መስከረም 05 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ34 ዓመቱ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን እና የሳዑዲ ዓረቢያው አል-አህሊ ግብ ጠባቂ ኤድዋርድ ሜንዲ ከብሔራዊ ቡድን በይፋ ራሱን ማግለሉን እና የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ቆይታውን በማጠናቀቅ ሀገሩን መወከል ማብቃቱን አስታውቋል። ሜንዲ ይህን ውሳኔውን ለአዲሱ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ፓትሪክ ቪዬራ ቀድሞ ካሳወቀ በኋላ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ገጹ ባስተላለፈው የቪዲዮ መልእክት ለሀገሩ ደጋፊዎች ምስጋናውን አቅርቧል። በስምንት ዓመታት የብሔራዊ ቡድን ቆይታው ለቴራንጋ አንበሶቹ 60 ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን፣ በ31 ጨዋታዎች ላይ ግብ ሳያስተናግድ (Clean Sheet) ይዞ መውጣት ችሏል። ሜንዲ ሴኔጋል በ2021 ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ (AFCON) ሻምፒዮን ስትሆን ግብ ባለማስተናገድ ረገድ ድንቅ ብቃቱን ያሳየ ሲሆን፣ በ2019 እና 2025 የአፍሪካ ዋንጫዎች ቡድኑን ለፍጻሜ ማድረስ እንዲሁም በሁለት የዓለም ዋንጫዎች ላይ መሰለፍ ችሏል። በክለብ ደረጃ በአል-አህሊ ቤት የAFC ቻምፒየንስ ሊግ እና የሳዑዲ ሱፐር ካፕ ዋንጫዎችን ያሸነፈው ሜንዲ፣ በቅርቡ ይፋ በተደረገው የ2026 የባሎንዶር የዓመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ (Yashin Trophy) ዕጩዎች ዝርዝር ውስጥ መካተቱ ይታወሳል።
___
ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
ምላሽ ይስጡ