መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) ሴቶች በግጭት ወቅት ጉዳት እንዳይደርስባቸው የመጠበቅና በሰላምና ደህንነት ዙሪያ ያላቸውን ሚና የማጉላት ሥራ ሊሠራ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት (NEWA) “ብሔራዊ የሴቶች፣ ሰላምና ደህንነት ፎረም” በሚል ባዘጋጀው መድረክ ላይ ገልጿል። የቅንጅቱ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳባ ገብረመድህን የሴቶች ሰላምና ደህንነት አጀንዳ በሴቶች የሰላም ድርድር ተሳትፎ ብቻ ሳይወሰን ከግጭት በመከላከል፣ በጥበቃ እና በአካቶ መተግበር አለበት ብለዋል። በተለይ ግጭት በሚከሰትባቸው አካባቢዎች ሴቶች ከፍተኛ ጉዳት እንደሚደርስባቸው ተናግረው፤ ከግጭቱ በኋላ ለማገገም የሚያስችሏቸው መሠረተ ልማቶችና አገልግሎቶች መጠናከር እንዳለባቸውም አብራርተዋል። በውሳኔ ሰጪ ሂደቶች የሴቶች ዝቅተኛ ተሳትፎ በግጭት ወቅት የበለጠ ሊጎለብቱ የሚችል መሆኑን ጠቅሰው፤ በማኅበረሰብ ደረጃ ሴቶች እያደረጉት ያለው የሰላም እንቅስቃሴ፣ የሴቶች ድርጅቶች የሚያከናውኑት የጥበቃና የድጋፍ ሥራ እንዲሁም ለግጭት ተጎጂዎች የሚሰጡ አገልግሎቶች ታውቀውና ተመዝግበው ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል ብለዋል። በተለይም በዚህ ላይ የሚሠሩ የሴቶች ማኅበራት ጥረቶችንም መደገፍ፣ እነዚህን ጥረቶች ማስተባበር እና ግጭትን ከመከላከል ጀምሮ በሰላም ማስፈን ሂደት ሴቶች የሚኖራቸውን ሚና ማሳደግ እንደሚገባ አመላክተዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በትግራይ ክልል የሜርኩሪ መርዛማ ኬሚካል በከፍተኛ ሁኔታ አደጋ እያደረሰ መሆኑ ተገለጸ
በክልሉ በማዕድን ዘርፍ ላይ በተደረገ ጥናት በአከባቢው የሜርኩሪ መርዛማ ኬሚካል አጠቃቀም ከፍተኛ አደጋ እያደረሰ መሆኑን ለመናኸሪያ ሬዲዮ የገለጹት በትግራይ ክልል... read more
የኃይል ሥርቆት በፈጸሙ 111 ደንበኞች ላይ ክስ ተመሠረተ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሸገር ሪጅን በ8 ወራት ውስጥ አንድ መቶ አስራ አንድ ደንበኞች የኃይል ሥርቆት መፈጸማቸውን ባደረገው ድንገተኛ ምርመራ እና... read more
በክልል ከተሞች በቤቲንግ ውርርድ ዘርፍ የተሰማሩ ግለሰቦችን መቆጣጠር ባለመቻሉ በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች ለችግር እየተጋለጡ ነው ተብሏል
ኅዳር 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባለፉት ጊዜያት በመዲናዋ በቤቲንግ ውርርድ ዘርፍ የተሰማሩ አካላት ህገ-ወጥ ድርጊትን መቆጣጠር ተችሏል ቢባልም፤ አሁንም ድረስ... read more
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከአዲሱ የኢራን መንግሥት ጋር በኒውክሌር ጉዳይ ላይ በቅርበት ለመሥራት ስምምነት ላይ መደረሱን አስታወቁ
መጋቢት 30 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ከተካሄደው "ውጤታማ የመንግሥት ለውጥ" በኋላ ከአዲሱ የሀገሪቱ አመራር ጋር... read more
የ13 ዓመት ህጻንን መንገድ ላይ ጠብቆ አስገድዶ የደፈረው ግለሠብ በፅኑ እስራት ተቀጣ
ኅዳር 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ተከሳሽ እሠየ ደባሽ የተባለ ግለሰብ በደሐና ወረዳ 014 ቀበሌ ግራር ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ በ2016 ዓ/ም የ13... read more
የውሾች አፍንጫ፡ ከቦምብ መለየት እስከ ካንሰር ምርመራ
መስከረም 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ውሾች ከሰው ልጅ እጅግ የላቀ የሆነ የማሽተት ችሎታ ያላቸው መሆናቸውን ሳይንሳዊ መረጃዎች ያመለክታሉ።
በአፍንጫቸው ውስጥ እስከ... read more
ማረፊያ_እንግዳ
🔰‘‘ስራዬ መረበ’ሽ ነው፤ እሱን ደግሞ የማደርገው በቴአትር ነው!’’- ደራሲና ዳይሬክተር መዓዛ ወርቁ
ከደራሲና ዳይሬክተር መዓዛ ወርቁ ጋር የተደረገ ቆይታ 👉
https://youtu.be/Ik3kU3GWdgM
read more
በአዲስ አበባ ከተማ የእብድ ዉሻ በሽታ የተገኘባቸዉን ዉሾች የማስወገዱ ስራ በመደኛ ሁኔታ መቀጠሉ ተገለጸ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የእንስሳት በሽታ መከላከልና ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ የሺዳኛ በላይሁን የእብድ... read more
የትራምፕ አስተዳደር በ36 ተጨማሪ ሀገራት ላይ የጉዞ እገዳ ለመጣል ማቀዱ ተገልጿል
የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ማስታወሻ አዲሱ የጉዞ እገዳ እቅድ አፍሪካ፣ ካሪቢያን፣ መካከለኛው እስያ እና የፓሲፊክ አገራትን ያነጣጠረ መሆኑ ተገልጿል።
በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ... read more
ለጎረቤት ሀገራት ጠብ አጫሪ እንቅስቃሴዎች ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ምላሽ ያስፈልጋል ተባለ
በኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝቦች መካከል ያለዉን አዎንታዊ ግንኙነት በሚያሳይ መልኩ እና በኤርትራ በኩል ያለውን ነባራዊ ጠብ ቀስቃሽ እንቅስቃሴ ብስለት በሚስተዋልበት ዲፕሎማሲያዊ... read more
ምላሽ ይስጡ