መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የዓለም የቱሪዝም ቀን ሲከበር ዘመኑ የደረሰበት የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ለቱሪዝሙ ዘርፍ የሚያመጣው ሚና የሚነገርበትም እንደሆነ የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ ትላንት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ47ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ39ኛ ጊዜ “የዲጂታል አጀንዳ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ለቱሪዝም አዲስ ቅኝት” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር የተገለጸው የዘንድሮው የዓለም የቱሪዝም ቀን ፡ የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች የአገልግሎት ጥራትን ለማስጠበቅ ትኩረት የሚሰጥበትም ወቅት ነው ተብሏል። ቴክኖሎጂው በቱሪዝም ዘርፍ የጎብኚዎችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ መረጃ ለመስጠት፣ የጉዞ ዕቅድና ቆይታ ለማቀላጠፍ፣ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በተቀናጀ መንገድ ለማስተዋወቅ እና የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ሚኒስትሯ ጠቅሰዋል፡፡ የዓለም አቀፍ ቱሪዝም ቀን በማስመልከት በትላንትናው እለት አዲስ የቱሪስት ዲጂታል የመረጃ ማዕከል ተመርቆ ወደ ስራ መግባቱንም ሚኒስትሯ አስታውቀዋል። በዓሉ ከመስከረም 14 እስከ 17 ቀን 2019 ዓ.ም በተለያዩ ፕሮግራሞች የሚከበር ሲሆን ከሚከበርባቸው ኹነቶች መካከልም ጎብኚዎችን ከአዲስ አበባ ወደ ቤኑና መንደር በባቡር ትራንስፖርት ማጓጓዝ፣የጎንደር ቤተ መንግስት እና የጅማ አባ ጅፋር ቤተ-መንግስት የእድሳት ስራዎች ተጠናቀው “ሕይወት በአብያተ መንግስት” በተሰኘ ፕሮጀክት ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚደረጉም ጠቁመዋል። የዘንድሮው የዓለም የቱሪዝም ቀን በጎንደር ከተማ እንደሚከበርና ክብረ በአሉም የዓለም አቀፍ የማይዳሰስ ቅርስ የሆነውን የመስቀል ደመራ በዓል በጋራ ማከበርን እንደሚያካትትም ጭምር ሚኒስትሯ ገልጸዋል። አሁን ላይ በዘርፉ የሚደረጉና የተደረጉ የዲጂታል ስርአት ለውጦችና ተሞክሮዎች ለሰው ሰራሽ አስተውሎት ትግበራም መንገድ የሚከፍቱ በመሆናቸው ጅምሩ ከዘንድሮው የዓለም የቱሪዝም ቀን መሪ ቃልም ጋር የተስማማ እንደሆነ አብራርተዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎትን መጠቀም በተለይ በጎብኚዎች ፍላጎት ላይ ተመስርቶ አገልግሎት ለመስጠት ይበልጥ አጋዥ ስለመሆኑም ተጠቁሟል ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ኢሬቻን ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነጻ በሆነ መልኩ የኦሮሞ አባ ገዳዎች ህብረት ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ብቻ ማክበር እንደሚገባ ተገለጸ
መስከረም 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ዘንድሮም በዓሉ በሚከበርባቸው ሁሉም አከባቢዎች በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ቅድመ በቂ... read more
🛑 ፍጥነት ገዳይ ነው፡ የፍጥነት ወሰንን በማክበር ሕይወትን እንታደግ!🛑
ትራፊክ አደጋ የብዙ ንጹሃን ዜጎች ሕይወት የሚቀጥፍ፣ ቤተሰብን የሚያፈርስ እና አገርን በከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ የሚጎዳ ዋነኛ ችግር ነው። በየቀኑ በዓለምና... read more
የአረንጓዴ አሻራና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያና አሥተዳደር አዋጅ ጸደቀ
ታኅሳስ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ አመት የስራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ ከአለም... read more
ቪኒሲየስ ጁኒየር በሪያል ማድሪድ እስከ 2030 የሚቆይበትን አዲስ ውል ተስማማ
መጋቢት 16 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ሪያል ማድሪድ እና ብራዚላዊው ኮከብ ቪኒሲየስ ጁኒየር በኮንትራት ማራዘሚያ ጉዳይ ላይ ከረጅም ጊዜ ድርድር በኋላ ስምምነት... read more
በኢትዮጵያ በቅርቡ በተደረገ ጥናት 37 በመቶ የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ተጠቃሚ እንዳልሆነ ተገለጸ
ሰኔ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ በቅርቡ በተደረገ ጥናት እስካሁን ካለው የህዝብ ቁጥር የዜሮ አምፖል ተጠቃሚዎችን ጨምሮ 63 በመቶ የሚሆነው... read more
💥 ሰበር ዜና፡ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ «የማይቀመስ ከባድ አደብ የማስተማሪያ ጥቃት እንሰነዝራለን» ሲሉ ዛቱ!
ሐምሌ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ፣ በዮርዳኖስ በሚገኙ የአሜሪካ ኃይሎች ላይ የተቃጣውን... read more
የኅብረት ሥራ ማኅበርን ስንዴ ባልተገባ ዋጋ ሽጠዋል የተባሉ አመራሮች በጽኑ እስራት ተቀጡ
የአምቦ የገበሬ ኅብረት ሥራ ማኅበር የስንዴ ምርትን ባልተገባ ዋጋ በመሸጥ ከ4 ሚሊየን ብር በላይ አሳጥተዋል የተባሉ የማኅበሩ አመራሮች በጽኑ እስራት... read more
በአውስትራሊያ ከ60 በላይ ልጃገረዶች ላይ ጾታዊ ጥቃት የፈጸመው ግለሰብ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት
ኅዳር 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአውስትራሊያ ጨካኙ ሰው የሚል ቅጽል የተሰጠው ግለሰብ የቀድሞ የሕጻናት እንክብካቤ ሠራተኛ በነበረበት ጊዜ ወደ 70... read more
“ምንም ሳላጠፋ ነው የተቀጣሁት” ሲል አነጋጋሪው ተጫዋች ፕሬስቲያኒ በአዲስ ቃለ መጠይቅ ተናገረ
መጋቢት 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ጂያንሉካ ፕሬስቲያኒ በቪኒሲየስ ጁኒየር ላይ የዘረኝነት ስድብ ሰድቧል በሚል የቀረበበትን ክስ በአዲስ ቃለ መጠይቅ ያስተባበለ ሲሆን፤... read more
በአሜሪካ ላሞች ላይ የVR መነጽር በማድረግ ጭንቀታቸው እንዲቀንስ እየተደረገ ነው ተባለ
👉መነጸሩ አረንጓዴ ሜዳዎችን እንዲያዩና ብዙ ወተት እንዲያመርቱ ያግዛቸዋል ነው የተባለው
ነሐሴ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአሜሪካ በሚገኙ አንዳንድ እርሻዎች ላሞች በረት... read more
ምላሽ ይስጡ