ሰኔ 02 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ተግባራዊ በሆነው አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ውስጥ የሀገር በቀል እውቀት ከጽሑፍ ያለፈ ለትግበራ የተዘጋጀ አካሄድ የለም ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ጤና መምህር እና በሀገር በቀል እውቀት ዙሪያ ምርምር የሚያደርጉት ፕሮፌሰር መንገሻ አድማሱ ለጣቢያችን ተናግረዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር የተጠና ጥናት ቢኖረውም ወደ ትግበራ አልገባም የሚሉት ባለሙያው፣ ሰነድ ማዘጋጀትና መተግበር እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ሌሎች ተቋማትም ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ሀገር በቀል እውቀቶችን አካቶ በትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲተገበር ለማስቻል የማስፈጸሚያ ሰነድ እየተዘጋጀ መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር የሀገር በቀል እውቀትና የማህበረሰብ ትስስር ዴስክ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላም አለሙ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል።
ፍኖተ ካርታው መተግበር ከጀመረ ዓመታትን ያስቆጠረ እንደሆነ የተናገሩት ዳይሬክተሯ፣ ነገር ግን የሀገር በቀል እውቀትን አካቶ ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር ለማስቻል የሚቀሩ ስራዎች መኖራቸውን አምነዋል።
ዳይሬክተሯ በሚመሩት የሀገር በቀል እውቀትና የማህበረሰብ ትስስር ዴስክ በኩል የማስፈጸሚያ መመሪያ ሰነድ መዘጋጀቱን ተናግረዋል። ይህ ብቻም ሳይሆን አሁን ላይ በካሪኩለም ወይም በስርዓተ ትምህርት ክፍሉም በኩል እንዲሁ የማስፈጸሚያ መመሪያዎች መቀረጻቸውን ገልጸዋል። ስርዓተ ትምህርቱ ሙሉ በሙሉ የሀገር በቀል እውቀትን እንዲያካትት ለማስቻል ነው በቂ ቅድመ ዝግጅት ያስፈለገው ሲሉም አክለው ተናግረዋል።
አዲስ የትምህርት ፍኖተ ካርታ መቅረጽ ያስፈለገው ሀገር በቀል እውቀቶችን ለማካተት እንደሆነ ካሁን ቀደም የትምህርት ሚኒስትሩ መናገራቸው ይታወሳል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ቼልሲዎች ለማይክ ሜኞ ያቀረቡት የመጀመሪያ ዙር ጥያቄ ውድቅ የተደረገ ሲሆን፥ ሚላኖች እስከ 45 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚጠብቁ አሳውቀዋልቼልሲ እና ማይክ ሜኞ ስማቸው በድጋሚ እየተያያዘ ይገኛል።
ሰኔ 01 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ቼልሲዎች ግብ ጠባቂ ፍለጋ ወደ ገበያው መውጣታቸው የሚታወቅ ሲሆን፤ ዋና ትኩረታቸው የሆነውን ማይክ ሜኞን ለማስፈረም... read more
ኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ በተለያዩ ዘርፎች በጋራ ለመሥራት መስማማታቸው ተገለጸ
ታኅሳስ 08 ቀን 2017 ዓ.ም(መናኸሪያ ሬዲዮ)ኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ በተለያዩ ዘርፎች በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት መፈራረማቸው ተገልጿል፡፡
በስምምነቱ በሰላም እና ፀጥታ፣ ኢኮኖሚ... read more
ተቋሙ ሃገራዊ ግዳጅ እና ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ ነው👉ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ
ታኅሳስ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢፌዴሪ አየር ሃይል ዋና አዛዡ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ አየር ኃይሉ እያከናወናቸው የሚገኙ ዘርፈ ብዙ... read more
የካቲት 12 ሆስፒታልን ወደ ዩኒቨርሲቲነት ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የባለሙያ እጥረት ተግዳሮት መፍጠሩ ተገለጸ
በርካታ የጤና ባለሙያዎችን በማፍራት 102 ዓመታትን ያስቆጠረው የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2016 ዓ.ም ባስቀመጠው የ10 አመት የስትራቴጂ ዕቅድ ኮሌጁን... read more
ሊቨርፑል ፊቱን ወደ ጎንዛሎ ኢናሲዮ በማዞር ይህን ፖርቹጋላዊ የመሀል ተከላካይ ለማስፈረም እንቅስቃሴ መጀመሩን የሚጠቁሙ መረጃዎች ወጡ
ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ሊቨርፑል በዚህ ክረምት የተከላካይ መስመሩን ማጠናከር ዋነኛ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አድርጎ ወደ ዝውውር ገበያው ለመግባት... read more
በትግራይ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ ለማከናወን ከ22 ጊዜ በላይ ውይይት መደረጉ ተገለጸ
ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል አጀንዳ ለማሰባሰብ ክልሉን ወክለው ከሚንቀሳቀሱ ተቋማት ጋር ተደጋጋሚ ውይይት ቢደረግም፣ እስካሁን የሚፈለገው ውጤት... read more
በካናዳ ቅዝቃዜውን የሚያቀልሉ ‘የልብስ ደኖች’፡ ለችግረኞች የሚቀርብ ልብ የሚነካ የሙቀት ስጦታ
መስከረም 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በካናዳ በክረምቱ ወቅት ሰዎችን ከብርድ ለመጠበቅ ያለመ “የልብስ ደኖች” የሚል ልብ የሚነካ ሰብአዊ ተነሳሽነት በመላ... read more
ቻይና ስታርሊንክን በልጣ በ2 ዋት ሌዘር እጅግ ፈጣን ኢንተርኔት ማስተላለፏ ተዘገበ
ሰኔ 23 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ)ቻይና በህዋ ላይ ባደረገችው አስደናቂ ግኝት፣ ከስታርሊንክ (Starlink) በአምስት እጥፍ የሚበልጥ ፈጣን የኢንተርኔት ፍጥነት ማግኘት... read more
ሩሲያ በኪየቭ ላይ በሰነዘረችው ጥቃት የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ
👉40 የሚሆኑ ሰዎች ቆስለዋል ነው የተባለው
ሰኔ 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የሩሲያ ፌዴሬሽን በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ላይ ሰኞ ምሽት በሰነዘረው የአየር... read more
85ኛዉ የአገዉ የፈረሰኞች ማህበር ዓመታዊ በዓል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ
የአገው ፈረሰኞች ማህበር ዓመታዊ በዓል ከ4 ሺህ 500 በላይ ፈረሰኞች እና ከ500 በላይ እግረኞች እንዲሁም የክብር እንግዶች በተገኙበት ዘንድሮ ለ85ኛ... read more
ምላሽ ይስጡ