ነሐሴ 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ይህንን ያለው ዛሬ ባካሄደው የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ላይ ነው። በ2019 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት አመራር ማሰልጠኛ ማዕከልን ተግባራዊ ለማድረግ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በጥናት የተደገፈ አሠራርን ከወዲሁ እየተከተለ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሽኔ ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም በነበረው አሠራር ስልጠና ሳይወስዱ አመራር ሆነው የሚቀጥሉ በርካታ ባለሙያዎች እንደነበሩ የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው፣ ከ2019 ዓ.ም. ጀምሮ ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት አመራር ወደ ሥራ ከመግባቱ በፊት ወይም በሥራ ላይ እያለ የአመራር ክህሎት ስልጠና መውሰድ የግድ እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል። በመሆኑም የስልጠና ሞጁሎችንና ግብዓቶችን ዝግጅት በሚመለከት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ማድረጉንም ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም በዘፈቀደ ይከናወኑ የነበሩ ሥራዎችን ለማስተካከል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በባለሙያዎች ጥናት ማስጠናቱንና ጥናቱም የቅድመና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች ወጪና አስተዳደርን፣ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎችና መምህራን እርካታን እንዲሁም ተማሪዎች ከተመረቁ በኋላ ያለውን የመቀጠር ምጣኔ በተመለከተ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተገልጿል። ትምህርት ሚኒስቴር በበርካታ ከፍተኛ ባለሙያዎች ያስጠናቸውን ጥናቶች ተንተርሶ ለቀጣይ ዓመት አዲስ የፖሊሲ ማዕቀፍ እንደሚያዘጋጅም ተገልጿል። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አዳዲስ ጥናቶችን እያስጠና የሚገኘው የከፍተኛ ትምህርት ሪፎርም ከተደረገ ጀምሮ በቅጡ መተግበር ላልጀመሩ ዘርፎች በማስረጃ የተደገፈ ክትትልና አፈጻጸም እንዲኖር ለማድረግ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ