መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) ማንቸስተር ዩናይትድ ቀደም ሲል ባርሴሎና ይጠቀምበት የነበረውን የገቢ ማግኛ መንገድ በመከተል የኦልድ ትራፎርድ ስታዲየሙን የሜዳ ሳር ለደጋፊዎች መሸጥ መጀመሩ ተዘግቧል። ክለቡ 7 ሴንቲሜትር ስፋት ያለውን የኦልድ ትራፎርድ የሜዳ ሳር በብርጭቆ ዕቃ (Turf Cube) ውስጥ አሽጎ በ125 ፓውንድ ለገበያ አቅርቦታል ተብሏል። በታዋቂው የስፖርት ዘጋቢ ፖል ሂርስት እና በታዋቂ የስፖርት መገናኛ ብዙኃን ዘገባ መሠረት፣ ማንቸስተር ዩናይትድ የባርሴሎናን የካምፕ ኑ አሰራር በመከተል የታዋቂውን ኦልድ ትራፎርድ ስታዲየም የሜዳ ሳር ለአንደኛ ደረጃ የትኬት ባለቤቶች (Season-ticket holders) እና ለደጋፊዎች መቸርቸር ጀምሯል። ክለቡ ከ14 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኦልድ ትራፎርድን ሙሉ የሜዳ ሳር በአዲስ መቀየሩን ተከትሎ፣ በቅርቡ የፋይናንስ ሪፖርቱን ይፋ ባደረገበት እና የ47 ሚሊዮን ፓውንድ ዓመታዊ ከታክስ በፊት ኪሳራ ባጋጠመበት ወቅት ይህንን ማድረጉ ተጨማሪ የገቢ ማስገኛ መንገዶችን ለመፈለግ በሚያደርገው ጥረት አካል እንደሆነ ተገልጿል። ክለቡ ጥቂት ግራም ሳር በ125 ፓውንድ ከፍተኛ ዋጋ መሸጡን ተከትሎ ጉዳዩ በእግር ኳስ ደጋፊዎችና በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ መነጋገሪያ እና የቀልድ ርዕስ ሆኗል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ቀነኒሳ በቀለ በጉዳት ምክንያት ከለንደን ማራቶን ውጪ መሆኑን አሳወቀ
በአለም አትሌቲክስ ኤሊቴ ፕላቲኒየም ደረጃ ከተሰጣቸው የማራቶን ውድድሮች መካከል አንዱ የለንደን ማራቶን እንደሆነ ይታወቃል። ዘንድሮ ከ55 ሺሕ በላይ ሯጮች ይሳተፉበታል... read more
የሩበን አሞሪም የመጀመሪያው ፈራሚ ዲዬጎ ሊዮን እንደሚሆን ይገመታል
ጥር 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ17 አመቱ ፓራጓዊ ዲዬጎ ሊዮን ክለቡን በመልቀቅ ሴሮ ፖርቴኖን በመልቀቅ ፊርማውን ለማንቸስተር ዩናይትድ ለማስቀመጥ ወደ... read more
ኪሊያን ምባፔ 10 ቀን ከሜዳ እንደሚርቅ ተገልጿል
ታኅሳስ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ፈረንሳዊው ኮኮብ ኪሊያን ምባፔ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ 6ኛ ጨዋታ ጣልያን ቤርጋሞ ላይ ሪያል ማድሪድ... read more
ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ እስከ 2029 የማድሪድ ፕሬዚዳንት ሆነው እንደሚቀጥሉ ታወቀ
ስኬታማ የቢዝነስ ሰው እና የክለብ ፕሬዚዳንት እንደሆኑ የሚነገርላቸው ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ሮድሪጌዝ ለተጨማሪ 4 አመት የማድሪድ ፕሬዚዳንት ሆነው እንደሚያገለግሉ በፊርማቸው አረጋግጠዋል።
ለፉክክር... read more
ስንብትን አልፈራም ሲል ፔፕ ጋርዲዮላ ሀሳቡን ሰጥቷል
ከዛሬው ተጠባቂ የሻምፒዮንስ ሊግ የknock out Play-off ጨዋታዎች በፊት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በሰጠው የቅድመ ጨዋታ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የትኛው ማንቸስተር... read more
ለአትሌቲክስ ልኡክ ቡድን የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት መርሀግብር ተከናወነ
ሐምሌ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በናይጄሪያ አቡኩታ በተካሄደው የአፍሪካ ከ18 እና 20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ... read more
ጀማል ሙሲያላ የጀርመን ብሄራዊ ቡድን የወንዶች ምርጡ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል
ታኅሳስ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ለባየር ሙኒክ እየተጫወተ የሚገኘው ጀማል ሙሲያላ 56 በመቶ ድምጽ በማግኘት ነው የአመቱ ምርጥ የጀርመን ብሄራዊ... read more
አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ “በዳኛ ስህተት ጎል አስቆጥራችሁ የከተማ ደርቢውን አሸንፋችኋል” ለሚለው ሀሳብ “እኛም ከ3 ዓመት በፊት ብሩኖ ፈርናንዴዝ ላስቆጠረብን ጎል ይቅርታ እየጠበቅን ነው” በማለት እጅግ ያልተጠበቀ አስገራሚ ምላሽ መስጠታቸውን ተከትሎ ጉዳዩ መነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል።
መስከረም 08 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የማንቸስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ እሁድ ዕለት በኦልድ ትራፎርድ ማንቸስተር ዩናይትድን 1-0 ባሸነፉበት የደርቢ... read more
የዩናይትድ አሰልጣኝ የሆነው ሩበን አሞሪም ማርከስ ራሽፈርድ እና አሌሀንድሮ ጋርናቾ ላይ የወሰነው ውሳኔ ተገቢ እና የክለቡ መልሶ ግንባታ አብዮት ቀስቃሽ ነው ሲሉ የቀድሞ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ሀሳብ ሰጥተውበታል
ታኅሳስ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በ195ኛው የማንቹሪያን ደርቢ ከትላንት በስቲያ ዩናይትዶች ማንም ባልጠበቀው መልኩ በአማድ ዲያሎ ተአምር እና ተፆእኖ ፈጣሪነት ከኤቲሀድ... read more
የተጣለ መስታወት ወደ መንገድ ግንባታ — የጃፓን የመልሶ መጠቀም ሙከራ
መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በጃፓን የተጣሉ የመስታወት ጠርሙሶችን እንደገና ጥቅም ላይ በማዋል ለመንገድ ግንባታ የሚሆኑ ጥሬ ዕቃዎችን... read more
ምላሽ ይስጡ