መስከረም 08 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከሃምሳ ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ይሳተፉበታል ተብሎ የሚጠበቀው ሁለተኛው ታላቁ የኢሬቻ ሩጫ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ እንደሚካሄድ የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታውቋል። የኦሮሚያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሮዛ ቢያ ለውድድሩ አሸናፊዎች ከፍተኛ የሆነ ሽልማት መዘጋጀቱን በመግለጽ፣ በዚህም በሁለቱም ጾታዎች ለአንደኛ ለወጡት አንድ አንድ ሚሊዮን ብር፣ ለሁለተኛ ሰባት መቶ ሺህ፣ ለሦስተኛ አምስት መቶ ሺህ እያለ እስከ ስድስተኛ ለሚወጡት ሽልማት እንደተዘጋጀላቸው ገልጸዋል። ውድድሩ አስር ኪሎሜትሮችን የሚሸፍን ሲሆን፣ የዲባባ ቤተሰቦች የዚህ ዓመት የውድድሩ ብራንድ አምባሳደሮች መሆናቸውን አስረድተዋል። በዚህ ዓመትም ኢሬቻን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ብቸኛው ውድድር መሆኑን በመግለጽ፣ የተወዳዳሪዎች የምዝገባ ቦታዎች በአዲስ አበባ፣ በአዳማ እና በቢሾፍቱ ከተሞች እንደሚካሄዱ ተናግረዋል። የኦሮሞ አባገዳዎች ኅብረት ዋና ጸሐፊ አባገዳ ጌቱ ተሊላ ሁሉም በአንድነት ሩጫው ላይ እንዲሳተፉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ በበኩላቸው ሩጫውን ጨምሮ ለኢሬቻ ክብረ በዓል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። የመጀመሪያው ታላቁ የኢሬቻ ሩጫ በ2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወሳል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት እና የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ጭማሪ
በመካከለኛው ምስራቅ በእስራኤል እና በኢራን መካከል ከሰሞኑ የተፈጠረው ከፍተኛ ውጥረት የአለምን የድፍድፍ ነዳጅ ገበያ በእጅጉ አንቀጥቅጧል። እነዚህ ግጭቶች ወደ ሰፊ... read more
በአሜሪካ ላሞች ላይ የVR መነጽር በማድረግ ጭንቀታቸው እንዲቀንስ እየተደረገ ነው ተባለ
👉መነጸሩ አረንጓዴ ሜዳዎችን እንዲያዩና ብዙ ወተት እንዲያመርቱ ያግዛቸዋል ነው የተባለው
ነሐሴ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአሜሪካ በሚገኙ አንዳንድ እርሻዎች ላሞች በረት... read more
በትግራይ እንዴት ሰላም ይስፈን? 👉
https://youtu.be/C9t7w_FLFSI
read more
ከቅመማ ቅመም ምርት ከ3 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለጸ
ታኅሳስ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ከቅመማ ቅመም ምርት የወጪ ንግድ ለማግኘት ከታቀደው እቅድ ከ75 በመቶ በላይ ማሳካት እንደታቻለ የኢትዮጵያ ቡና እና... read more
የአፍሪካ ወጣቶች እጣ-ፋንታ
አፍሪካ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ሃብቶች የታደለች ምቹ መልካ ምድርና ከፍተኛ ቀጥር ያለው ትኩስ የሰው ኃይል ቢኖራትም በሠላም እጦት ምክንያት አፍሪካ... read more
አርሰናል ቤን ዋይትን ለመተካት ዓይናቸውን የሮማው ዌስሊ ፍራንካ ላይ መጣላቸው ተሰማ
መጋቢት 14 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)አርሰናል በክረምቱ የዝውውር መስኮት ቤን ዋይትን በሽያጭ ዝርዝር ውስጥ ሊያካትተው እንደሚችል የሚጠቁሙ ጭምጭምታዎች መደመጥ መጀመራቸውን ተከትሎ፣... read more
ትርክትና ታሪክ ወለድ ችግሮችን ለመፍታት ምሁራን ሃሳብ እንዲያዋጡ ተጠየቀ
በቀሪ የሀገራዊ ምክክር ሂደት የምሁራን ሚና ከፍ ማለት እንዳለበት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዛሬ ባካሄደው ውይይት አስታውቋል።
ኮሚሽኑ ዛሬ ሰኔ 9... read more
ኢትዮጵያ የተቀቀለ ስጋ ለቻይና ልትልክ ነው
ኢትዮጵያ የተቀቀለ ስጋ ለቻይና ልትልክ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን አስታወቀ።
የኢፌደሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች... read more
ለሙት አንሳ ገዳም የገቢ ማሰባሰብ ዘመቻ 30 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡ ተገለጸ
መስከረም 14 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር፣ ምስራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው የሙት አንሳ ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም መነኮሳትን... read more
ምላሽ ይስጡ