ሰኔ 23 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የፈረንሳይ መከላከያ ሚኒስቴር የሀገሪቱን የባህር ኃይል ይበልጥ ለማዘመንና ስልታዊ አቅሟን ለማሳደግ የያዘችው ታላቅ እቅድ አካል የሆነችውንና በኑክሌር ኃይል የምትሰራውን ‘ደ ግራስ’ (De Grasse) የተሰኘች እጅግ ዘመናዊ የባህር ሰርጓጅ መርከብ በይፋ መረከቡ ታውቋል።
በቼርቦርግ የባህር ወደብ የተገነባችውና በውሃ ውስጥ እስከ 5 ሺህ 200 ቶን ክብደት የመሸከም አቅም ያላት ይህቺ ሰርጓጅ መርከብ፤ ፈረንሳይ እድሜጠገብ የሆኑትን የ‘ሩቢስ’ (Rubis) ዝርያ መርከቦቿን ለመተካት ከቀረጸችው የስድስት ሰርጓጅ መርከቦች ፕሮግራም መካከል የመጨረሻዋና እጅግ አስፈሪዋ መሆኗ ተነግሯል።
የባህር ላይ ጥቃቶችን፣ የረጅም ርቀት የስለላ ስራዎችንና ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽኖችን በልዩ ብቃት የመወጣት አቅም ያላት ይህቺ የ‘ባራኩዳ’ (Barracuda) ዝርያ መርከብ፤ ሙሉ በሙሉ በውሃ ውስጥ ተደብቃ ለ270 ቀናት ያህል ያለ ምንም መቆራረጥ ስራዋን ማከናወን የምትችል ሲሆን 65 የቡድን አባላትንም በውስጧ ትይዛለች። ይበልጥ አስፈሪ የሚያደርጋት ደግሞ በውስጧ የታጠቀቻቸው የባህር ላይ ክሩዝ ሚሳኤሎች፣ የ‘F21’ ከባድ ቶርፔዶዎች እና የ‘Exocet SM39’ የፀረ-መርከብ ሚሳኤሎች መሆናቸውን ወታደራዊ ተንታኞች ገልጸዋል።
የፈረንሳይ የመከላከያ ግዥ ኤጀንሲ (DGA) በበላይነት የመራው ይህ የባራኩዳ ፕሮጀክት፤ በድብቅ የመጓዝ (stealth) እና የረጅም ጊዜ ጽናትን ከኑክሌር አቅም ጋር በማጣመር በአሁኑ ወቅት በአውሮፓ ውስጥ ካሉ እጅግ የላቁና አስፈሪ የኑክሌር ጥቃት ሰርጓጅ መርከብ ንድፎች መካከል ቀዳሚው ተደርጎ ተወስዷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ለአዲሱ የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ የኦዲት መመሪያ እቅድ ትግበራ ተቋማት ቅድመ ስልጠና እንደሚያስፈልጋቸው ተገለጸ
ጥር 22 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ውስጥ ጥራትን አስጠብቆ ለመቀጠል ተቋማትን ኦዲት ማድረግ እንደሚገባ መገለጹን... read more
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የንግድ ፍቃድ እድሳትን በወቅቱ ለመጨረስ የሰዓት ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ
ታኅሳስ 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከሃምሌ 01 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2017 ዓ.ም... read more
ከፍተኛ ኃይል አስተላላፊ መስመር በመውደቁ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኃይል አቅርቦት ተቋረጠ
ኅዳር 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከመንዲ ወደ ጊዳሚና እና አሶሳ የተዘረጋው የከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ትናንት ማታ ሁለት ሰዓት ሰዓት... read more
ወደ ፍጻሜው የደረሰው የጋዛ ተኩስ አቁም ስምምነትና ኔታንያሁ የገጠማቸው የካቢኒያቸው ጫና
https://youtu.be/DTfy1rTwgxI
read more
ሳይንቲስቶች የመብረቅ አደጋን ተቋቁሞ የሚበቅል የዛፍ ዝርያ ማግኘታቸውን አስታወቁ
መብረቅ ከሚመታቸው ዛፎች መካከል አብዛኞቹ ይደርቃሉ፤ ነገር ግን ሳይንቲስቶች ከመብረቅ አደጋ የሚተርፉ ብቻ ሳይሆኑ በአደጋው ምክንያት የሚበቅሉ የዛፍ ዝርያዎች እንዳሉ... read more
ለንጹሕ ኢነርጂ እንደ ግዙፍ ባትሪ የሚያገለግል ታላቅ የውሃ ኃይል ማመንጫ ቻይና እየገነባች ነው
👉በቀን 12 ሚሊዮን ኪሎዋት ሰዓት በማከማቸት ለ2 ሚሊዮን አባወራዎች የኤሌክትሪክ ብርሃን የሚሰጠው ሜጋ ፕሮጀክት! ሐምሌ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የታዳሽ ኃይል... read more
በካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኔይ የሚመራው ሊብራል ፓርቲ የአገሪቱን አጠቃላይ ምርጫ ማሸነፉ ተገለፀ
ማርክ ካርኔይ እና ሊብራል ፓርቲ በካናዳ ምርጫ ድል እንደቀናቸው የተናገሩ ሲሆን፣ የዶናልድ ትራምፕ አቋም ለውጤቱ እንዳገዛቸው ተገልጿል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ... read more
ጀርመን ሙሉ በሙሉ በሃይድሮጂን ኃይል የሚሰራ የባቡር መርከቦችን ስራ አስጀመረች
ሰኔ 23 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ)ጀርመን በዓለም የመጀመሪያውን ሙሉ በሙሉ በሃይድሮጂን ኃይል የሚሰራ የባቡር መርከቦችን በማስጀመር በአረንጓዴ ትራንስፖርት አብዮት ግንባር... read more
ፈጽሞ ድምጽ ማሰማት የማይቻልበት ከጩኸት ነፃ የሆነው የጃፓን ካፌ
መስከረም 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)ከዘመናዊው ዓለም ግርግርና ውጥረት ርቀው የአእምሮ እረፍት የሚሹ ሰዎች መዳረሻ የሆነ አዲስ የካፌ ጽንሰ ሃሳብ... read more
ዩናይትድ ስቴትስ የፍልስጤምን እውቅና በተመለከተ የፈረንሳይን ዕቅድ ‘በፅኑ እንደምትቃወም’ ገለጸች
👉ሳውዲ አረቢያ ግን 'ታሪካዊ ውሳኔ' ስትል አመሰገነች::
ሐምሌ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)አሜሪካ ፍልስጤምን እንደ መንግስት እውቅና ለመስጠት የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን... read more
ምላሽ ይስጡ