መስከረም 08 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) 7ኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ማሸነፉን ተከትሎ ብልጽግና ፓርቲ በያዝነው ወር መጨረሻ አዲስ መንግሥት እንደሚመሰርት ይታወቃል። ይህንን ተከትሎም ምክር ቤቶቹ በየደረጃው ሲመሰረቱ እና ሥራ ሲጀምሩ የሕዝቡን ጥያቄ በሚገባ ማስተናገድ እንዳለባቸው ተጠቁሟል። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የምዕራብ ኦሞ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ በድሉ መአዛ ለአዲስ እና ነባር የምክር ቤት አባላት በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ ሥልጠና መሰጠቱን እና ለሕዝቡ ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ቅድሚያ እንዲሰጡ መደረጉን ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል። ከመንግሥት ምስረታው በፊት ሀገራዊ ምክክር መካሄዱ በራሱ የሕዝቡን ለዘመናት የተከማቹ ችግሮች ለመለየት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል። ይህም ለምክር ቤት አባላቱ ትልቅ እገዛ እንደሚኖረው ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቀዋል። በተያዘው የመስከረም ወር የመጨረሻው ሰኞ ይመሰረታል ተብሎ በሚጠበቀው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አብላጫውን ወንበር ብልፅግና ፓርቲ ማሸነፉ ይታወቃል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ማዕከላት በአሜሪካውያን ላይ የጤና ቀውስ እየፈጠሩ መሆኑ ተሰማ
ግንቦት 12 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአሜሪካ በተለያዩ ግዛቶች በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፉ የመጡት የሰው ሰራሽ አስተውሎት(AI) መረጃ ማዕከላት በአቅራቢያቸው በሚኖሩ ነዋሪዎች... read more
🛑 ሰበር የህክምና ዜና፡ በሰው ግንባር ላይ የበቀለው አስደናቂው አፍንጫ!
መጋቢት 16 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በከባድ ኢንፌክሽን ምክንያት አፍንጫቸውን ላጣ ግለሰብ የተደረገው የህክምና ተዓምር በመላው ዓለም መነጋገሪያ ሆኗል።
የዘመናዊ ቀዶ ጥገና... read more
በዓሉን ምክንያት በማድረግ ደንብ በተላለፉ 280 በሚሆኑ አካላት ላይ የቅጣት እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ
ጥር 03 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት በገና በዓል የተለያዩ ህገ ወጥ ድርጊቶች... read more
የሌሎች ሀገራት የሀገራዊ ምክክር ሂደቶች ለሀገራችን ኢትዮጵያ ምን ትምህርት ይሰጣሉ?
በተለያዩ ሀገራት የተከናወኑ የሀገራዊ ምክክር ሂደቶች ለሀገራችን በጎ የሚሆን ትምህርትን አስቀምጠውልን እንዳለፉ የስነ-ምክክር መዛግብት ያስረዳሉ፡፡
የደቡብ አሜሪካዊቷ ኮሎምቢያ እ.አ.አ ከ2012-2016 ያካሄደችው... read more
በአማራ ክልል ያለው ግጭት ከቀጠለ በርካታ ወገኖች ለአዕምሮ ጤና ችግር ይጋለጣሉ ተባለ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባበር በአማራ ክልል ከሕወሀት ጦርነት ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያሉ ግጭቶች እና ውጥረቶች በተማሪዎች፣ በሴቶች፣... read more
57ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 57ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው ከዓለም... read more
ኔታንያሁ በዶሃ ላይ በተደረገው የእስራኤል ጥቃት ይቅርታ ጠየቁ
መስከረም 20 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ላይ እስራኤል በሰነዘረችው የአየር ጥቃት የኳታር... read more
ኤ አይ ፎር ጉድስ ኢትዮጵያ 5 ሺህ ኢትዮጵያዉያን ተወዳዳሪዎችን በሳይንስ ሙዚየም በሚዘጋጀዉ የሮቦቲክ ዉድድር እንደሚያሳትፍ ገለጸ
ታኅሳስ 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በስያትል አካዳሚ ፤ በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ እና በስራና ክህሎት ሚኒስቴር አጋርነት የሚዘጋጀው ኤ አይ ፎር... read more
መሉጌታ ከበደን (ወሎዬው) የሚዘክር ኮሚቴ ተቋቋመ
ሐምሌ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የአጥቂ መስመር ተጫዋች የሆነው ሙሉጌታ ከበደን የሚዘክር ኮሚቴ በዛሬው... read more
ምላሽ ይስጡ