ዴማ ሆፕ ሪል እስቴት በ18 ወራት አጭር ጊዜ ውስጥ ግንባታውን ያጠናቀቀውንና ሁለተኛ ሳይቱ የሆነውን ባለ 21 ፎቅ የቦሌ አደይ አበባ 1 ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት በታላቅ ድምቀት አስመርቋል።
በምረቃው መርሃ-ግብር ላይ የድርጅቱ አመራሮች፣ የሳይት ኢንጂነሮች፣ አርክቴክቶች፣ የብራንድ አምባሳደሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው አጋሮች እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ማርሽ ባንድ ተገኝተዋል። ኩባንያው ወደ ዘርፉ በገባ በ30 ወራት ውስጥ 11 ንቁ (Active) የግንባታ ሳይቶች ያሉት ሲሆን፣ ሁለቱን ሳይቶች በጥራት አጠናቆ በይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ለደንበኞቹ ማስረከቡን አስታውቋል።
ዛሬ የተመረቀው ባለ 21 ፎቅ ዘመናዊ ሕንፃ ከንግድ ሱቆች እስከ ቅንጡ አፓርትመንቶች ያካተተ ሲሆን፤ የኳስ ሜዳ፣ ጂም፣ ሁለገብ አዳራሽ እና በርካታ የጋራ መጠቀሚያ አገልግሎቶችን የያዘ መሆኑ ተገልጿል።

የድርጅቱ አመራሮች በሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደገለጹት፤ በሪል እስቴት ዘርፉ የሚታየውን የመኖሪያ ቤቶችን በወቅቱ አለማስረከብ ችግር በመቅረፍ፣ በጥራት እና በፈጣን ጊዜ ውስጥ ቤቶችን ከነካርታቸው አዘጋጅቶ ማስረከብ የኩባንያው ዋነኛ ዓላማ መሆኑን ተናግረዋል።
በተጨማሪም ኩባንያው ከደንበኞች ለቀረበለት የ«ድገሙልን» ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት «አደይ አበባ 2» የተሰኘ አዲስ ፕሮጀክት እዛው በሳይት 1 ፊት ለፊት በይፋ ማስጀመሩን አብስሯል። አዲሱን ፕሮጀክት አስመልክቶ «እንደተወደደ ተደገመ» በሚል መሪ ቃል ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም ለሦስት ቀናት የሚቆይ ልዩ የሽያጭ እና የጉብኝት ኤክስፖ ከልዩ ቅናሽ ጋር መዘጋጀቱ ተመላክቷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ