ነሐሴ 30 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ለረጅም ዓመታት የአብነት ትምህርት በመስጠት የምትታወቀው የታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ገዳም አስተዳደር ይፋ ያደረገው ይህ ፕሮጀክት ቤተክርስቲያኗ ይዛው የመጣችውን ሃይማኖታዊ መሠረት ለማስቀጠል ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ቅዳሜ ነሐሴ 30 በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ተገልጿል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያሉት ስምንት ጉባኤያት ትምህርት ለመስጠ ያስችላል የተባለው ይህ ፕሮጀክት በ10 ሺ 248 ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ ሲሆን፣ አሁን ባለው ዋጋ ጠቅላላ የግንባታ ወጪው 2.5 ቢሊየን ብር እንደሚሆን ነው ግንባታው ግንባታው ሲጥናቀቅ በእንድ ጊዜ 1500 የአብነት ተማሪዎችን መያዝ እንደሚችል የገለጹት የገዳሙ አበምኔት ሊቀ ሊቃውንት ቆሞስ አባ ተክለ ሃይማኖት ወልዱ በተጨማሪም አብሮት የመጣውን የአረጋውያን መርጃና የህጻናት ማሳደጊያ እንደሚያካትት አስታውቀዋል። መስከረም 03 2019 ዓ.ም የመሠረት ድንጋይ የሚቀመጥለትና “ግንባታ ለበዓታ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ፕሮጀክት ስራውን ለመጀመር የሚያስፈልገውን 100 ሚሊየን ብር ለማግኘትም 20 ሺ ምዕመናን እያንዳንዳቸው 5 ሺ ብር የሚሰጡበት የገቢ ማሰባሰቢያ እቅድ መያዙ ተገልጿል። ላለፉት 93 ዓመታት በስምንት ጉባኤ ቤቶች የአብነት ትምህርት ስትሰጥ የቆየችው የታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ገዳም በ1909 ዓ.ም በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ እንደተመሠረተች ይታወቃል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ