መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) መስከረም 17 ቀን የሚከበረውን የመስቀል በዓል ለመታደም እና ሀገሪቷን ለመጎብኘት የሚመጡ ቱሪስቶች በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የኢትዮጵያ ቱሪስት አስጎብኚ ባለሙያዎች ማህበር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል። የመስቀል በዓል በኢትዮጵያ ከሚከበሩ ታላላቅ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ በዓላት አንዱ በመሆኑ፣ ለጎብኚዎች የበዓሉን ሥርዓቶች እንዲሁም የሀገሪቱን ባህል፣ ትውፊት እና እሴቶች በስፋት ለማስተዋወቅ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የማህበሩ ዋና ፀሐፊ አቶ ፋሲል አበበ ገልጸዋል ። በዓሉን ለማክበር የሚመጡ ቱሪስቶች የመስቀል በዓልን ሃይማኖታዊ ሥርዓት በሚገባ እንዲረዱ እና የሀገሪቱን መልካም ገጽታ በሚያሳይ መልኩ ባለሙያዎቹ የማስጎብኘት አገልግሎት እንዲሰጡ ቅድመ ውይይት መደረጉንም አብራርተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ቱሪስቶች አዳዲስ መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ እና በአጠቃላይ በዓሉ ወደሚከበርባቸው የሀገሪቱ ክፍሎች እንደሚወስዷቸው ጠቅሰዋል። የቱሪስቶች ወደ ሀገር ውስጥ መምጣት ከኢኮኖሚ ፋይዳው ባለፈ ሀገሪቱን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ የሚረዳ በመሆኑ፣ ባለሙያዎቹ ሙያውን በተከተለ መንገድ አገልግሎት እንደሚሰጡ ገልጸዋል፡፡ ማህበሩ ከቱሪዝም ሚኒስቴር እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የመስቀል በዓልን እንዲሁም አብሮ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ቀንን ለማክበር በጋራ እየሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በእንግሊዝ አንድ ባልና ሚስት ከኩሽና ካቢኔታቸው ጀርባ ያለውን ግድግዳ በማፍረስ አስፈሪ የሆረር ፊልም የሚመስል ድብቅ ምድር ቤት አገኙ
ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በእንግሊዝ ኬንት ግዛት ውስጥ ለዘጠኝ ዓመታት በኖሩበት መኖሪያ ቤት ውስጥ የነበሩ ባልና ሚስት፣ በኩሽናቸው ውስጥ... read more
በለንደን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን በመጠቀም የመጀመሪያው የአንጎል ዕጢ የማስወገድ ቀዶ ሕክምና በስኬት ተከናውኖ የሕመምተኛው የማየት ብቃት መመለሱ ተገለጸ
ነሐሴ 24 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በለንደን የሚገኘው የብሔራዊ የኒውሮሎጂ እና ኒውሮሰርጀሪ ሆስፒታል ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስቶች በዓለም የታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን በሰው... read more
ቻይና ለባሕር ውስጥ ምርምርና ደኅንነት የሚሆን የሮቦት ዓሣ ይፋ አደረገች
መስከረም 06 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ) ቻይና በባሕር ውስጥ ምርምር እና የደኅንነት ቁጥጥር ዘርፍ አዲስ እምርታ ያሳየችበትንና የሰው ልጅ ቀጥተኛ እጅ... read more
100 አዳዲስ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን አስገብተን አገልግሎት እየሰጡ ነው 👉ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ 100 አዳዲስ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን በማስገባት በቀን 1,408 (97.5%)... read more
ኤዱዋርዶ ሜንዲ ከብሄራዊ ቡድን ራሱን በማግለል ጓንት መስቀሉን ይፋ አድርጓል
መስከረም 05 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ34 ዓመቱ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን እና የሳዑዲ ዓረቢያው አል-አህሊ ግብ ጠባቂ ኤድዋርድ ሜንዲ ከብሔራዊ ቡድን... read more
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የወደሙ የትምህርት ተቋማትን ለመጠገን የሚያስፈልገዉን 3 ቢሊየን ብር የማሰባሰብ ስራ እንደተጀመረ ተገለጸ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት አራት ዓመታት በነበረው ግጭትና በተያያዥ ችግሮች የተነሳ ከ300 ሺሕ ተማሪዎች ውስጥ፣ ከ50 ሺሕ በላይ የሚሆኑት እስከ... read more
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አሰራሩን ሊያሻሽል እንደሚገባ ቋሚ ኮሚቴው አመላከተ
የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ የብድር አሰጣጥና አመላለስ ላይ በቀረበው ኦዲት በተሰጡ ሃሳቦች ላይ የኢትዮጵያ ልማት... read more
ቅሬታን ያስተናገደው የአካባቢ ፅዳትና ውበት
ሙሉ ፕሮግራሙን ለመስማት ከታች የተያያዘውን ሊንክ ይጫኑ
የአካባቢ ፅዳትና ውበት መጠበቅ ከአይን ማረፊያነት ባለፈ ለሰው ልጅ ጤና፣ ደህንነት እና አጠቃላይ የኑሮ... read more
የስኳር መድሃኒት እጥረት የለም ቢባልም በመድሃኒት መሸጫ መደብሮች የኢንሱሊን እጥረት መኖሩ ተገለጸ
ኅዳር 06 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የስኳር መድሃኒት እጥረት እንደሌለ የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ቢገልጽም በመድሃኒት መሸጫ መደብሮች የኢንሱሊን እጥረት መኖሩን... read more
ዛጎል የጉዞ መተግበሪያ በቱሪዝምና በዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ ተገለጸ
ነሐሴ 28 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ፣ የጉዞና የቱሪዝም እንቅስቃሴ ዘመናዊ የዲጂታል መፍትሔዎችን በማቅረብ የሚታወቀው ዛጎል ሴሊቲዮስ ትራቭል፣ በዛሬው ዕለት በሰጠው... read more
ምላሽ ይስጡ