መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) መስከረም 17 ቀን የሚከበረውን የመስቀል በዓል ለመታደም እና ሀገሪቷን ለመጎብኘት የሚመጡ ቱሪስቶች በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የኢትዮጵያ ቱሪስት አስጎብኚ ባለሙያዎች ማህበር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል። የመስቀል በዓል በኢትዮጵያ ከሚከበሩ ታላላቅ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ በዓላት አንዱ በመሆኑ፣ ለጎብኚዎች የበዓሉን ሥርዓቶች እንዲሁም የሀገሪቱን ባህል፣ ትውፊት እና እሴቶች በስፋት ለማስተዋወቅ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የማህበሩ ዋና ፀሐፊ አቶ ፋሲል አበበ ገልጸዋል ። በዓሉን ለማክበር የሚመጡ ቱሪስቶች የመስቀል በዓልን ሃይማኖታዊ ሥርዓት በሚገባ እንዲረዱ እና የሀገሪቱን መልካም ገጽታ በሚያሳይ መልኩ ባለሙያዎቹ የማስጎብኘት አገልግሎት እንዲሰጡ ቅድመ ውይይት መደረጉንም አብራርተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ቱሪስቶች አዳዲስ መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ እና በአጠቃላይ በዓሉ ወደሚከበርባቸው የሀገሪቱ ክፍሎች እንደሚወስዷቸው ጠቅሰዋል። የቱሪስቶች ወደ ሀገር ውስጥ መምጣት ከኢኮኖሚ ፋይዳው ባለፈ ሀገሪቱን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ የሚረዳ በመሆኑ፣ ባለሙያዎቹ ሙያውን በተከተለ መንገድ አገልግሎት እንደሚሰጡ ገልጸዋል፡፡ ማህበሩ ከቱሪዝም ሚኒስቴር እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የመስቀል በዓልን እንዲሁም አብሮ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ቀንን ለማክበር በጋራ እየሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የጸረ-ተህዋሲያን መድሃኒት አቅርቦት ችግር መኖሩን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታወቀ
ኅዳር 06 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጸረ-ተህዋሲያን መድሃኒት አቅርቦት ችግር መኖሩን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
ለጸረ-ተህዋሲያን የሚሆኑ መድሃኒቶች ከድህረ... read more
ከ2019 ዓ.ም. ጀምሮ ስልጠና ሳይወስድ የሚመራ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም አመራር እንደማይኖር የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ነሐሴ 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ይህንን ያለው ዛሬ ባካሄደው የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ላይ ነው። በ2019 ዓ.ም.... read more
ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተሰጠ መግለጫ
ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሚዲያ አገልግሎት በተሰኘ የዜና ማሰራጫ እንደ ሰበር ዜና የተላለፈ መልእክት “በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የውስጥ... read more
ቻይና ለባሕር ውስጥ ምርምርና ደኅንነት የሚሆን የሮቦት ዓሣ ይፋ አደረገች
መስከረም 06 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ) ቻይና በባሕር ውስጥ ምርምር እና የደኅንነት ቁጥጥር ዘርፍ አዲስ እምርታ ያሳየችበትንና የሰው ልጅ ቀጥተኛ እጅ... read more
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አሰራሩን ሊያሻሽል እንደሚገባ ቋሚ ኮሚቴው አመላከተ
የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ የብድር አሰጣጥና አመላለስ ላይ በቀረበው ኦዲት በተሰጡ ሃሳቦች ላይ የኢትዮጵያ ልማት... read more
ለኤርሊንግ ሀላንድ በሲቲ የሚዪቆየውን ውል ለማደስ ተቃርቧል
ኅዳር 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ይፋዊ ንግግሮችን በወኪሉ አማካኝነት ከክለቡ ጋር መጀመሩ ሲገለጽ መቆየቱ አይዘነጋም።
ጎል ማስቆጠርን እና የሚያገኛቸውም እድሎች በሚገባ... read more
የሜክሲኮ ደጋፊዎች አሰልጣኙ ላይ የወሰዱት እርምጃ በብዙ እያነጋገረ ይገኛል
ኅዳር 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የደቡብ አሜሪካ ሀገራት የ2026ቱ የአለም ዋንጫ ጋር ማጣሪያ ጨዋታዎች እያከናወኑ እንደሚገኙ ይታወቃል። ታዲያ ምክሲኮ በሁንዱራስ... read more
ኤዱዋርዶ ሜንዲ ከብሄራዊ ቡድን ራሱን በማግለል ጓንት መስቀሉን ይፋ አድርጓል
መስከረም 05 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ34 ዓመቱ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን እና የሳዑዲ ዓረቢያው አል-አህሊ ግብ ጠባቂ ኤድዋርድ ሜንዲ ከብሔራዊ ቡድን... read more
የስኳር መድሃኒት እጥረት የለም ቢባልም በመድሃኒት መሸጫ መደብሮች የኢንሱሊን እጥረት መኖሩ ተገለጸ
ኅዳር 06 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የስኳር መድሃኒት እጥረት እንደሌለ የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ቢገልጽም በመድሃኒት መሸጫ መደብሮች የኢንሱሊን እጥረት መኖሩን... read more
ቅሬታን ያስተናገደው የአካባቢ ፅዳትና ውበት
ሙሉ ፕሮግራሙን ለመስማት ከታች የተያያዘውን ሊንክ ይጫኑ
የአካባቢ ፅዳትና ውበት መጠበቅ ከአይን ማረፊያነት ባለፈ ለሰው ልጅ ጤና፣ ደህንነት እና አጠቃላይ የኑሮ... read more
ምላሽ ይስጡ