መስከረም 08 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ አጥቂ የሆነው ጆአዎ ፔድሮ ባጋጠመው የጉዳት ህመም ምክንያት ከመጪው ዓለም አቀፍ የወዳጅነት እና የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች ከሀገሩ ብራዚል ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውጪ መሆኑ ተረጋገጧል። ባለፈው ሳምንት ቼልሲ ከሃል ሲቲ ጋር 2-2 በተለያየበት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ላይ ለ90 ደቂቃ ተሰልፎ የአቻነቷን ግብ ያስቆጠረው የ24 ዓመቱ አጥቂ፣ ከጨዋታው በኋላ በተደረጉ የልምምድ መርሃ ግብሮች ላይ ሳይሳተፍ ቀርቷል። የሴሌሳኦዎቹ አሰልጣኝ ካርሎ አንቼሎቲ ለአውስትራሊያ እና ህንድ የወዳጅነት ጨዋታዎች በስብስባቸው ውስጥ አካተውት የነበረ ቢሆንም፣ በጉዳቱ ምክንያት ከስብስቡ ውጪ በመሆኑ የፍሉሚኔሴው ማርቲኔሊ በእሱ ቦታ ተተክቶ መጠራቱን የብራዚል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል። ጆአዎ ፔድሮ በያዝነው አዲሱ የውድድር ዘመን በ4 የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች 3 ግቦችን በማስቆጠር እና 3 ግቦችን አመቻችቶ በመስጠት አስደናቂ አጀማመር ያደረገ ሲሆን፣ የነሐሴ ወር የፕሪምየር ሊጉ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ መመረጡ ይታወሳል። የቼልሲው አሰልጣኝ ሻቢ አሎንሶ በቅርቡ ስለ ተጫዋቹ አጠቃላይ ብቃት ሲናገሩ፣ ከሳጥን ውጪ እና ውስጥ ባለው ሁለገብነት የታከለ የመጫወት ችሎታው የቀድሞውን የሪያል ማድሪድ አንጋፋ ተጫዋች ካሪም ቤንዜማን እንደሚያስታውሳቸው መናገራቸው የሚታወስ ነው። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ፍራንክ ጄምስ ላምፓርድ እና ማይክል ካሪክ የፕሪሚየር ሊጉ ከአሰልጣኝነት የመሰናበት እጣ ፋንታ የተደቀነባቸው 2 አሰልጣኞች መሆናቸው ተገልጿል
መስከረም 08 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) አዲሱ የፕሪምየር ሊግ ውድድር ዘመን ከተጀመረ አራት ሳምንት ወይም 40 ጨዋታዎች የተደረገ ቢሆንም፣ የእንግሊዝ የስፖርታዊ... read more
ሪካርዶ ካሊያፊዮሪ በዚ የውድድር ዘመን ለ4ኛ ጊዜ ጉዳት እንዳጋጠመው እየተገለፀ ነው
ጥር 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ይህ ጣልያናዊ ለጉዳት በጣም ተጋላጭ የሆነ ተጫዋች መሆኑ በተደጋጋሚ ገና ቦሎኛም እያለ የጉዳት ታሪክ በብዛት... read more
ያኒክ ሲነር ዌምብልደንን አሸነፈ
ሐምሌ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በAll england club አዘጋጅነት ሲከናወን የቆየው ተወዳጁ እና ትልቁ የሜዳ ቴኒስ ውድድር ዌምብልደን ትላንት ሲጠነመቀቅ በወንዶች... read more
የአርሰናል የተከላይ መስመር ተጫዋች የሆነው ዩሪየን ቲምበር ጉልበቱ ላይ የቀዶ ጥገና እንደሚያከናውን ተገልጿል
ተያይዞም ሌላው የመሀል ተከላካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነው ዊሊያም ሳሊባ በበኩሉ ተጨማሪ ምርመራዎች እንደሚደረጉለት ክለቡ አሳውቋል።
ዩሪየን ቲምበር ያለፉትን ወራቶች ከነጉዳቱ ሲጫወት... read more
የተጣለ መስታወት ወደ መንገድ ግንባታ — የጃፓን የመልሶ መጠቀም ሙከራ
መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በጃፓን የተጣሉ የመስታወት ጠርሙሶችን እንደገና ጥቅም ላይ በማዋል ለመንገድ ግንባታ የሚሆኑ ጥሬ ዕቃዎችን... read more
ሞሀመድ ሳላህ ዘንድሮ ከሻምፒዮንስ ሊጉ ይበልጥ ፕሪሚየር ሊጉን ማሳካት እፈልጋለሁ ሲል ሀሳቡን ሰጥቷል
ታኅሳስ 26 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ግብፃዊው ኮኮብ ፍርኦኑ ሞ ሳላህ ዘንድሮ አይቀመሴ አቋም ላይ ነው የሚገኘው። በወርሀ ታኅሳስ ብቻ በ7... read more
ሩበን አሞሪም ለማርከስ ራሽፈርድ ንግግር ምላሽ ሰጡ
ታኅሳስ 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በማንቸስተር ዩናይትድ ቤት እህል ውሀው ሊያበቃ ከጫፍ የደረሰው የ27 አመቱ እንግሊዛዊ እኔ በግሌ ክለቡን ለቅቄ አዲስ... read more
ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ እስከ 2029 የማድሪድ ፕሬዚዳንት ሆነው እንደሚቀጥሉ ታወቀ
ስኬታማ የቢዝነስ ሰው እና የክለብ ፕሬዚዳንት እንደሆኑ የሚነገርላቸው ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ሮድሪጌዝ ለተጨማሪ 4 አመት የማድሪድ ፕሬዚዳንት ሆነው እንደሚያገለግሉ በፊርማቸው አረጋግጠዋል።
ለፉክክር... read more
ሪስ ኔልሰን ከአርሰናል ጋር የነበረውን ኮንትራት በጋራ ስምምነት በማቋረጥ ነፃ ተጫዋች መሆኑን የሚጠቁሙ መረጃዎች ወጥተዋል
ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ26 ዓመቱ የእንግሊዝ የክንፍ መስመር ተጫዋች ሪስ ኔልሰን ከአርሰናል ጋር የነበረውን ውል በጋራ ስምምነት በማቋረጥ፣... read more
ሊቨርፑል – ከቶተንሃም
♻️በመናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 በቀጥታ ይከታተሉ፡፡
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ወደ ለንደን አቅንቶ ቶተንሃምን ይገጥማል።
ይህንን ጫዋታ ስፖርት... read more
ምላሽ ይስጡ