መስከረም 08 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) አዲሱ የፕሪምየር ሊግ ውድድር ዘመን ከተጀመረ አራት ሳምንት ወይም 40 ጨዋታዎች የተደረገ ቢሆንም፣ የእንግሊዝ የስፖርታዊ ውርርድ ተቋማት ከመንበራቸው በመጀመሪያ የሚሰናበቱ አሰልጣኞችን ይፋ አድርገዋል። በዚህ መሠረት የኮቨንትሪ ሲቲው አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ እና የማንቸስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ከሥራ ኃላፊነታቸው የመሰናበት ዕድላቸው በከፍተኛ ሁኔታ የስንብት ሥጋት የተጋረጠባቸው ግለሰቦች ሲሆኑ፣ በተለይም ኮቨንትሪ ሲቲ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ከተመለሰ በኋላ ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ያስመዘገበው ደካማ ውጤት በላምፓርድ ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል። ከፊት ለፊታችን የሚጠበቀው የሦስት ሳምንታት የብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታዎች እረፍት (International break) ለክለብ ባለቤቶች አዲስ አሰልጣኝ ለመቀየር እና ለቀጣይ ጨዋታዎች በቂ ዝግጅት ለማድረግ አመች ጊዜ የሚፈጥር በመሆኑ በአሰልጣኞቹ ላይ ያለው ሥጋት እንዲጨምር አድርጎታል። በዚህ ሳምንት ኮቬንትሪ ሲቲዎች ወደ ሲቲ ግራውንድ አምርተው ከኖቲንጋም ፎረስት ጋር፣ እንዲሁም ማንቸስተር ዩናይትድ ወደ ክራቨን ኮቴጅ በማቅናት ከፉልሃም ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ኪሊያን ምባፔ 10 ቀን ከሜዳ እንደሚርቅ ተገልጿል
ታኅሳስ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ፈረንሳዊው ኮኮብ ኪሊያን ምባፔ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ 6ኛ ጨዋታ ጣልያን ቤርጋሞ ላይ ሪያል ማድሪድ... read more
የእንግሊዝ ክለቦችን የሚያፋጥጠው የዩሮፓ ሊጉ የፍፃሜ ጨዋታ ዳሰሳ
በክለቦች የውድድር መድረክ ላይ ሁለተኛ እርከን የሚሰጠው የዩሮፓ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ በሁለት እጅግ አስከፊ የውድድር ዘመንን ባሳለፉ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች... read more
የሩበን አሞሪም የመጀመሪያው ፈራሚ ዲዬጎ ሊዮን እንደሚሆን ይገመታል
ጥር 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ17 አመቱ ፓራጓዊ ዲዬጎ ሊዮን ክለቡን በመልቀቅ ሴሮ ፖርቴኖን በመልቀቅ ፊርማውን ለማንቸስተር ዩናይትድ ለማስቀመጥ ወደ... read more
ፊዮሬንቲና ጆሹዋ ዚርክዚን ለማስፈረም የዝውውር ጥያቄ ማቅረቡ ተገለጸ
ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጣሊያኑ ክለብ ፊዮሬንቲና የ25 ዓመቱን የማንቸስተር ዩናይትድ እና የኔዘርላንድስ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ጆሹዋ ዚርክዚን ለማስፈረም... read more
የሳዑዲ ፕሮ ሊግ ክለብ አልሂላል የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ኦሊ ዋትኪንስን ከአስቶን ቪላ ለማስፈረም ከስምምነት ላይ መድረሱ ተሰማ።
ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዝውውር ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሠራው ታዋቂው ጋዜጠኛ ፋብሪዚዮ ሮማኖ እንደገለጸው፣ ሁለቱ ክለቦች በ58.4 ሚሊዮን... read more
«ባሎንዶሩ ለእኔ ነው የሚገባው» ሲል ላሚን ያማል አስተያየቱን ሰጠ
መስከረም 05 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የባርሴሎናው ወጣት አጥቂ ላሚን ያማል የ2026 የባሎንዶር ክብር ለእሱ እንደሚገባው በራስ መተማመን የተሞላበት አስተያየት የሰጠ... read more
ሊቨርፑል – ከቶተንሃም
♻️በመናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 በቀጥታ ይከታተሉ፡፡
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ወደ ለንደን አቅንቶ ቶተንሃምን ይገጥማል።
ይህንን ጫዋታ ስፖርት... read more
የአርሰናል እግርኳስ ክለብ የስኬት መንገድ ጠራጊው አንጋፋው አርሰን ቬንገር አዲስ እንዲተገበር ያሰቡት እቅድ ጨዋታ ቀያሪ ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል
ኅዳር 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ፈረንሳዊው የቀድሞው አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር በአሁን ሰአት በአለም አቀፉ የእግርኳስ አወዳዳሪው አካል ፊፋ chief of... read more
ቡካዮ ሳካ የሻምፒዮንስ ሊግ የሳምንቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተሰይሟል
ታኅሳስ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጥቁሩ ፈርጥ ባሳለፍነው እሮብ በነበረው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የ6ኛ ዙር ጨዋታ ሞኒኮ ላይ 2 ጎል... read more
ለአትሌቲክስ ልኡክ ቡድን የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት መርሀግብር ተከናወነ
ሐምሌ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በናይጄሪያ አቡኩታ በተካሄደው የአፍሪካ ከ18 እና 20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ... read more
ምላሽ ይስጡ