መስከረም 08 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከሃምሳ ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ይሳተፉበታል ተብሎ የሚጠበቀው ሁለተኛው ታላቁ የኢሬቻ ሩጫ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ እንደሚካሄድ የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታውቋል። የኦሮሚያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሮዛ ቢያ ለውድድሩ አሸናፊዎች ከፍተኛ የሆነ ሽልማት መዘጋጀቱን በመግለጽ፣ በዚህም በሁለቱም ጾታዎች ለአንደኛ ለወጡት አንድ አንድ ሚሊዮን ብር፣ ለሁለተኛ ሰባት መቶ ሺህ፣ ለሦስተኛ አምስት መቶ ሺህ እያለ እስከ ስድስተኛ ለሚወጡት ሽልማት እንደተዘጋጀላቸው ገልጸዋል። ውድድሩ አስር ኪሎሜትሮችን የሚሸፍን ሲሆን፣ የዲባባ ቤተሰቦች የዚህ ዓመት የውድድሩ ብራንድ አምባሳደሮች መሆናቸውን አስረድተዋል። በዚህ ዓመትም ኢሬቻን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ብቸኛው ውድድር መሆኑን በመግለጽ፣ የተወዳዳሪዎች የምዝገባ ቦታዎች በአዲስ አበባ፣ በአዳማ እና በቢሾፍቱ ከተሞች እንደሚካሄዱ ተናግረዋል። የኦሮሞ አባገዳዎች ኅብረት ዋና ጸሐፊ አባገዳ ጌቱ ተሊላ ሁሉም በአንድነት ሩጫው ላይ እንዲሳተፉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ በበኩላቸው ሩጫውን ጨምሮ ለኢሬቻ ክብረ በዓል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። የመጀመሪያው ታላቁ የኢሬቻ ሩጫ በ2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወሳል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የትራምፕ የታሪፍ መዘግየቶች የንግድ አለመረጋጋትን አባብሰዋል ሲል ተመድ አስጠነቀቀ
ሐምሌ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ)፣ በአሁኑ የአሜሪካ አስተዳደር የሚተገበሩ የታሪፍ ውሳኔዎች መዘግየቶች ዓለም አቀፍ የንግድ አለመረጋጋትን... read more
የአምሰት አመት #የብልፅግና ጉዞ
🔔ከሰብአዊ መብት እስከ ዲሞክራሲ
🔔ከሙስና እሰከ መልካም አስተዳደር
🔔ከውጪ ጉዳይ አስከ ብሔራዊ ጥቅም
🔔ከአመራር እስከ ተቋም ግንባታ
♻️የአምሰት አመት #የብልፅግና ጉዞ ሁሉም ለውይይት ቀርቧል፡፡
ኅዳር... read more
ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘርፉ ላይ ያላትን አቅም ማሳደግ እንድትችል በማድረግ ውስጥ በቴሌኮም ዘርፉ ያሉትን ፖወሮችን ቁጥር መጨመር ላይ መስራት እንደሚኖርባት ተገለፀ
👉ተቋሙ አሁንም ድረስ ፖወሮችን እና የኤሌትሪክ ምሶሶችኖን ወይም ፖሎችን በኪራይ መልክም እየተጠቀመ እንደሚገኝም አስታውቋል።
ጥቅምት 20 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ይህንን ያለው... read more
የኢትዮጵያ መድሃኒት አምራቾች የፋይናስ ችግርን ለመፍታት ከባንኮች ጋር ዳግም ስምምነት ሊደረግ ነዉ ተባለ
በኢትዮጵያ የሚገኙ 13 የመድሃኒት አምራች ፋብሪካዎች የፋይናንስ ችግራቸው ከተፈታ እንደ ሀገር አሁን ላይ ከሚሸፍኑት 30 በመቶ ወደ 60 በመቶ ከፍ... read more
ህፃን አግተው ገንዘብ የጠየቁ ግለሰቦች በጽኑ እስራት ተቀጡ
ግንቦት 05 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ6 ዓመት ህፃን በማገት እና ቤተሰቦቹን ለገንዘብ በመደራደር ወንጀል የተከሰሱ ሁለት ግለሰቦች በ12 እና በ9... read more
የተሻሻለው የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ደንብ ላይ የተደረገው የአገልግሎት ክፍያ ወሰን ጭማሪ የተጋነነ ነው ሲሉ የህግ ባለሙያዎች ተናገሩ
ኅዳር 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የወጣው ረቂቅ ደንብ የክፍያ ወሰን ጭማሪ ከሰሞኑን ለህዝብ ተወካዮች... read more
በኢትዮ ሶማሊያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ኃላፊነት የተሞላበት እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለጸ
ኅዳር 26 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮ ሶማሊያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ኃላፊነት የተሞላበት እርምጃ እንደሚወሰድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር... read more
ኢትዮጵያ በሃገር ደረጃ ያላት የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት 69.5 በመቶ መሆኑ ተገለጸ
ኅዳር 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ በሃገር ደረጃ ያላት የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት 69.5 ከመቶ መሆኑ የተገለፀው መናኸሪያ ሬዲዮ የሃገራችንን... read more
በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ የማይሳተፉ ሃገራትን በተመለከተ ህብረቱ ሃላፊነት ወስዶ ሊሰራበት እንደሚገባ ተጠቆመ
የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በየአመቱ የህብረቱ መቀጫ በሆነችው አዲስ አበባ እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡
በዚህም 55 አባል ሃገራት ያሉት ህብረቱ በየአመቱ በመገናኘት የተለያዩ አህጉሩን... read more
የሕግ ማዕቀፍ የሚሻው የማር ምርት
https://youtu.be/RkEjE2P7sok
read more
ምላሽ ይስጡ