መስከረም 07 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ንጋት ግሎባል ኢኒሼቲቭ የፕሮጀክቱ ዋነኛ አካል በሆነው የፍልሰት ግንዛቤ ማስጨበጫና የሙያ ስልጠና መሰረት፣ ተመላሾችን በተለያዩ የሙያ መስኮች አሰልጥኖ ለመጀመሪያ ጊዜ በዛሬው እለት ማስመረቁን አስታውቋል። በ10ኛው ዙር የስልጠና መርሃ ግብሩ ለ30 ወጣቶች ስልጠና ሰጥቶ ማስመረቅ መቻሉን የንጋት ግሎባል ኢኒሼቲቭ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል መለሰ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል። ከስደት ተመላሽ ወጣቶቹ በምግብ ዝግጅት፣ በውበት ሳሎን፣ በቤት አያያዝና ላውንደሪ፣ እንዲሁም በልጆች እንክብካቤ የሙያ መስኮች ላይ ስልጠና መውሰዳቸውንም ገልጸዋል። ተቋሙ ከተቋቋመ ገና ሁለተኛ ዓመቱ መሆኑን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ፤ ወጣቶች በሀገራቸው የሥራ እድል ፈጥረው እንዲሰሩና በፍልሰት ዙሪያ ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኙ የሚያግዙ ስልጠናዎችን እንደሚሰጥ አብራርተዋል። በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ 30 ወጣቶችን አሰልጥኖ ቢያስመርቅም፣ ወደፊት ቁጥራቸው በርከት ያሉ ሰልጣኞችን በተለያየ የሙያ ስብጥር አስመርቆ ሥራ ለማስቀጠር እንደሚሰራ ተገልጿል። አሁን ላይ ከተመረቁት 30 ከስደት ተመላሽ ወጣቶች መካከል 11ዱ ሥራ መጀመራቸውን አቶ ዳንኤል ተናግረዋል። ቀሪዎቹ ሰልጣኞችም በቅርቡ ሥራ እንደሚያገኙ በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ስምሪት አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ሰብሃዲን ሱልጣን አስታውቀዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ከሰሞኑን በጸደቀው አዋጅ 1387/2017 መሰረት የሚደረገው ምርመራ ከመደበኛው የወንጀል ምርመራ ሂደት በተለየ ዘዴ መሆኑ ተገለጸ
ሰኔ 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የቀድሞውን አዋጅ 780/2005ን ለማሻሻል የወጣው እና ሰኔ 10/2017 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጸደቀው አዋጅ 1387/2017... read more
ኢትዮጵያ በቅርቡ በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የአቻ ግምገማ ሊታስደርግ እንደምትችል ተገለጸ
በየአመቱ የአፍሪካ ህበረት ጉባኤ ሲካሄድ በኔፓድ አስተባባሪነት የሚካሄደው የአቻ ሀገራት ግምገማ ተጠቃሽ ነው፡፡ በግምገማው ፈቃደኛ የሆኑ ሀገራት በመልካም አስተዳደር ፤... read more
ስጋቱ ተቀጣጥሎ ቀጥሏል
👉
https://youtu.be/D_OV1HZakvU
በትዕግስቱ በቀለ
read more
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በተጨመረለት የ1 ዓመት የስራ ቆይታ አጀንዳዎችን የመቅረፅ እና ይፋ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ ገለጸ
ሰሞኑን የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሦስት ዓመት የስራ... read more
በየመን ዋና ከተማ ላይ የተፈጸመው የእስራኤል የአየር ጥቃት የሁቲ ከፍተኛ አመራሮችን ገድሏል ተባለ
ነሐሴ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የእስራኤል ጦር በየመን ዋና ከተማ በሆነችው ሳና ላይ ባደረሰው የአየር ጥቃት የኢራን ደጋፊ የሆነውን የሁቲ ቡድን... read more
የአሜሪካ መንግሥት ሥራ መቋረጥ አደጋ ሊገጥመው እንደሚችል ዋይት ሃውስ አስታወቀ
መስከረም 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዩናይትድ ስቴትስ ዋይት ሃውስ፣ የፌዴራል ሴኔት የፌዴራል ኤጀንሲዎች ወጪ የሚሸፍነውን ረቂቅ ሕግ (Spending Bill) በጊዜው... read more
የደም ካንሰርን ለመግታት አለምአቀፍ አዲስ ሕክምና ይፋ ሆነ
ሰኔ 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የ"ትሮጃን ፈረስ" ተብሎ የተሰየመው የደም ካንሰር ሕክምና በእንግሊዝ የጤና አገልግሎት (NHS) በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ መቅረብ ጀመረ።... read more
የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ አዲስ አበባ ገቡ
የካቲት 07 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ... read more
በአማራ ክልል የሚገኙ አርሶ አደሮች ማዳበሪያ እንዳንወስድ ተከልክለናል አሉ
የግብርና ሚኒስቴር በበኩሉ ለአማራ ክልል የሚያስፈልገዉን የማዳበሪያ መጠን መላኩን አስታዉቋል፡፡
በአማራ ክልል ያሉ አርሶ አደሮች ለመናኸሪያ ሬዲዮ ባሰሙት ቅሬታ፤ መጪው የበልግ... read more
የአፍሪካ ቁጥር አንድ ባለሀብት አልኮ ዳንጎቴ በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ መካከል ለሚገነባው የ660 ሚሊዮን ዶላር የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር በገንዘብ ድጋፍ ሊያደርጉ ነው
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) ናይጄሪያዊው የአፍሪካ ባለሀብት አልኮ ዳንጎቴ በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መካከል የሚዘረጋውን የ660 ሚሊዮን ዶላር... read more
ምላሽ ይስጡ