን እንደገና ጥቅም ላይ በማዋል ለመንገድ ግንባታ የሚሆኑ ጥሬ ዕቃዎችን... read more
አሪያና ሳባሌንካ እና ያኩፕ ሜንሲክ የማዬሚ ኦፕንን አሸነፉ
ዘንድሮ ለ40ኛ ጊዜ በተከናወነው አመታዊው የማዬሚ ኦፕን ሜዳ ቴኒስ ውድድር በአሜሪካ ማዬሚ ግዛት ላይ ሲከናወን በሴቶች የአለም ቁጥር አንዷ አሪና... read more
የአርሰናል እግርኳስ ክለብ የስኬት መንገድ ጠራጊው አንጋፋው አርሰን ቬንገር አዲስ እንዲተገበር ያሰቡት እቅድ ጨዋታ ቀያሪ ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል
ኅዳር 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ፈረንሳዊው የቀድሞው አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር በአሁን ሰአት በአለም አቀፉ የእግርኳስ አወዳዳሪው አካል ፊፋ chief of... read more
ፍይኖርዶች ሩበን ቫን ፐርሲን በአሰልጣኝነት መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል
የ41 አመቱ የቀድሞ የማንቸስተር ዩናይትድ እና የአርሰናል የአጥቂ መስመር ተጫዋች የሆነው ሮቨን ቫን ፐርሲ በኤርዲቪዝዬው እየተጫወተ የሚገኘው ኸረንቪን እያሰለጠነ እንደሚገኝ... read more
ስንብትን አልፈራም ሲል ፔፕ ጋርዲዮላ ሀሳቡን ሰጥቷል
ከዛሬው ተጠባቂ የሻምፒዮንስ ሊግ የknock out Play-off ጨዋታዎች በፊት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በሰጠው የቅድመ ጨዋታ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የትኛው ማንቸስተር... read more
የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ አንጋፋ ተጫዋች ጋሪ ኔቪል የቀድሞ የቡድን አጋሩ እና የአሁኑ የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ላይ ከባድ ትችት ሰንዝሯል
መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ተከላካይ እና የስፖርት ተንታኝ ጋሪ ኔቪል በፉልሃም ጨዋታ ወቅት በማይክል... read more
ያኒክ ሲነር ዌምብልደንን አሸነፈ
ሐምሌ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በAll england club አዘጋጅነት ሲከናወን የቆየው ተወዳጁ እና ትልቁ የሜዳ ቴኒስ ውድድር ዌምብልደን ትላንት ሲጠነመቀቅ በወንዶች... read more
ምላሽ ይስጡ