መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) ማንቸስተር ዩናይትድ ቀደም ሲል ባርሴሎና ይጠቀምበት የነበረውን የገቢ ማግኛ መንገድ በመከተል የኦልድ ትራፎርድ ስታዲየሙን የሜዳ ሳር ለደጋፊዎች መሸጥ መጀመሩ ተዘግቧል። ክለቡ 7 ሴንቲሜትር ስፋት ያለውን የኦልድ ትራፎርድ የሜዳ ሳር በብርጭቆ ዕቃ (Turf Cube) ውስጥ አሽጎ በ125 ፓውንድ ለገበያ አቅርቦታል ተብሏል። በታዋቂው የስፖርት ዘጋቢ ፖል ሂርስት እና በታዋቂ የስፖርት መገናኛ ብዙኃን ዘገባ መሠረት፣ ማንቸስተር ዩናይትድ የባርሴሎናን የካምፕ ኑ አሰራር በመከተል የታዋቂውን ኦልድ ትራፎርድ ስታዲየም የሜዳ ሳር ለአንደኛ ደረጃ የትኬት ባለቤቶች (Season-ticket holders) እና ለደጋፊዎች መቸርቸር ጀምሯል። ክለቡ ከ14 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኦልድ ትራፎርድን ሙሉ የሜዳ ሳር በአዲስ መቀየሩን ተከትሎ፣ በቅርቡ የፋይናንስ ሪፖርቱን ይፋ ባደረገበት እና የ47 ሚሊዮን ፓውንድ ዓመታዊ ከታክስ በፊት ኪሳራ ባጋጠመበት ወቅት ይህንን ማድረጉ ተጨማሪ የገቢ ማስገኛ መንገዶችን ለመፈለግ በሚያደርገው ጥረት አካል እንደሆነ ተገልጿል። ክለቡ ጥቂት ግራም ሳር በ125 ፓውንድ ከፍተኛ ዋጋ መሸጡን ተከትሎ ጉዳዩ በእግር ኳስ ደጋፊዎችና በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ መነጋገሪያ እና የቀልድ ርዕስ ሆኗል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የተጣለ መስታወት ወደ መንገድ ግንባታ — የጃፓን የመልሶ መጠቀም ሙከራ
መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በጃፓን የተጣሉ የመስታወት ጠርሙሶችን እንደገና ጥቅም ላይ በማዋል ለመንገድ ግንባታ የሚሆኑ ጥሬ ዕቃዎችን... read more
ማንቸስተር ሲቲዎች ኢሊማን ንዲያዬን ለማስፈረም ጥረት እያደረጉ መሆኑ ተገለጸ
ነሐሴ 23 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ማንቸስተር ሲቲዎች የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት የኤቨርተኑን ኢሊማን ንዲያዬን ለማስፈረም ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ጋዜጠኛ ቤን... read more
የሩበን አሞሪም የመጀመሪያው ፈራሚ ዲዬጎ ሊዮን እንደሚሆን ይገመታል
ጥር 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ17 አመቱ ፓራጓዊ ዲዬጎ ሊዮን ክለቡን በመልቀቅ ሴሮ ፖርቴኖን በመልቀቅ ፊርማውን ለማንቸስተር ዩናይትድ ለማስቀመጥ ወደ... read more
ፍይኖርዶች ሩበን ቫን ፐርሲን በአሰልጣኝነት መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል
የ41 አመቱ የቀድሞ የማንቸስተር ዩናይትድ እና የአርሰናል የአጥቂ መስመር ተጫዋች የሆነው ሮቨን ቫን ፐርሲ በኤርዲቪዝዬው እየተጫወተ የሚገኘው ኸረንቪን እያሰለጠነ እንደሚገኝ... read more
ፍራንክ ጄምስ ላምፓርድ እና ማይክል ካሪክ የፕሪሚየር ሊጉ ከአሰልጣኝነት የመሰናበት እጣ ፋንታ የተደቀነባቸው 2 አሰልጣኞች መሆናቸው ተገልጿል
መስከረም 08 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) አዲሱ የፕሪምየር ሊግ ውድድር ዘመን ከተጀመረ አራት ሳምንት ወይም 40 ጨዋታዎች የተደረገ ቢሆንም፣ የእንግሊዝ የስፖርታዊ... read more
አርሰናል ቀጣይ አመት የሚጠቀሙበትን ማልያ ይፋ አድርገዋል
አርሰናል ከአዲዳስ የትጥቅ አምራች ተቋም ጋር ባላቸው ስምምነት መሰረት በየአመቱ የክለቡን ታሪክ ፤ ማንነትን ሊያሳዩ የሚችሉ ዲዛይኖችን በመጠቀም ሁሌም አዲሱ... read more
ያኒክ ሲነር ዌምብልደንን አሸነፈ
ሐምሌ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በAll england club አዘጋጅነት ሲከናወን የቆየው ተወዳጁ እና ትልቁ የሜዳ ቴኒስ ውድድር ዌምብልደን ትላንት ሲጠነመቀቅ በወንዶች... read more
ፊዮሬንቲና ጆሹዋ ዚርክዚን ለማስፈረም የዝውውር ጥያቄ ማቅረቡ ተገለጸ
ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጣሊያኑ ክለብ ፊዮሬንቲና የ25 ዓመቱን የማንቸስተር ዩናይትድ እና የኔዘርላንድስ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ጆሹዋ ዚርክዚን ለማስፈረም... read more
ዳቪድ አላባ በነፃ ዝውውር ኡዲኔዜን ተቀላቀለ
መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በታዋቂው የዝውውር ጋዜጠኛ ፋብሪዚዮ ሮማኖ ይፋዊ መረጃ መሠረት፣ የቀድሞው የሪያል ማድሪድ እና የባየርን... read more
ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ እስከ 2029 የማድሪድ ፕሬዚዳንት ሆነው እንደሚቀጥሉ ታወቀ
ስኬታማ የቢዝነስ ሰው እና የክለብ ፕሬዚዳንት እንደሆኑ የሚነገርላቸው ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ሮድሪጌዝ ለተጨማሪ 4 አመት የማድሪድ ፕሬዚዳንት ሆነው እንደሚያገለግሉ በፊርማቸው አረጋግጠዋል።
ለፉክክር... read more
ምላሽ ይስጡ