መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) ሴቶች በግጭት ወቅት ጉዳት እንዳይደርስባቸው የመጠበቅና በሰላምና ደህንነት ዙሪያ ያላቸውን ሚና የማጉላት ሥራ ሊሠራ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት (NEWA) “ብሔራዊ የሴቶች፣ ሰላምና ደህንነት ፎረም” በሚል ባዘጋጀው መድረክ ላይ ገልጿል። የቅንጅቱ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳባ ገብረመድህን የሴቶች ሰላምና ደህንነት አጀንዳ በሴቶች የሰላም ድርድር ተሳትፎ ብቻ ሳይወሰን ከግጭት በመከላከል፣ በጥበቃ እና በአካቶ መተግበር አለበት ብለዋል። በተለይ ግጭት በሚከሰትባቸው አካባቢዎች ሴቶች ከፍተኛ ጉዳት እንደሚደርስባቸው ተናግረው፤ ከግጭቱ በኋላ ለማገገም የሚያስችሏቸው መሠረተ ልማቶችና አገልግሎቶች መጠናከር እንዳለባቸውም አብራርተዋል። በውሳኔ ሰጪ ሂደቶች የሴቶች ዝቅተኛ ተሳትፎ በግጭት ወቅት የበለጠ ሊጎለብቱ የሚችል መሆኑን ጠቅሰው፤ በማኅበረሰብ ደረጃ ሴቶች እያደረጉት ያለው የሰላም እንቅስቃሴ፣ የሴቶች ድርጅቶች የሚያከናውኑት የጥበቃና የድጋፍ ሥራ እንዲሁም ለግጭት ተጎጂዎች የሚሰጡ አገልግሎቶች ታውቀውና ተመዝግበው ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል ብለዋል። በተለይም በዚህ ላይ የሚሠሩ የሴቶች ማኅበራት ጥረቶችንም መደገፍ፣ እነዚህን ጥረቶች ማስተባበር እና ግጭትን ከመከላከል ጀምሮ በሰላም ማስፈን ሂደት ሴቶች የሚኖራቸውን ሚና ማሳደግ እንደሚገባ አመላክተዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የ103 የእሳት ቃጠሎ መንስኤዎችን በፎረንሲክ ምርመራ አጣርቶ ውጤቱን ይፋ አደረገ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2017 ዓ.ም ስድስት ወራት ውስጥ በአዲስ አበባ እና በሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች የደረሱ የ103 የእሳት ቃጠሎ መንስኤዎችን በፎረንሲክ... read more
እስራኤል የጠላትን ድሮኖች በአየር ላይ የመጥለፍ እና ወደ ራሷ ኃይሎች የመምራት ቴክኖሎጂን አዳብራለች ተባለ
ሐምሌ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጦርነት ስልት እና ቴክኖሎጂ አዲስ ምዕራፍ ላይ ደርሷል። እስራኤል የጠላት ድሮኖችን በአየር ላይ እያሉ በመጥለፍ... read more
የጦርነቱ ዋነኛ መነሻ ምክንያት ምንድነው?
ሰኔ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በእስራኤል እና በኢራን መካከል ያለው ግጭት የአጭር ጊዜ ክስተት ሳይሆን ለበርካታ አስርት ዓመታት የዘለቀ ውስብስብና የተደራረበ... read more
የንግድ ቢሮው ከፍተኛ አመራሮች በመዲናዋ ያለውን የቀይ ሽንኩርት ምርት እጥረትና መወደድ ለመፍታት በተለያዩ ክልሎች ፍለጋ መጀመራቸው ተገለጸ
የክረምት ወቅት ሲቃረብ የቀይ ሽንኩርት ምርት መቀነስ እና መወደድ በከተማዋ መከሰቱን ተከትሎ ከፍተኛ አመራሮች ግብረ-ሃይል በማቋቋም በሶስት ክልሎች በቂ... read more
የህብረት ስራ ሸማች ማህበራት ያሉበት ደረጃ ወቅታዊ ሁኔታውን እንደማይመጥን የፌደራል የህብረት ስራ ኮሚሽን ገለጸ
የህብረት ስራ ሸማች ማህበራት አምራቹ ምርቶችን በተገቢው ዋጋ ለገበያ እንዲያቀርብ፤ ሸማቹም አላስፈላጊ በሆነ የዋጋ ጭማሪ እንዳይጎዳ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የፌደራል... read more
ንጋት ግሎባል ኢኒሼቲቭ ለመጀመሪያ ጊዜ ከስደት ተመላሾችን በተለያዩ የሙያ ዘርፎች አሰልጥኖ ማስመረቁን ገለጸ
መስከረም 07 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ንጋት ግሎባል ኢኒሼቲቭ የፕሮጀክቱ ዋነኛ አካል በሆነው የፍልሰት ግንዛቤ ማስጨበጫና የሙያ ስልጠና መሰረት፣ ተመላሾችን በተለያዩ... read more
ኢትዮጵያ በ100 ቢሊዮን ብር ካፒታል የመጀመሪያውን የቤት መግዣ ብድር ማጠናከሪያ ኩባንያ ልታቋቁም ነው
ነሐሴ 28 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) በሀገሪቱ የመጀመሪያው የሆነውን የቤት መግዣ ብድር... read more
በማይናማር የሚገኙ ዜጎችን ማስመለሱ ቢቀጥልም አሁንም በህገ ወጥ መንገድ ወደ ስፍራው የሚያቀኑ ዜጎች መበራከታቸው ተገልጿል
በማይናማር የሚገኙ ዜጎችን ማስመለሱ ቢቀጥልም አሁንም በህገ ወጥ መንገድ ወደ ስፍራው የሚያቀኑ ዜጎች መበራከታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ... read more
በታይዋን ግድብ በመፍረሱ ምክንያት የ17 ሰዎች ሕይወት አለፈ
መስከረም 14 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በታይዋን ደሴት ላይ በሚገኝ አንድ ሰው ሰራሽ ሐይቅ ግድብ በመፍረሱ ምክንያት በደረሰው አደጋ 17... read more
ምላሽ ይስጡ