መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) «የምድር ጌጥ ኢትዮጵያ» በሚል ርዕስ ሲካሄድ የቆየው ታሪካዊና ባህላዊ አውደ ርዕይ የመጎበኛ ጊዜ፣ ከህዝብ የቀረበውን ከፍተኛ ፍላጎትና ጥያቄ መነሻ በማድረግ ለተጨማሪ ሶስት ሳምንታት መራዘሙ የዝግጅቱ አዘጋጅ «የሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት» አስታዉቋል፡፡ አውደ ርዕዩ ከዚህ ቀደም ከነሐሴ 28 እስከ መስከረም 10 ቀን ሲካሄድ የነበረ ቢሆንም፣ በወቅቱ የነበሩ የሃይማኖታዊና የባህላዊ በዓላት መደራረብ እንዲሁም ከቦታ ምቾት ጋር ተያይዘው የነበሩ ችግሮች የጎብኚዎችን ቁጥር እንደገደበዉ ድርጅቱ ገልጻል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ተዘጋጅቶ የቀረበው ይህ አውደ ርዕይ፤ ህፃናትና ቤተሰቦች የሀገራቸውን፣ የሃይማኖታቸውን፤ የቅዱሳት ቤተክርስቲያናትን ታሪክና ቅርሶች በቅርበት የሚያውቁበትን እድል የፈጠረ ነው ተብሏል። ዝግጅቱም በማየት፣ በመዳሰስ፣ በመስማት፣ በማሸተትና በመቅመስ አምስቱንም የስሜት ሕዋሳት በሚያሳትፍ ልዩ አቀራረብ የተዘጋጀ ሲሆን፤ የላሊበላ፣ የአክሱም፣ የደብረ ዳሞና የሌሎችም ታሪካዊ ቦታዎች ምስልና ቅርሶች ቀርበውበታል። በተጨማሪም በቦታው ላይ በርካታ ታሪካዊና ባህላዊ ይዘቶች በመኖራቸው፤ አውደ ርዕዩን ወደፊት «ቋሚ ሙዚየም» ለማድረግ የሚያስችል ሥራ በጥረት ላይ እንደሚገኝ ተጠቅሷል። በዚሁ መሠረት አውደ ርዕዩ ከመስከረም 30 ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት ወር አጋማሽ ድረስ ባሉት ተከታታይ ሶስት ሳምንታት፤ በየሳምንቱ ቅዳሜና እሁድ ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ እንደሚቀጥል ተገልጿል። አስተባባሪዎቹ አክለውም፤ እስካሁን አውደ ርዕዩን ያላዩ ህፃናትና ቤተሰቦች ከጦር ኃይሎች ወደ ቀራኒዮ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው «ሆላንድ ፓርክ» በመገኘት ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ወፎች እጅግ የሚያቃጥል በርበሬ በልተው ለምን አይቃጠሉም? ድንቅ የተፈጥሮ ሚስጥር!
ነሐሴ 06 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) አብዛኞቻችን በምግባችን ላይ ትንሽ ቃሪያ ስንጨምር የአፍ መቃጠል፣ የእንባ መውረድ እና የውኃ ጥም ያጋጥመናል።... read more
ጃፓን ከህዋ የፀሐይ ኃይልን ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል ለመቀየር ሙከራ ልታደርግ ነው
መስከረም 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ጃፓን የፀሐይን ኃይል ከምድር ምህዋር ላይ ያለገደብ አሰባስቦ በገመድ አልባ መንገድ ወደ ምድር የማስተላለፍ ታሪካዊ ሙከራ... read more
የብሔር ተኮር የፌዴራሊዝም ስርዓቱ ምን ያህል የብሔር ብሔረሰቦችን መብት አስጠብቋል?
በሀገራችን ኢትዮጵያ የዜጎች አኗኗር ከቀን ወደ ቀን መልክ እና ሁኔታ እየቀያየረና እየተባባሰ ስለምጣቱ በርካታ ማሳያዎች አሉ። ለዚህም በምክንያትነት የሚነሳው የብሔር... read more
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የቴክኒካል ጥገና ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ገለጸ
👉የፌደራል ቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ከቻይና አጋር አካላት ጋር በጋራ በመሆን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የቴክኒካል ጥገና ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ገለጸ
ነሐሴ... read more
ከደረሰኝ ጋር የተገናኙ ጠቅላላ ወንጀሎች
👉ማንኛውም ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ ያለበት ታክስ ከፋይ ያለደረሰኝ ግብይት ያከናወነ እንደሆነ ከብር 25ሺ (ሃያ አምስት ሺ ብር) እስከ ብር 50... read more
የTwitter ተባባሪ መስራች ጃክ ዶርሲ ያለ ኢንተርኔት የሚሰራ የመልዕክት መላኪያ መተግበሪያ “Bitchat”ን ይፋ አደረገ
ሐምሌ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የTwitter ተባባሪ መስራች የሆኑት ጃክ ዶርሲ (Jack Dorsey) ኢንተርኔት ሳያስፈልገው የሚሰራ አዲስ የመልዕክት መላኪያ መተግበሪያ "Bitchat"ን... read more
የአባይ ግድብ ምረቃ እና ዓለም አቀፍ ዘገባዎች
ሰኔ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ኢትዮጵያ በመጪው የመስከረም ወር የአባይ ወንዝ ታላቁን ህዳሴ ግድብ (GERD) ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ ስትሆን፣ ይህ ሜጋ... read more
በመዲናዋ ፍቃድ እና ህጋዊነት ያላቸው ተንቀሳቃሽ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች 9ሺህ ብቻ ናቸው ተባለ
ሐምሌ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን እንዳስታወቀው አሁንም ድረስ ያለ ፈቃድ የሚንቀሳቀሱ የሞተር ሳይክል ተጠቃሚዎች ስለመኖራቸው አስታውቋል፡፡
መናኸሪያ... read more
በየዓመቱ በደብረ-ታቦር ከተማ የሚከበረውን የፈረስ ጉግስ እና የቅዱስ መርቆሪዮስ በዓልን በዩኒስኮ ለማስመዝገብ ጥናት እየተካሄደ ነው ተባለ
ጥር 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) አሁን ያለንበት የጥር ወር በርካታ መንፈሳዊ እና ባህላዊ ኹነቶች የሚደረግበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከነዚህም መካከል... read more
መርዛማ ብረቶችን በመመገብ ንፁህ ወርቅ የሚያመነጭ ባክቴሪያ ተገኘ
ሐምሌ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ሳይንቲስቶች መርዛማ ብረቶችን ከተመገበ በኋላ ንፁህ ወርቅ የማምረት ችሎታ ያለው ባክቴሪያ መለየታቸውን አስታወቁ። ይህ ግኝት በወርቅ... read more
ምላሽ ይስጡ