መስከረም 21 ቀን 2019 (መናኸሪያ ሬዲዮ) — “የተትረፈረፈ ባለጸግነትን ለትውልድ እናወርሳለን” በሚል መሪ ቃል ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እያከናወነ የሚገኘው አፍሪካ ሆልዲንግ ቢዝነስ ግሩፕ፣ የ2025 ሚስ ዎርልድ አፍሪካ አሸናፊ የሆነችውን ዓለም አቀፍ ሞዴል ሀሴት ደረጀን የ“GODU Housing and smart real estate” ብራንድ አምባሳደር አድርጎ መሾሙን አስታወቀ።
ይህንን ሹመት አስመልክቶ በተዘጋጀው መርሐ ግብር ላይ የአፍሪካ ሆልዲንግ ኃላፊዎች፣ ሞዴል ሀሴት ደረጀን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው አርቲስቶች እና ጋዜጠኞች ተገኝተዋል። በአስተሰሰ ስነ-ሰርዓቱ ላይ የተገኘችው ሞዴል ሀሴት ደረጀ በድርጅቱ ውስጥ የሚጠበቅባትን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች።
የድርጅቱ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ደረጀ ማሞዬ በበኩላቸው፣ አፍሪካ ሆልዲንግ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ በሥሩ ከ150 በላይ ድርጅቶችን በማቋቋም ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅዶ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም በዚሁ የዕቅድ ዘመን ውስጥ በ“GODU Housing and smart real estate” አማካኝነት 500 ሺሕ ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ዋና ሥራ አስፈጻሚው አበክረው ገልጸዋል።
ምላሽ ይስጡ